የካቲት ወር በኢትዮጵያ
━━━━✦❁✦━━━━
አገራችን ኢትዮጵያ ካስተናገደቻቸው እና የወደፊት እጣ ፈንታዋን ከወሰኑ የታሪክ ክስተቶች ውስጥ የካቲት ወር ትልቅ ድርሻ አለው።
👇
በ1888 ዓ.ም. አገራችንን ቅኝ ለመግዛት ቋምጦ የመጣውን ወራሪውን የጣሊያን ጦር አያት ቅድመ አያቶቻችን አድዋ ላይ የደመሰሱት በዚህ በያዝነው የየካቲት ወር፤ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም.ነበር። እነሆ ዛሬ አባቶቻችን በደምና በአጥንት በከፈሉት መስዋዕትነት እና ባስመዘገቡት አኩሪ ድል እኛ አንገታችንን ቀና አድርገን የነጻነት ሳይሆን የድል በዓልን እናከብራለን።
👇
በ1969 ዓ.ም. የዚያድ ባሬ ሶማሊያ የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ 700 ኪ.ሜ. ያህል ወደ ውስጥ ዘልቆ ነበር ። ታዲያ በጊዜው በመንግሥት ለውጥ ላይ የነበረችው ኢትዮጵያ ይህን ወራሪ ኃይል ለመመከት በቂና የተዘጋጀ ሰራዊትና የጦር መሳሪያ ባይኖራትም ነጻነቷን ግን አሳልፋ አልሰጠችም። በሶስት ወራት ጊዜ ውስጥ 300,000 ወታደር አሰልጥና ሶማሊያን ድል ስታደርግ ወርቃማው ድል የተመዘገበው የካቲት 26 ቀን 1970 ዓ.ም. ካራማራ ላይ ነበር።
👇
ፋሺስት ኢጣሊያ ከ1927 እስከ 1933 ዓ.ም. ለአምስት ዓመታት ኢትዮጵያን በወረራ ይዞ ቆይቷል። በተለያዩ መንገዶች በጣሊያን ጦር ላይ ጉዳት ለማድረስ ከተደረጉ ሙከራዎች አንዱ የፋሺስቱ እንደራሴ ሮዶልፎ ግራዚያኒን በቦምብ ለመግደል የተደረገው ነው። የግድያ ሙከራው ሲከሽፍ በግራዚያኒ ትዕዛዝ በአዲስ አበባ ላይ መዓት ዘነበባት። ቤቶች ከነነዋሪዎቻቸው እየተዘጉ ተቃጠሉ። በየመንገዱ የተገኘ ሰው እንደ በግ እየተጎተተ ታረደ። በሦስት ቀናት ጭፍጨፋ በአዲስ አበባ ብቻ ከ30 ሺህ በላይ ሰዎች በግፍ የተጨፈጨፉት በዚሁ ወር የካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም. ነበር።
👇
የመጨረሻውን የሰለሞናዊው ስርወ መንግሥት ንጉሠ ነገሥት የአጼ ኃይለ ሥላሴን መንበር የነቀነቀውና ከስልጣን ያወረደው አብዮትም የተቀጣጠለው በዚሁ በየካቲት ወር ነበር። የካቲት 1966 ዓ.ም.።
👇
አጼ ሰርጸ ድንግል፣ አጼ ቴዎድሮስና ንግሥት ዘውዲቱን የመሳሰሉ ነገሥታት የነገሱት በየካቲት ወር ውስጥ ነበር። ከታላላቅ ጦረኞች እና ስመ ጥር የፖለቲካ ሰዎች መካከል ግራኝ አህመድ፣ እቴጌ ጣይቱ፣ ንጉሥ ወልደ ጊዮርጊስ፣ ራስ ደስታ ዳምጠው እና ራስ አሉላ እንግዳን የመሳሰሉት በሥጋ ከዚህ ዓለም ያረፉበት ወርም ነው። የካቲት!
👇
የካቲት ወር ብዙ የስነ-ፅሁፍ ኮከቦቻችንን ያጣንበት ወርም ነው። አቤ ጉበኛ የካቲት 2፣ ስብሐት ገብረ እግዚአብሄር የካቲት 12፣ ጸጋዬ ገብረመድኅን የካቲት 18፣ ማሞ ውድነህ የካቲት 23፣ እንዲሁም ተወዳጁ ደራሲና ጋዜጠኛ በዓሉ ግርማ እንደወጣ የቀረው የካቲት 24 ነበር።
📖 📖 📖 📖 📖
@AdamuReta
@AdamuReta
@isrik