13 ታጋቾች እንዲለቀቁ ተደረገ።
13 ታጋቾችን ከእገታ ማስለቀቁን የጭልጋ ወረዳ ሰላም እና ደህንነት ጽሐፈት ቤት አስታውቋል።
መነሻውን አዘዞ አድርጎ ወደ መተማ እየሄደ ባለ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ተሳፍረው ከነበሩት ተሳፋሪዎች 13ቱ ታግተው እንደነበር ተገልጿል።
የጭልጋ ወረዳ ሰላም እና ጸጥታ ጽሕፈት ቤት ምክትል ኀላፊ መላኩ አብዬ የጭልጋ ወረዳ የጸጥታ ኃይል በደረሰው መረጃ ወደ ቦታው በመግባት ባደረገው የተኩስ ልውውጥ 13ቱን ታጋቾች ማስለቀቁን ተናግረዋል።
መንገድ ላይ እየተደረገ ያለው እገታ ማኅበረሰባችን ጉዳት ላይ የሚጥል ነው ያሉት ምክትል ኀላፊው ማኅበረሰቡ መረጃ በመስጠት ከጸጥታ ኀይሉ ጋር እንዲሠራ አሳስበዋል።
የጭልጋ ወረዳ ሚሊሻ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ጋሻው ብርሀኔ እገታ የማኅበረሰቡን ኢኮኖሚ ከመጉዳት ባሻገር በሥነ ልቡና ላይም ትልቅ ተፅእኖ እንደሚያሳድር ተናግረዋል።
ሁሉም የማኅበረሰብ ክፍል የእገታ ተግባርን በማውገዝ እና መረጃ በመስጠት ከጸጥታ መዋቅሩ ጎን እንዲሰለፍ ጠይቀዋል።
ከማዕከላዊ ጎንደር ዞን ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ከእገታ የተለቀቁ ወገኖች በሕይወታቸው ለደረሰላቸው የወረዳው የጸጥታ ኀይል ምስጋና አቅርበዋል።
እገታን ሁሉም ማኅበረሰብ ሊያወግዘው እና ሊከላከለው የሚገባ ተግባር መኾኑንም ተናግረዋል።