ወላጆች ልጆቻቸውን በትምህርታቸው ስኬታማ ማድረግ የሚችሉባቸው 9 ቀላል ዘዴዎች
Easy ways for parents to support their children's studies
ክፍል 1
ባለንበት ዘመን ልጆች ማሳደግ እጅግ ፈታኝ ከሆኑት ሃላፊነቶች አንዱ ነው፡፡ “ልጄ ምርጥ ትምህርት አግኝቶ ስኬታማ መሆን እንዲችል እኔ ምን ማድረግ አለብኝ?” የሚለውም እንደወላጅ በጣም አሳሳቢና ዕረፍት የማይሰጥ ርዕሰ ጉዳይ ነው፡፡ አፋጣኝና ተገቢ ምላሽ የሚሻ:: የልጅዎትን የትምህርት ሁኔታ ሲያስቡም ልጆችን በትምህርታቸው ለመርዳት ይህ ነው የሚባል አስተዋፅኦ ማበርከት የማይችሉ ሊመስልዎት ይችላል፡፡ ሆኖም ግን ጥናቶች እንደሚነግሩን ወላጆች ልጆቻቸውን በትምህርታቸው መርዳት ወይም ሥኬታማ ማድረግ የሚችሉባቸው በርካታ ዘዴዎች መኖራቸውን እንገነዘባለን፡፡
እኛም ወላጆች ልጆቻቸውን በትምህርታቸው ሥኬታማ ማድረግ ከሚችሉባቸው ቀላል ዘዴዎች መካከል 9ኙን ለዛሬው ሳምንታዊ የግንዛቤ ማስጨበጫ መልዕክት በርዕሰ ጉዳይነት መርጠናል፡፡ በጽሑፉ ልጆችዎትን በትምህርታቸው ለመርዳት የሚያስችሉ ጠቃሚ ዕውቀቶችን እንደሚቀስሙበት እምነታችን ነው፡፡ መልካም ንባብ
1. ልጆችዎ ሲማሩ የሚቸገሩበት ስለመኖሩ ጊዜ ሰጥተው ይጠይቋቸው፡፡ ቀረብ ብለው ያወያዩዋቸው፤ የሚችሉትን ዕገዛም ያድርጉላቸው!!
ልጆችዎን በትምህርታቸው ከሚረዱበት ዘዴዎች እጅግ ቀላል የሚባለው የልጆችዎን የትምህርት እንቅስቃሴ እርስዎም ጉዳዬ ብለው እንደሚከታተሉዋቸው ማሳየት፤ የሚከብዳቸው ትምህርት ካለም እነርሱን መጠየቅ ነው፡፡ “ትምህርት እንዴት ነው? ምን ችግር ገጠመህ/ሽ? የምረዳህ/ሽ ነገር አለ?” እና መሰል ጥያቄዎችን ልጆችን ቀርቦ መጠየቅ ቀላል ግን የላቀ ፋይዳ የሚገኝበት ነው፡፡ ግን ስንቶቻችን ነን ሥራዬ ብለን ይህን የምናደርገው? ስንቶቻችን ነን ልጆቻችንን ት/ቤት ከመላክ በዘለለ እንዲህ በትምህርታቸው ተጨንቀን የምንጠይቅ? እራሳችንን እንጠይቅ! ልጆችዎ የርስዎን ዕርዳታ ሲፈልጉ ለዚህ ዝግጁ መሆንዎን ማወቃቸው በራሱ እርስዎ ለእነርሱ ትምህርት ዋጋ እንደሚሰጡ ብሎም ከጎናቸው መሆንዎን ለማሳየት ጭምር ይጠቅማል፡፡ ልጀችዎ የሚቸገሩበትን የትምህርት ርዕስ (topic) ለእርስዎ መጥተው ካሰረዱዎት በቻሉት መጠን ሳይዘገዩ ተገቢውን ምላሽ መስጠት ይገባዎታል፡፡ ልጅዎን የገጠመው/ማት የትምህርት ችግር ከአቅም በላይ ከሆነም በጉዳዩ ዙሪያ የተሻለ መርዳት የሚችሉ ባለሙያዎችን በማማከር አለያም በትምህርቱ ዙሪያ የተዘጋጁ መጽሐፍትን ገዝተው ማቅረብን እንደ መፍትሔ መጠቀም አስፈላጊ ይሆናል፡፡ ይህ ብቻም ሳይሆን ልጆችዎ ላይ የሚያስተውሉት የትምህርት ችግር እየከፋ ከሄደና ለመስተካከል ረጅም ጊዜ የሚፈልግ አይነት ከሆነ ልጅዎን በትምህርት አይነቱ (subject) ዙሪያ የግል አስጠኚ መቅጠርዎ ሌላው አማራጭ ሊሆን ይችላል፡፡ በተለይ ልጅዎ ከትምህርት ገበታ የቀረ ወይም ታሞ ከነበረ አለያም ሌላ የጤና ችግር ገጥሞት የትምህርት አቀባበሉ ላይ ጉልህ ችግር ከተፈጠረ ከት/ቤት ባሻገር ቤት መጥቶ በግል የሚረዳው የትምህርት ባለሙያ (አስጠኚ) ቀጥሮ ልጅዎ እንዲረዳ ማድረግ ተገቢ ነው የሚሆነው፡፡
2. ልጆችዎ ማንበብን የደስታ ምንጫቸው እንዲያደርጉ ያበረታቱ
ማንበብ የብዙ ስኬታማ የሆኑ ተማሪዎች አይነተኛ ባህሪ ነው፡፡ ወላጆች ይህን ተግባር ልጆች ይተገብሩት ዘንድ ማበረታታት አለባቸው፡ ይህን ማድረግ ምን ይከብዳል? ወደ ቤተ-መጻሕፍት ሲሄዱ ልጆችዎንም ይጋብዟቸው ፣ በቤትዎ በቂ መጽሐፍ እንዲኖር ያድርጉ ከተቻለም የቤት ውስጥ ቤተ-መጻሕፍት (ላይብረሪ) ይኑርዎት፤ ልጆችዎ የተሻለ የትምህርት ውጤት ካመጡም መጽሐፍ ይሸልሟቸው፤ ስጦታም ያበርክቱላቸው፡፡ እነዚህ ተግባራት በየትኛውም የዕድሜ ክልል ለሚገኙ ልጆች የንባብ ፍቅርን ለማስረፅ የሚያስችሉ ቀላል ዘዴዎች ሆነው ማገልገል ይችላሉ፡፡
3. በቤት ውስጥ የፀጥታ ጊዜ እንዲኖር ያድርጉ
በቤት ውስጥ ያሉ ህጻናትም ሆኑ ዐዋቂዎች እየተንጫጩና እየረበሹ ሌሎች ልጆች ሀሳባቸውን ሰብሰብ አድርገው በአንድ ልብ ማንበብ፣የቤት ስራቸውንም ሆነ ሌሎች በትምርት ቤት የታዘዙትን መስራት ይቸግራቸዋል፤ ሀሳባቸው ይበታተንባቸዋል፡፡ የተሰበሰበ ትኩረት ማድረግ ይሳናቸዋል፡፡ ይህን ችግር ለመቅረፍ ታዲያ በቀን ውስጥ በተወሰነ የጊዜ ገደብ ውስጥ ምንም አይነት የልጅዎትን ትኩረት የሚነሳ ጫጫታና ረብሻ የማይኖርበት የጸጥታ ጊዜ ስርዓት በቤትዎ ውስጥ ሊኖር ይገባል፡፡ ይህም ልጆች በቤት ውስጥ የሚያስፈልጋቸውን የትምህርት ተግባራት በተረጋጋና ፀጥታ የሰፈነበት (distraction-free) በሆነ ሁኔታ እንዲሰሩ ያመቻቻል፡፡
4. ከልጆችዎ ት/ቤትና መምህራን ጋር ቅርብ ይሁኑ
ት/ቤት የነገ የልጅዎ ማንነት የሚቀረፅበት ስፍራ ነውና እንደ ወላጅ የልጆችዎን ት/ቤት ጉዳዬ ብለው ሊከታተሉ ይገባል፡፡ አሁን እያነበቡ ያሉት ሳምንታዊ ግንዛቤ ማስጨበጫ መልዕክትን ጨምሮ ሌሎች በት/ቤቱ የሚዘጋጁ መልዕክቶችን (ዕለታዊ፣ወርሃዊ … ) በሚገባ ማንበብና ቦታ ሰጥተው መረዳት እንዲሁም ከልጆችዎ መምህራን ጋር በቅርብ መነጋገር ይጠበቅቦታል፡፡ ከዚህ ባሻገር በየጊዜው ስለ ልጆችዎ የትምህርት ጉዳይ ሳይታክቱ ከመምህራን ጋር በመወያየት (በመጠየቅ) ልጅዎ ምን አይነት ድጋፍ ከእርስዎ እንደሚያስፈልገው መረዳት ይጠበቅብዎታል፡፡ ከልጅዎ መምህራን ጋር ቅርርብ በመፍጠር በሚኖርም ውይይት ልጆችዎ ተጨማሪ ድጋፍ የሚፈልጉባቸው ክፍተቶችንም ይገነዘባሉ፡፡
ክፍል 2 ይቀጥላል