#አንደራደርም
#አትደራደሩ
{ይነበብ፦ሮሜ 8÷28-39}
ሁላችንም በህይወታችን የምንደራደርባቸው አልያም ደግሞ ከሚገጥመን ሁኔታ አንፃር አቋማችንን/ውሳኔያችንን የምንቀይርባቸው ብዙ ነገሮች አሉን።ነገር ግን በምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ ብናልፍ አቋማችንን የማንቀይርበት ወይም የማንደራደርበት አንድ ነገር አለ ይህም ከአምላካችን እግዚአብሔር እንዲሁ በነፃ የተቀበልነው የዘላለም ህይወት ስጦታ ነው።ይህን ስጦታ የተቀበልነው በነፃ ቢሆንም ዋጋው ግን እጅግ ውድ ነው ምክንያቱም በጌታችን ኢየሱስ ክርሰቶስ የመስቀል ስቃይ የተገኘ ነውና።ስለዚህ ይህ ታላቅ ስጦታ ሊቀልብን አይገባም።እንደ ሙሴ ምቾትን ትተን ብንሰደድ፣እንደ አብርሃም የፀሎት መልሳችን ቢዘገይ፣እንደ ይስሐቅ ሰዎች ቢገፉን፣እንደ ዮሴፍ የቅርብ በምንላቸው ሰዎች ብንገፋ፣እንደ ኢዮብ ብንታመም፣እንደ ዳንኤል በአንበሳ ጉድጓድ ውስጥ ብንጣል፣እንደነ ሲድራቅ ሚሳቅና አብደናጎ በእቶን እሳት ውስጥ ብንጣል፣እንደ ዲያቆን እስጢፋኖስ በድንጋይ ብንወገር፣እንደ ሐዋሪያቱ ብንገረፍና ብንታሰር፣ልጆቻችን ቢታመሙ፣በጣም የምንወዳቸው ሰዎች በሞት ቢለዩን፣ቢርበን፣በማጣት ውስጥ ብናልፍ፣ነገሮች/ሁኔታዎች እንዳሰብነው ባይሆኑልን፣በአጠቃላይ ብዙ መከራና ችግር ውስጥ ብናልፍ ባገኘነው የዘላለም ህይወት አንደራደርም።እኚህ ከላይ የተዘረዘሩት ነገሮች በሙሉ ከጌታ እቅፍ ወጥተን ወደ ኋላ እንድናፈገፍግ(ልባችን እንዲሸፍት) ምክንያት ሊሆኑን አይገባም።በዚህ ሁሉ ግን ሐዋሪያው ጳውሎስ እንደተናገረው(2ተሰ 3÷3) በእምነታችን የሚያጸናን ከክፉውም የሚጠብቀን ጌታ የታመነ ነው።አሜን!✍ #Kirubel
@Amen_Maranata
@Amen_Maranata
@Amen_Maranata
❇️Join and Share❇️