መምህሩ 4,000,000 / አራት ሚሊየን / ብር ተሸለመ !
የሀዋሳ ከተማ ነዋሪው መምህር ማሙሽ ሔኖክ ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ሎተሪ የመቁረጥ ልምድ ያለው ሲሆን በተለይ የአድማስ ዲጂታል ሎተሪ ዕጣ ከተጀመረ ወዲህ በየዙሩ አድማስ ሎተሪን ይቆርጣል ፡፡ ታዲያ እንደተለመደው የ27ኛው ዙር የአድማስ ዲጂታል ሎተሪ በመቁረጥ የመውጫውን ቀን ሲጠባበቅ ነበር እና ዕጣው ከወጣ በኋላ በማግስቱ ለማመን የከበደው ስልክ ከኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ተደውሎለት የ4ሚሊየን ብር አሽናፊ መሆኑን ብስራቱ ይነገረዋል ፡፡ ለማመንም ከበደኝ ይላል መምህር ማሙሽ ፡፡ ታዲያ የ4 ሚሊየን ብር ቼኩን ከኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ተረክበዋል ፡፡ በደረሰውም ገንዘብ የንግድ ስራ ለመጀመር እንዳቀደ ተናግረዋል ፡፡