በአዲስ አበባ ከተማ ደንበኞች የባንክ አካውንት ለመክፈት “ፋይዳ” የዲጂታል መታወቂያ በግዴታነት እንዲያቀርቡ ታዟል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከቀጣዩ ወር ታህሳስ 23/2017 ዓ.ም. ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ደንበኞች የባንክ አካውንት ለመክፈት “ፋይዳ” የተሰኘውን የዲጂታል መታወቂያ በግዴታነት እንዲያቀርቡ አዘዘ።
ከሁለት ዓመት በኋላ ደግሞ በመላ አገሪቱ የሚገኙ ደንበኞች የትኛውንም የባንክ አገልግሎት ለማግኘት የፋይዳ መታወቂያ እንዲይዙ መገደድ እንደሚጀምሩ ባንኩ አስታውቋል።
ብሔራዊ ባንክ፤ የ“ፋይዳ” ዲጂታል መታወቂያ ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ በአስገዳጅነት ጥቅም ላይ እንዲውል ያዘዘው ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ ሕዳር 17/2017 ዓ.ም. ለሁሉም ባንኮች በጻፈው ደብዳቤ ነው።
እያንዳንዱ ሰው የሚለይበት ባለ 12-አሃዝ ልዩ መለያ ቁጥር እንዲያገኝ የሚያስችለው የ“ፋይዳ” መታወቂያ፤ የነዋሪዎች የባዮሜትሪክ መረጃዎችን በመውሰድ ምዝገባ የሚደረግበት ስርዓት ነው።
የጣት አሻራ፣ አይን አይሪስ ስካን እና የፊት ምስል ነዋሪዎች መታወቂያውን ለማግኘት የሚያቀርቧቸው የባዮማትሪክ መረጃዎች ናቸው።እስካሁን ድረስም ከ10 ሚሊዮን በላይ ደንበኞች ይህንን የዲጂታል መታወቂያ ለማግኘት እንደተመዘገቡ የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም መረጃ ያመለክታል።
ይህ አስገዳጅ አሰራር በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ተግባራዊ መሆን የሚጀምረው በተለያየ ጊዜ እንደሆነም ባንኩ ገልጿል።የብሔራዊ ባንክ ደብዳቤ እንደሚያስረዳው አዲሱ አሰራር ተግባራዊ መሆን የሚጀምረው በአዲስ አበባ ከተማ ነው።
@Addis_Mereja