........ ባለ ቅኔ..........
ብዙ ተራኪያን ብዙ ሰዉ ዜመኛ
ብዙ ሰአሊያን ብዙ ሰራተኛ
ሁሉ ባለቅኔ ባለሰም ባለወርቅ
ሁሉን ሁሉ አዋቂ ነገር አራቃቂ
ለሚሰራዉ ስራ ምክንያት ጠያቂ
ለሚገጥመዉ ግጥም ለሚቀኘዉ ቅኔ ርእስ ፈላጊ
ሁሉ ሰዉ ፈራጅ ነዉ ሁሉ ትምክተኛ
ሁሉ ተናጋሪ ሁሉም ወቃሽ ዳኛ
ሁሉ ቅኔ አለዉ እርእስ ሳይኖረዉ
ብርቱ በደካማዉ ጎበዝ በሰነፉ የሚቀባበለዉ
ከማወቁ ጀርባ አንዳንድ አለማወቅ ደብቆ የያዘዉ
ሁሉ ቅኔ አለዉ ርእስ የሌለዉ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
በረቀቀ አይምሮ ልቆ በመጠቀ
ባራሙቻ ስልጣኔ ህሊናን የሸጠ
ቅኔ አለኝ ይላል ሰም ወርቁን እያጣ
ምላስ አለዉና አፍ ስራ አይፈታ
አንዳንድ ባለቅኔ ቢላሆን የሳለ
ሲያዩት የሚያስጎመጅ ስጋን የሰቀለ
ከቀዩ ከነጩ ከትፎ የሚበላ
ዋጋን የሰቀለ ሌላዉ እንዳይበላ
ይላል ከሱቅ ሆኖ አሻቅቧል አሻቅቧል
የሚበላዉ ስጋ ሳይሆን የሚበላዉ ስጋ መርከሱ ሳይገዉ
አሻቅቧል በማለት ሲጠራ ይዉላል
ስጋዉን የሸጠ ቸርቻሪ በሙሉ
አልታየዉ አለ የለበሰዉ ስጋ ዉዳቂ መሆኑ
ሁሉ ባለቅኔ ባለሰም ባለ ወርቅ
የራሱን የሚጥል የሰዉን የሚነጥቅ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
እግር ጫማ ረግጦ ጫማዉ መሬት ሲረግጥ
በረገጠዉ ጫማ ማደሪያዉን ሲያበጅ
ሞተ ይባላል በሙሾና ለቅሶ
ከመሞቱ በፊት በህይወት እያለ
ምን እንኳ ሳይዘራ መልካም ሚያስብል ፍሬ
ሲሞት ግን ይባላል ፍሬህን ሳታየዉ ምነዋ አካሌ
በሙት ላይ መቀኘት ሚወድ አዘብዛቢ
አልሰማሁም ይላል ነገር አራጋቢ
ከዉጉዝ ምግባሩ ተሳታፊ ሁላ
አልሰማ ብሎ ነዉ ይላል በጥቆማ
ሁሉ ባለቅኔ የሞተም የቆየ
ርእስን ያጣ ቅኔን በሆድ ይዞ
ሲሞት ዋይ ይባላል በሙሾ በለቅሶ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ብቻ ብዙ አለ የለም ካልነዉ ወዲያ
ጠቢብ ይሁን ጠባብ ያላወቅነዉ እኛ
ብቻ ብዙ አለን ምናቅ ማያዉቁንን
እነሱ የሚያቁን ማናቅ የሌላዉን
ሁሉ ባለ ቅኔ ባለሰም ባለወርቅ
የራሱን የሚጥል የሰዉን የሚነጥቅ
ሁሉ ቅኔ አለዉ መፍታት የማይችለዉ
ከማወቁ ጀርባ አንዳንድ አለማወቅ ደብቆ ያኖረዉ
ርዕስ ያጣለት ሁሌ ሚናገረዉ
ሰዉማ ቅኔ አለዉ ለሰዉ ሚናገረዉ
እንቁ ማርያም (መባ)
ብዙ ተራኪያን ብዙ ሰዉ ዜመኛ
ብዙ ሰአሊያን ብዙ ሰራተኛ
ሁሉ ባለቅኔ ባለሰም ባለወርቅ
ሁሉን ሁሉ አዋቂ ነገር አራቃቂ
ለሚሰራዉ ስራ ምክንያት ጠያቂ
ለሚገጥመዉ ግጥም ለሚቀኘዉ ቅኔ ርእስ ፈላጊ
ሁሉ ሰዉ ፈራጅ ነዉ ሁሉ ትምክተኛ
ሁሉ ተናጋሪ ሁሉም ወቃሽ ዳኛ
ሁሉ ቅኔ አለዉ እርእስ ሳይኖረዉ
ብርቱ በደካማዉ ጎበዝ በሰነፉ የሚቀባበለዉ
ከማወቁ ጀርባ አንዳንድ አለማወቅ ደብቆ የያዘዉ
ሁሉ ቅኔ አለዉ ርእስ የሌለዉ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
በረቀቀ አይምሮ ልቆ በመጠቀ
ባራሙቻ ስልጣኔ ህሊናን የሸጠ
ቅኔ አለኝ ይላል ሰም ወርቁን እያጣ
ምላስ አለዉና አፍ ስራ አይፈታ
አንዳንድ ባለቅኔ ቢላሆን የሳለ
ሲያዩት የሚያስጎመጅ ስጋን የሰቀለ
ከቀዩ ከነጩ ከትፎ የሚበላ
ዋጋን የሰቀለ ሌላዉ እንዳይበላ
ይላል ከሱቅ ሆኖ አሻቅቧል አሻቅቧል
የሚበላዉ ስጋ ሳይሆን የሚበላዉ ስጋ መርከሱ ሳይገዉ
አሻቅቧል በማለት ሲጠራ ይዉላል
ስጋዉን የሸጠ ቸርቻሪ በሙሉ
አልታየዉ አለ የለበሰዉ ስጋ ዉዳቂ መሆኑ
ሁሉ ባለቅኔ ባለሰም ባለ ወርቅ
የራሱን የሚጥል የሰዉን የሚነጥቅ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
እግር ጫማ ረግጦ ጫማዉ መሬት ሲረግጥ
በረገጠዉ ጫማ ማደሪያዉን ሲያበጅ
ሞተ ይባላል በሙሾና ለቅሶ
ከመሞቱ በፊት በህይወት እያለ
ምን እንኳ ሳይዘራ መልካም ሚያስብል ፍሬ
ሲሞት ግን ይባላል ፍሬህን ሳታየዉ ምነዋ አካሌ
በሙት ላይ መቀኘት ሚወድ አዘብዛቢ
አልሰማሁም ይላል ነገር አራጋቢ
ከዉጉዝ ምግባሩ ተሳታፊ ሁላ
አልሰማ ብሎ ነዉ ይላል በጥቆማ
ሁሉ ባለቅኔ የሞተም የቆየ
ርእስን ያጣ ቅኔን በሆድ ይዞ
ሲሞት ዋይ ይባላል በሙሾ በለቅሶ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ብቻ ብዙ አለ የለም ካልነዉ ወዲያ
ጠቢብ ይሁን ጠባብ ያላወቅነዉ እኛ
ብቻ ብዙ አለን ምናቅ ማያዉቁንን
እነሱ የሚያቁን ማናቅ የሌላዉን
ሁሉ ባለ ቅኔ ባለሰም ባለወርቅ
የራሱን የሚጥል የሰዉን የሚነጥቅ
ሁሉ ቅኔ አለዉ መፍታት የማይችለዉ
ከማወቁ ጀርባ አንዳንድ አለማወቅ ደብቆ ያኖረዉ
ርዕስ ያጣለት ሁሌ ሚናገረዉ
ሰዉማ ቅኔ አለዉ ለሰዉ ሚናገረዉ
እንቁ ማርያም (መባ)