እናመሰግናለን!!!
ሹክረን!!!
ውድ እና የተከበራችሁ ወላጆች/አሳዳጊዎች፡-
“ሪድ አል-አፊያ” በሚል መሪ ቃል ለወራት በተሻለ እንቅስቃሴ ሲካሄድ የቆየው የ 2017 የንባብ ዘመቻ በሁሉም ካንፓሶቻችን በተለያዩ ንባብ ተኮር መርሃግብሮች በከፍተኛ ድምቀት በዚህ ሳምንት ተጠናቋል፡፡ እኛም የዚህ ሳምንት መልዕክታችን ስለንባብ እንዲሆን መርጠናል፡፡ መልካም ንባብ፡፡
በኣረብኛ አል-ኢልሙ ፊ ሲገር ከነቅሹ አለል ሃጀር ማለትም በልጅነት የሚቀሰም ዕውቀት እንደ ድንጋይ ላይ ፅሁፍ ነው ይባላል ፡፡ ንባብ ደግሞ ሁላችንም እንደምናውቀው የዕውቀት መግቢያ በር ነው፡፡ ልጆቻችን በንባብ ሲጠነክሩ የተሻለ ዕውቀት ይሰንቃሉ፤በዚህም የአስተሳሰብ አድማሳቸው እየሰፋ ይሄዳል፡፡ በዚያው መጠንም የሚኖራቸው ተቀባይነት እንዲሁም ተፅእኖ ፈጣሪነት እያደገ ይሄዳል፡፡ ለዚህም ነው ብዙውን ጊዜ አንባቢዎች መሪዎች ናቸው የሚባለው፡፡
ዓመታዊ የንባብ ዘመቻ በአል-ዓፊያ ት/ቤቶች የትምህርት ፅ/ቤት ስር በሚገኘው የእንግሊዝኛ ቋንቋ ዲፓርትመንት አማካኝነት በ2016 በይፋ የተጀመረ ሲሆን ለ2ተኛ ጊዜ በ2017ም በተሻለ ሁኔታ ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ ለማካሄድ ተሞክሯል፡፡
በተለይ በዚህ ዓመት በመንግስት ትምህርት ቢሮ በቅድመ-መደበኛ (ኬጂ) ጭምር የንባብ እንቅስቃሴው እንዲጀመር በሰርኩላር ደረጃ መውረዱ የንባብ ክህሎት ከስር ከመሰረቱ መጀመር እንደሚገባው ያረጋገጠ እንዲሁም ተቋማችን በዚህ ረገድ አንድ እርምጃ ወደፊት ቀድሞ መሄዱን ያመላከተ ልዩ ክስተት ሆኖ አልፏል፡፡
ሁላችንም ተማሪዎቻችን ማንበብ እንዲወዱ የመርዳት ፍላጎት አለን። ስለዚህ ሁላችንም ይህንን ግብ ማሳካትይኖርብናል። ይህን ከባድ ሥራ ትምህርት ቤት በአመታዊ የንባብ ዘመቻ ብቻውን ሊወጣው አይችልም። ተማሪዎች ማንበብ ለመማር የሚያደርጉትን ጥረት ማህበረሰቡ እንዲደግፍ እንፈልጋለን። ወላጆች ልጆችን እንዲያበረታቱና እንዲያግዙ እንፈልጋለን። ወላጆች ለማንበብ፣ ሞዴል ንባቦችን ለማቅረብ የሚያግዙ ተግባራትንና ቦታዎችን በማመቻቸት እንዲተባበሩ እንፈልጋለን።ወላጆች/አሳዳጊዎች ተማሪዎች ጥሩ አንባቢ እንዲሆኑ እንዲያግዙና አቅጣጫ እንዲያመላክቱ እንፈልጋለን።
በዚህ መሰረት ወላጆች/አሳዳጊዎች ልጆቻችንን ዛሬ ባሉበት ዕድሜ ክልል ይህንን መሰረታዊ የስኬት ቁልፍ የሆነ ክህሎት( ንባብ) ፍላጎት እንዲኖራቸው በማበረታት እና ሁኔታዎችን በማመቻቸት ልጆች አንባቢ ሆነው እንዲታነፁ የድርሻችንን ኃላፊነት መወጣት ከቻልን በዕርግጥም የላቀ ውለታ ውለናቸዋል፡፡ ምክንያቱም ከላይ ቀደም ብሎ እንደተጠቆመው ልጆች ብዙ ባነበቡ ቁጥር የዕውቀት አድማሳቸው እየሰፋ ይሄዳል ፡፡ ይህም በትምህርታቸው ጎበዝ ፤በስነ-ምግባራቸውም እየተመሰገኑ ሆነው እንዲታነፁ ብሎም ወደፊት ኃላፊነት የመሸከም ብቃታቸው ክፍ እንዲል በእጅጉ ያግዛቸዋል፡፡
ከናንተ ጋር በአንድ ላይ ሆነን ጠንካራ ግንኙነት በመፍጠር ልጆቻችን ስኬታማ አንባቢዎች እንዲሆኑ ማብቃት እንችላለን። በመሆኑም ልጆች ገና ናቸው ብለን ሳንዘናጋ ከወዲሁ በዕድሜያቸው ልክ የንባብ ፍላጎት ማስረፅ ይቻል ዘንድ የተጀመረው የጋራ ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥል!! እንዲሁም በዚህ ሳምንት የተጠናቀቀው በት/ቤቱ ሲካሄድ የቆየው ዓመታዊ የንባብ ዘመቻ እንጂ ንባብ አለመሆኑን ሳንታክት ለልጆቻችን እናስታውስ!! እንምከር!! እናስረዳ!!
ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል፣አንባቢዎች አሸናፊዎች ናቸው፤አሸናፊዎችም አንባቢዎች ናቸው፣የማያነብ ሰው መስኮት እንደሌለው ቤት ነው ይባላል እና እኛ እያነበብን ለልጆቻችን አርአያ በመሆን አንባቢ ትውልድ በማፍራት ልጆቻችን የዕውቀት ጉዞዋቸው የተሳካ ይሆን ዘነድ የድርሻችንን እንወጣ!!
ውድ እና የተከበራችሁ ወላጆች/አሳዳጊዎች
እናንተም “ስለልጄ የንባብ ክህሎት መዳበር የድርሻዬን እወጣለሁ” በሚል ለልጆቻችሁ የተለያዩ መፅሀፍት በመግዛት፣ሰዓት መድባችሁም በማገዝና በማበረታታት እንዲሁም ንባብን የሚያግዙ ሁኔታዎችንም በማመቻቸት ብሎም ንባብን ለማጎልበት ስንልክላችሁ የነበሩ መልዕክቶችን በሚገባ ተግባራዊ በማድረግ ከት/ቤቶቻችን እንዲሁም ከመምህራኑ ጋር በመወያየት ጭምር የንባብ አርአያ በመሆን፤ ከዚህ ባሻገር በት/ቤቶቻችን ንባብ ማጠቃለያ ፕሮግራም መድረኮች እንድትገኙ የቀረበላችሁን ጥሪ አክብራችሁ በመገኘትና ስለንባብ አስፈላጊነት ገንቢ እና አነቃቂ መልዕክቶች በማቅረብ ለንባብ ዘመቻው ስኬታማነት ላሳያችሁት ቁርጠኝነትና ቀና ትብብር ሁሉ በመላው የትቤታችን ማህበረሰብ ስም እጅግ አድርገን ከልብ እናመሰግናለን!!! ሹክረን!! በማለት የዛሬውን ሳምንታዊ መልዕክታችንን እንቋጫለን፡፡