🔥🔥"የሚያየኝን ፊት ለፊት አየሁት"(የራሽያ ወጣት ኮሚኒስት) 😱🔥
ክፍል :9
✍️...........እስዋ ስትወድቅ አጠገቡ የነበረው ሌላ ወታደር በያዘው መሳሪያ ግንባሩን በጣጠሰው፣ደሙ በዛ ነጭ በረዶ ላይ ሲፈስ ታዋቂ አርቲስት የሳለው ውብ አበባ አስመስለው። ቀጠለና መሳርያውን ወደ ኮሚኒስቶች በመመለስ ሌላስ በነዚህ እስረኞች ላይ ተኩሶ ሊገድል የሚደፍር ሰው ካለ ይንገረኝ በማለት አነጣጠረባቸው።መልስ ሲያጣ ከመኪነው በመውረድ መሳርያውን ወደ ሰማይ ያንጣጣው ጀመር።ጓደኞቹ አንድ ላይ "ፓዳዥዴ ቲሆንቺኩ "(ተረጋጋ ቀስ በል)ማንኛችንም ብንሆን አንገድላቸውም፥አንተ እንዳልክ እናደርጋለን፤መሳርያህን ጣለው በማለት ይጭዋጭዋሁ ጀመር። እሱ ግን በእጁ የያዘውን ጥይት እስኪያልቅ ድረስ እንደእብድ ሆኖ ይተኩስ ነበር። በመጨረሻ እንደሰከረ ሰው ይንገዳገድ ስለነበር ከአሁን አሁን ሁላችንን ፈጀን ጨረሰን ብለን ሰጋን።ከድቦች ጥርስ ያዳነን አምላክ ከሰው ጥይት ሊያድነን እንደሚችል ተጠራጠርነው። በመጨረሻም ያ ሰው ወደ እኛ ዘወር ብሎ በመጠጋት ""ማሩኝ ይቅር በሉኝ የእንጀራ ጉዳይ ሆኖብኝ ነው። አሁን ግን እኔ እንደእናንተ ውብ እናት እህት እና ከልቤ የማትጠፋ እጮኛ አለችኝ። ቤተሰቦቼ እንደእናንተ በሰማይ በዚህ በሚታየው ጋላክሲ ሰማያዊ ጠፈር ባሻገር #አገር አለ ምድር አለ ብለው የሚያምኑ ናቸው።እኔ ወደዚ ከተማ ወደማይታየው በአየር ላይ ሀገር አለ ወደምትሉት ሰው እና የፓርቲያችሁ መሪ ወይም ንጉስ አስተዋውቁኝ እና ማህበርተኛ ልሁን፣አባል ለመሆን እፈልጋለሁ ፣የሚከፈል ነገር ካለ አዋጣለው። ከአንድ ፓርቲ ወደ ሌላ ፓርቲ መቀየር አዲስ ሀሳብ (አይዶሎጂ)ታገኛለህ የማለው አባባል ለመቀበል ተገድጃለሁ። ከዚህ ቀደም ቤተሰቦቼ ስለዚህ ጉዳይ ሲተርኩልኝ በጣም ትንሽ ህፃን ሆኜ እሰማ ነበር። ያ አፈ ታሪክ ከደመናት ከጠፈር ባሻገር አገር አለ ያሉትን አፈታሪክ በገሀድ አይቼዋለሁ።ከሀይለኛ ድቦች ጥርስ ንጥቂያ ያዳናችሁ መሪያችሁን እከተላለሁ፤እኔም የእናንተ ማህበርተኛ የፓርቲያችሁ አባል መሆን ወስኛለሁ """ብሎ እየተንቀጠቀጠ እና እያለቀሰ የለበሰውን ጃኬት አውልቆ ለአንዳችን ሰጠን።ሸሚዙን አውልቆ ለሌላዋ ሰጣት።ካኔቴራ እና ሱሪውን አውልቆ አከፋፍሎ ጨረሰ።በጥይት የተመታችዋን እህታችንን እያቀፈ የፈሰሰው ደሟን እየጠረገ ለጓደኞቹ ይማፀን ጀመር ካላችሁ የልብስ መአት አንድ አውጡና ስጧቸው። ባዶ ሰውነት እራቁት ገላ ማየት ህሊናችሁ አይወቅሳችሁም።እህት የላችሁም ወይም አፍቃሪ የላችሁም ፣ይህ ሁሉ ባይሆን ቢያንስ እናት የሌለው ሰው የለም። እዘኑላቸው ለአመታት አሰቃየናቸው፤ዛሬ ግን እንራራላቸው ይል ጀመር።እኛም በሚሆነው እየተገረምን በመሀከላችን አስገብተን ከከበብነው በኋላ ስለ እርሱ መፀለይ ጀመርን። ጌታ ስለእርሱ ባደረገው በጎነት እያመሰገንን ሳለን ሌሎች ኮሚኒስቶች ጌታ ከድቦች ሲያድነን ያላዩ ወታደሮች በሁለት ትላልቅ መኪና መጥተው ምንድነው? እንዴት ነው? ሳይሉ እያዳፉ እየረገጡ እየገረፉ በጥፊ በካልቾ እየወለወሉን ጭነው ወደ እስር ቤታችን ወሰዱን። ማጎርያ ቤታችን ስንደርስ በእጃችን በእግራችን በፀጉራችን ባገኙት አካላችን እየጎተቱ አወረዱን።ያ በጎነት ያደረገልን ወንድም ማንነቱ ሳይለዩ አብሮኖና ባዶ ያለ ልብስ ሲያዩ እየቀጠቀጡ አስገቡት።በዚህ መሀል የሰጠንን ልብስ ሰጥተነው እራሱን እንዲልጥ ብንለምነውም ከእናንተ አልለይም ብሎ እምቢ አለ።ጌታን መርክረንለት የጌታን ፍቅር ገለፅንለት እና በብዙ እምባ ጌታን ተቀበለ። ይህ በድንገት ባገኘነው ቅዱስ ሰው በብዙ ነገር ይረዳን ጀመር። ይህ በእንዲህ እያለ ለሊት ወታደሮች መጥተው ምን እንደሰሙ አናውቅም ብቻ ወንድማችን የሰጠንን ልብስ ነጥቀው ወሰዱብን። ጌታ ለዚህ ወንድም ሰርቶ የማይደክም ጉልበት ሰጠሰቶት ስለነበር ሁላችንንም በቁፋሮ በከባድ ስራ ያግዘን ነበር።አንድ ጊዜ ከዚ ቀደም ያገኘናት የመፅሐፍ ቅዱስ ጥቅስ አንስተን ስናነብ አይቶ ጠየቀን። የመፅሐፍ ቅዱስ ቃል መሆኑን ስንነግረው ብድግ ብሎ በዛ ለሊት ወጣና ሔደ።ሁላችንም ተደናገጥን። ምክንያቱም አማኝ መስሎ ልባችንን ከሰለለን የምናደርገውን ካየ በኋላ ነግሮ መከራችንን እንዳያብስብን ተጠራጠርን። ከአንድ ሰዐት በኋላ በፍርሀት እና በድንጋጤ ሆነን ሳለን ያ ወንድም በብዙ ላብ ተጠምቆ እያለከለከ በእጁ አራት መፅሀፍ ቅዱስ ሙሉ ያልተቀደደ ይዞልን መጣ።ማመን አቃተን፤ ሁላችንም የጌታ ቃል የሆነውን በብዙ እምባ እና ናፍቆት የምንጠማውን እንደ እንጀራ የምንራበውን ያን ቅዱስ መፅሐፍ ስናይ ሁላችንም ተነስተን የመንጠቅ ያህል ተቀበልነው። ትኩስ እሬሳ የወጣበት ቤት እሰኪ ይመስል አለቀስን። ሁኔታችንን ያየ ያ ሰው ፊቱ ላይ መደናገጥን ጭንቀትን ተሞልቶ ምን ሆናችሁ? ይህን መፅሀፍ አትወዱትምን? ይህኮ እንድናቃጥለው ብለን የሰበሰብነው መፅሐፍ ነው፣ቦታውን ስለማውቀው እኮ ነው ያመጣሁላችሁ፤የማትፈልጉት ከሆነ ልመልሰው በማለት ድንጋጤ በሞላው ፊት ይጠይቀን ጀመር።መከራ መቀበላችን ስቃያችን ለክርስቶስ እና ለዚህ ታላቅ ቃል መሆኑን ስንነግረው ተደነቀ።ይቀጥላል.......
🔥🔥ይቀጥላል የቀሩትን ገፅ ለማግኘት join ይበሉ።🔥🔥
🔥🔥 @amharicbsh 🔥🔥
🔥🔥join👆👆👆👆🔥🔥