(አበበች ጎበና )
አበበች ጎበና፣ የእኔ ባለዝና
የእናቴ ምትክ ፣ የኑሮዬ ፋና
የሚስጥር አውድማ ፣ ገመና ከታቼ
አቅፈሽ ያሳደግሽኝ ፣ ብቸኛ አጫዋቼ
በእሳት ዙሪያ ሆነሽ፣ ተረት ያወራሽኝ
ከብራና ዓለም ፣ ፊደል ያስቆጠርሽኝ
መንፈሰ ብርቱ ፣ ትሁት አገልጋይ
በመከራ ግዜ ፣ እንጀራ አቀባይ
በሄድሽበት ሁሉ ፣ ለእኔ እንደለፋሽ
አንድ ቀን ሳያምርብሽ፣ ይኸው ተደፋሽ
አንቺ ነበርሽ፣ የእኔ መገለጫ
የኑሮዬ ቅመም ፣ የሕይወቴ ማጣፈጫ
ሆዴም ተከፋ፣ መረረ ሀዘኔ
አወየው ዘንድሮ ፣ ተበላሸ ቀኔ
እንባዬም ሳይቀር፣ ከፊቴ ፈሰሰ
የሚያብሰው አጥቶ፣ እራሱን ወቀሰ
እንግዲህ ፈጣሪ፣ ነፍስሽን ይማረው
ከጀግኖቹ ጋራ ፣ በገነት ያኑረው። 😭😭😭
✍️ ቤዚቾ
የጥበብ ልሳን!
@ArtGosa
@ArtGosa
አበበች ጎበና፣ የእኔ ባለዝና
የእናቴ ምትክ ፣ የኑሮዬ ፋና
የሚስጥር አውድማ ፣ ገመና ከታቼ
አቅፈሽ ያሳደግሽኝ ፣ ብቸኛ አጫዋቼ
በእሳት ዙሪያ ሆነሽ፣ ተረት ያወራሽኝ
ከብራና ዓለም ፣ ፊደል ያስቆጠርሽኝ
መንፈሰ ብርቱ ፣ ትሁት አገልጋይ
በመከራ ግዜ ፣ እንጀራ አቀባይ
በሄድሽበት ሁሉ ፣ ለእኔ እንደለፋሽ
አንድ ቀን ሳያምርብሽ፣ ይኸው ተደፋሽ
አንቺ ነበርሽ፣ የእኔ መገለጫ
የኑሮዬ ቅመም ፣ የሕይወቴ ማጣፈጫ
ሆዴም ተከፋ፣ መረረ ሀዘኔ
አወየው ዘንድሮ ፣ ተበላሸ ቀኔ
እንባዬም ሳይቀር፣ ከፊቴ ፈሰሰ
የሚያብሰው አጥቶ፣ እራሱን ወቀሰ
እንግዲህ ፈጣሪ፣ ነፍስሽን ይማረው
ከጀግኖቹ ጋራ ፣ በገነት ያኑረው። 😭😭😭
✍️ ቤዚቾ
የጥበብ ልሳን!
@ArtGosa
@ArtGosa