ልጆች ከካርድ ውጤት በላይ ናቸው
ውድ እና ተከበራችሁ ወላጆች/አሳዳጊዎች፡-
ተማሪዎች ከዚህ ሳምንት ጀምሮ የመጀመሪያው መንፈቀ-ዓመት ( ሴሚስተር) ውጤት ይቀበላሉ፡፡ እኛም የዛሬው ሳምንታዊ መልዕክታችን ከዚሁ ጋር በተያያዘ ከማህበራዊ ሚዲያ ያገኘነውን ወቅታዊ እና ጠቃሚ መረጃ እንዲሆን መርጠናል፡፡ መልካም ንባብ፡፡
እንደ ሰኔ 30 ባይሆንም የግማሽ ሴሚስተር ውጤትም ውጥረቶች አሉት፡፡ በልጆች ማንነት እና ልጆች አጥንተው በሚያገኙት ውጤት መካከል ሰፊ ልዩነት አለ፡፡
በአሪዞና ስቴት ዩኒቨርስቲ የተካሄደ ጥናት ወላጆች ይበልጥ ትኩረት የሚሰጡት ለልጆቻቸው ነው ወይንስ ለልጆቻቸው የፈተና ውጤት የሚለውን መፈተሸ ነበር፡፡
የጥናቱ ግኝት ለልጆቻቸው ትኩረት ከመስጠት ይልቅ አጥንተው ለሚያገኙት የትምህርት ውጤት ይበልጥ ትኩረት የሰጡ ወላጆች በልጆቻቸው ሊያዩ የጓጉትን ሳያገኙ ቀሩ፤ ልጆቻቸው ያስመዘገቡት ውጤት አነስተኛ ሆኖ ተገኘ፡፡
ልጆች አጥጋቢ ውጤት እንዲያመጡ ማበረታታት መልካም ሆኖ ሳለ የልጅን መሰረታዊ ፍላጎት ( መወደድ፣ መደመጥ፣ ትኩረት ማግኘት፣ የጋራ ጊዜ …) ችላ ተብሎ ለፈተና ውጤት ይበልጥ ትኩረት መስጠት ሚዛናዊነት ይጎድለዋል፡፡
ምክረ ሃሳብ
1. ልጅ ከፍተኛም ሆነ ዝቅተኛ የትምህርት ውጤት ቢያመጣ ከካርድ ውጤት በላይ ነው፡፡ ወላጅ ለልጁ አስተማማኝ ደህንነት እንዲሰማው ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡
2. የካርድ ውጤት ዝቅተኝነት የወላጅ ፍቅርን ሊያሳጣ አይገባም፡፡ ውጤት ሊለዋወጥ ይችላል፤ የወላጅ ፍቅር ግን ከሁኔታ ሊያልፍ ይመከራል፡፡
3. የልጅን ድክመት ማገዝ፤ ሙከራዎችን ማበረታታት ያስፈልጋል።
4. ያለ ዓላማና ያለአቅም ወደዚህ ምድር የመጣ ልጅ የለም፡፡
ስለዚህ ውድ እና የተከበራችሁ ወላጆች/አሳዳጊዎች ልጆች ምንም ዓይነት ውጤት ቢያስመዘግቡም ለራሳቸው ያላቸውን ክብርና በራስ መተማመን አንውሰድባቸው፤ እንደምንወዳቸውና ከጎናቸው እንደሆንን እናረጋግጥላቸው። ይህ የልጆችን አለም ይቀይራል።
ምንጭ፡- BBA