مدرسة نور الهدى dan repost
♦የነቢያችንን (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሲራ መማር የዲናችንን መሰረትና ውበት አላህ ለሳቸው የቸረውን ታላቅነት ለዲናቸው የለገሱትን መስዋእትነትና ታላቅ ሰብራቸውን ያሳያል።
🔹ሲራቸውን ትኩረት ሰጥቶ የተከታተለ ሰው ያንን እልህ አስጨራሽ ጉዞ በድል የጨረሱት በውስጣዊ ጠንካራ ዓቂዳ መሆኑን ይደርስበትና በቁርአንና በሀዲስ ትክክለኛ ዓቂዳ ውስጡን ይገነባል።
🔹በትክክል የሳቸውን መስመር ተከትሎ በዳዕዋው ውጤታማ መሆን የፈለገ ዳዒያህ ሲራቸውን አዘውትሮ ሊያጤን ይገባል።
🔹የሳቸውን ሲራ የተረዳ ሙስሊም ዲነል ኢስላም የተሟላ ከመሆኑም በላይ ሁሉንም የዲን ተግባር መፈፀም ቀላል እንዳልሆነ ስለሚገነዘብ ከቢድዓ እጅጉን ይርቃል።
🔹የሳቸውን ሲራ ወደ ህይወቱ ለማምጣት የሚጥር ግለሰብ ልቡ በኢማንና በሂክማ የተሞላ፣ በዒባዳ የማይሰለች ትጉህ፣ ለአላህ በሚያቀርበው ዒባዳ ልዩ እርጋታና እርካታ የሚያጥጥም ሙእሚን ይሆናል።
🔹የእኚህን ታላቅ ስብእና ሲራ የተማረ በስነምግባር አቻ የሌለው የምርጥ አኽላቅ ካባ ይላበሳል።
🔹ሲረቱ ረሱልን (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የተከተለ በማህበራዊ አኗኗሩ ስኬታማ፣ ትዳሩ የሰመረ፣ ልጆቹ የቀኑ፣ ጉዳዮቹ ሁሉ የተሳኩ ሲሆኑለት ለሚያጋጥመው ማንኛውም የህይወት ፈተና በድል የሚወጣባቸው የመፍትሄ ቀዳዳዎች ጎልተው ይታዩታል።
🔹በጥቅሉ የነቢያችንን ( ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ሲራ ላጤነውና ለተገበረው ሰው በሁለቱም ዓለም የበላይነትን ያጎናፅፋል።
♦ ولهذا أنصح نفسي وإخواني أن يعنوا بسيرة سيد الخلق أجمعين عليه من الله أفضل الصلاة وأزكى التسليم