ገላጋይ መስሎ አጥቂ
( ሰሎሞን ደሬሳ )
የተነጠፈልሽ እንድትረጋግጪው
አንች ልጅነቱን ጨክነሽ የቀጨሽው፤
በጨረቃ ብርሃን ጥርሶችሽን ሲቆጥር
በትምህርት ጊዜው አንቺን ሲያሰላስል
እየታየው የከንፈሮችሽ ውበት
ተቃጥሎ በጥርሶችሽ ንጣት
እያጥወለወለው ያይኖችሽ ጥራት ጥልቀት።
ታገኝዋለሽ ዘመን ሲገልጥለት
ዞር ብሎ ሲያይሽ አምስት አመት አልፎ
ያላዋቂ ፍቅሩ በማወቅ ተገፎ
ትዝታ ለውጦት መልክሽን ሲረሳው።
"ኢሾ ኢሾ ያአቦኮ
ቶርቶራዳ? ለፋ ፉቴ
ኢሾ ኢሾ "
1962 ዓ.ም
📚 ልጅነት (መድብል)📚
@AdamuReta
@isrik
( ሰሎሞን ደሬሳ )
የተነጠፈልሽ እንድትረጋግጪው
አንች ልጅነቱን ጨክነሽ የቀጨሽው፤
በጨረቃ ብርሃን ጥርሶችሽን ሲቆጥር
በትምህርት ጊዜው አንቺን ሲያሰላስል
እየታየው የከንፈሮችሽ ውበት
ተቃጥሎ በጥርሶችሽ ንጣት
እያጥወለወለው ያይኖችሽ ጥራት ጥልቀት።
ታገኝዋለሽ ዘመን ሲገልጥለት
ዞር ብሎ ሲያይሽ አምስት አመት አልፎ
ያላዋቂ ፍቅሩ በማወቅ ተገፎ
ትዝታ ለውጦት መልክሽን ሲረሳው።
"ኢሾ ኢሾ ያአቦኮ
ቶርቶራዳ? ለፋ ፉቴ
ኢሾ ኢሾ "
1962 ዓ.ም
📚 ልጅነት (መድብል)📚
@AdamuReta
@isrik