የሳትረ ሥነ ኑባሬ እንደሚያትተዉ፣ የሰዉ ልጅ ህልዉናዉ ከማንነቱ ወይም ተፈጥሮዉ ቀዳሚ በመሆኑ ዕጣ ፈንታዉን በራሱ እጅ የመጻፍ ሥልጣን አለዉ፡፡ በሌላ አነጋገር፣ የሰዉ ልጅ ያለ ረዳት የሚኖር ባይተዋር ፍጡር (abandoned) በመሆኑ አርነቱን ተጠቅሞ ራሱን የመፍጠር ሙሉ ኃላፊነቱ ጫንቃዉ ላይ የወደቀ ነዉ (ሳርተር፣ 2018)፡፡ በሳትረ ኤግዚስቴንሻሊዝም ዉስጥ አርነት እና ኃላፊነት የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸዉ፡፡ ባይተዋርነት በሳትረ ግብረ ገብ ዉስጥ የሚገኝ ዐቢይ ሴማም ነዉ፡፡ ይህ ሴማ የሳትረን ኢ-አማኝነት (atheism) የሚሰብክ ነዉ፡፡ ሳትረ ፈጣሪ (God) በህልዉና አለ ብሎ አያምንም፡፡ ፈጣሪ በህልዉና ባለመኖሩ ምክንያትም የሰዉ ልጅ እንዴት መኖር እንደሚገባዉ ፍፁማዊ (a priori) የግብረ ገብ ሕግጋትን የደነገገለት አካል የለም፡፡ በእዚህም የተነሳ፣ እያንዳንዱ ግለሰብ የራሱን የግብረ ገብ እሴት ፈጥሮ ሕይወቱን የመምራት ኃላፊነት አለበት፡፡ ሳትረ የፊዮዶር ዶስቶቭስኪን ንግግር ጠቅሶ እንደሚነግረን፣ ፈጣሪ በህልዉና ከሌለ ሁሉም ነገር የተፈቀደ ነዉ (ሳትረ፣ 2007)፡፡
እንደ ሳትረ (2018) እሳቤ፣ ቁሶች (being-in-itself) ተሟልተዉ የተፈጠሩ አካላት በመሆናቸዉ ዕድል ፈንታቸዉን በምርጫቸው የመቀየስ ኃይል የላቸውም፡፡ ጠረጴዛ ተሟልቶ የተፈጠረ ቁስ በመሆኑ ባለበት ፀንቶ ኗሪ ነው፡፡ ፈፅሞ በሥልጣኑ ራሱን መለወጥ አይችልም፡፡ የቁስ ተፈጥሮ ከህልዉናዉ ቀዳሚ ነዉ፡፡ በመሆኑም፣ ቁስ የሳቢያ እና ዉጤት ሕጎች (causal laws) ይተገበርበታል (ገቲንግ፣ 2001)፡፡ በተቃራኒዉ፣ የሰዉ ልጅ ከሳቢያ እና ዉጤት ሕግ እግር ብረት (causal determination) ነፃ ነዉ፡፡ ሰዉ ዕድል ፈንታዉን በተለመው መንገድ የመቀየስ ኃይል ያገኘዉ ልክ እንደ ቁስ ሙሉ ፍጡር ባለመሆኑ ነዉ (ዳግል፣ 2011፤ ፍሮንዲዚ፣ 1981)፡፡
አለንጋና ምስር እና ሌሎች አጫጭር ታሪኮች በተሰኘዉ የአዳም የአጫጭር ልብ ወለዶች መድብል ዉስጥ የቀረበዉ ኦቾሎኒ የተሰኘዉ አጭር ትረካ ከላይ የተመለከትነዉ ፍልስፍናዊ ዐሳብ በጥልቀት የተዳሰሰበት ሥራ ነዉ፡፡ ኦቾሎኒ ዉስጥ የተሳለዉ ዋና ገጸባሕርይ ስምዖን የእኛ የሰዉ ልጆች ባሕርይ (our character traits) በሥልጣናችን እንድንሆን ከመሰነዉ ዉሳኔ ዉጭ አለመሆኑን ተገንዝቦ የቀደመ ማንነቱን በራሱ ኃይል ሲለዉጥ እናገኘዋለን፡፡ ስምዖን ሰዉ በመሆኑ የተጎናፀፈዉን ፍፁማዊ አርነቱን ተጠቅሞ ማንነቱን በአዲስ መልክ ከመፍጠሩ በፊት በልጅነቱ ዘመን ሰዎች መልከ ጥፉነቱን እየጠቀሱ መስደባቸዉ ከባድ የበታችነት ስሜት ፈጥሮበት ሕይወቱ ሐዘን ያጠለበት ነበር (አዳም፣ 2001)፡፡
ስምዖን ኋላ ላይ ከላይ የነገረንን ተጣብቶት የኖረዉን የዝቅተኝነት ስሜት ሲኒማ ሊመለከት ከባልንጀሮቹ ጋር ፒያሳ ሲኒማ ኢትዮጵያ አቅንቶ ሳለ ሲኒማ ቤት ዉስጥ የተዋወቃት ልጃገረድ ሲታይ በነበረዉ ሲኒማ ዉስጥ የሚተዉነዉ ፈረንጅ ተዋናይ መልክ ከእሱ መልክ ጋር እንደሚመሳሰል ለእሱ እና ለወዳጆቹ በመጥቀሷ ምክንያት አሸንፎ ተቀባይነቱን ያረጋገጠባትን ‘ኦቾሎኒ’ ብሎ የሚጠራትን ሴት ለመጀመሪያ ጊዜ ለመተዋወቅ (ለመጥበስ) የቻለዉ በራሱ ሥልጣን ነዉ፡፡ ይህ ገጸባሕርይ ኋላ ላይ ከኦቾሎኒ በተጨማሪ ሌሎች ሴቶችን የሚያማግጥ ሴት አዉል (womanizer) ወደ መሆን እንደተሸጋገረም ከላይ በተጠቀሰዉ ትረካ ዉስጥ ይነግረናል፡፡ አዳም የሚከተለዉን ጽፏል፦
እና ግን እየቆየ በራስ መተማመኔ እያደገ ሌላ ሴት እንደሚፈልገኝ፣ እንደሚያየኝ ስረዳ ትሰለቸኝ ጀመር፡፡ በቀን በቀን ካላገኘሁሽ የምላት በመጀመሪያ ሁለት ቀን፣ በሚቀጥለዉ ጊዜ ሦስት ቀን እያለ ለሳምንትና ለወር የቀጠሮአችን ጊዜ መስፋት ጀመረ፡፡ የገባትም መሰለኝ፡፡ እኔ በተገኘዉ ክፍት ቦታ ሌሎች ሴቶችን ማማለል ወጣሁ፡፡ ብዙ ቀላቀልኩ፡፡ ቀድሞ ችላ የሚሉኝ የሚመስለኝን ደፈርኩ (አዳም፣ 2001፡ገጽ 270)፡፡
… እዚያዉ አጠገብዋ ዉለታ-ቢስ ነዉ የሆንኩት፡፡ ብዙ አልተጓዝኩም፡፡ ጐንዋ ቆሜ እየዳበስኳት ነዉ የከዳኋት፡፡ ክፉ አልተናገረችኝም፡፡ አልተናገረችኝም ማለት አልገባትም ማለት አይደለም፡፡ እኔ ግን የገመትኩት እንደዚያ ነበር፡፡ ምን እንደነካኝ አላዉቅም፡፡ ሲያጋጥመዉ አፌ ደ’ሞ ሊያታልላት ይፈልጋል …
“ትወደኛለህ?” ስትለኝ፡፡
“ኦቾሎኒዬ አይደለሽ” እላታለሁ፡፡
እህቴ ባል አግብታ አሜሪካ ስትሄድ መሸኛ ፓርቲ ተደርጎ አልጠራኋትም፡፡ ያን ማታ የመጣችዉ ሌላ ከእስዋ የተሻለች የምትመስል ‘አራዳ’ ቢጤ ናት፡፡ (‘አንቺ ሰዉዬ ትለዋዉጪያለሽ’ ሲሉኝ እኮራ ነበር ሀሀሀሀ!!!) (አዳም፣ 2001፡ገጽ 271-272)፡፡
እቴሜቴ ሎሚ ሽታ የተሰኘዉ የአዳም የአጫጭር ልብ ወለዶች መድበል ከላይ የዳሰስነዉ ፍፁማዊ አርነት ብለን የምንጠራዉ ፍልስፍናዊ ጽንሰ ዐሳብ የተፈከረበት ሌላኛዉ ሥራ ነዉ፡፡ እቴሜቴ ሎሚ ሽታ የተሰኘዉ አጭር ልብ ወለድ ይህ ፍልስፍናዊ ጭብጥ በጥልቀት የተዳሰሰበት የመድበሉ መጠሪያ ነዉ፡፡ እቴሜቴ ሎሚ ሽታ አጭር ልብ ወለድ ዉስጥ የተሳለችዉ ዋና ገጸባሕርይ ሎሚ ሽታ ግላዊ ምርጫዋን ተጠቅማ ሕይወቷን በአዲስ ጎደና የቀየሰች ሴት ናት፡፡ ደራሲዉ እዚህ ታሪክ ዉስጥ እንደሚነግረን፣ ይቺ ሴት ከሕግ ባሏ ታደሰ ጋር ትመራዉ የነበረዉ ሕይወት ድባቴ ያጠላበትና ሙሉ ደስታ ያልነበረዉ ሕይወት ነበር፡፡ ይህ የሆነዉ ደግሞ ባሏ ታደሰ ወሲባዊ አምሮቷን በምትፈልገዉ ልክ ሊያረካላት የሚችል ወንድ አለመሆኑ ነበር፡፡ አዳም የሚከተለዉን ጽፏል፦
ከላይ አያለሁ፡፡ በምሽት ሞተሩን አስነስቶ ሲከንፍ፡፡ ሦስተኛ ቀኑ ነዉ፡፡ እያስጮኸ ሞተር ሲያስነሳ፡፡ ለካስ የእኔ ሱስ ነበረበት፡፡ ደስ ይላል፡፡ የወደደን ራቅ አድርጎ ወደ ሌላ ወደ ወደደ መሸጋገር፡፡ እንዴት ነዉ ብልግና አይሆንም፡፡ ባል መለወጥ ይባላል፡፡ ለአፍታ እኔ ወደነበርኩበት ቀና ብሎ ያየ መሰለኝ፡፡ ያቺ ቀልቃላ ልጅ የት እንዳለሁ ነግራዉ ይሆናል፡፡ ደስ የሚሉ ዐይኖች ነበሩት፡፡ ታደሰ መልካም ዓይኖች ነበሩት፡፡ ልንተኛ ወይ ሊተኛ ሲል ሶፋዉ ዙሪያ እየተሽከረከረ ስራ ፈቶች የተበተቡትን ግጥም የሚባል ነገር ያነብልኝ ነበር፡፡ የሚያስፈራ፡፡ ገላልጦ እያሳየ የሚያስፈራ፡ ሴት ሳይሆኑ የሴትን ልብ እናዉቃለን የሚሉ ገጣሚዎች፡፡ አፍቃሪ መስዬ አሰቃይቼዋለሁ፡፡ ግን ደ’ሞ እኔ እንደ አንድ ግለሰብ የፈለግሁትን መምረጥ የመቻል መብት እንዳለኝ መዘንጋት የለበትም፡፡ ምን አንቀለቀለዉ ግን? ቢጋጭ ከሆነ ግንብ ጋር? ወይም አህያ ገጭቶ እንደ አህያ ቢሞትስ? ምን ሆንኩ ነዉ? መጀመሪያ አጠገቡ እያለሁ ወንድ መሆን ነበር፡፡ በሚያስፈልግበት ጊዜ ወንድ አይሆኑም፡፡ በእሷ ምክንያት ሞተ ለመባል ነዉ? ጤነኛዉን ሰዉዬ አሳበደችዉ እንዲባልለት ነዉ? በእኔ ላይ ሊያስፈርድ ነዉ? እሷ እንዲህ አድርጋዉ እንዲህ ሆነ ሊያሰኝ? የጠበቃ ተንኮል፡፡ ወይስ ገና ለገና ከዚህ ጉብታ ላይ አይቼዉ ‘እኔን! እኔን! እኔን!’ ብዬ ተንደርድሬ እንድመለስለት ነዉ? ልጅ አደረገኝ? አጠገባቸዉ ተጋድሞ ያልመተሩት ስጋ በጮሌ ድመት ሲወስድባቸዉ የሚነጫነጩ ስንት ዉሾች አሉ (አዳም፣ 2001፡ገጽ104)፡፡