አስኳላ-💚💛❤️ dan repost
.እውነት
አንድ ቀን እውነትና ውሸት ይገናኛሉ። ውሸት ለእውነት ''ዛሬ አስደናቂ ቀን ነው'' ትላታለች። እውነት ወደ ሰማይ ቀና ብላ ትመለከትና እውነትም እጅግ ውብ መሆኑን ታስተውላለች። ከዚያም ቀኑን ሙሉ አብረው ያሳልፉና በመጨረሻም አንድ የውሀ ጉድጓድ ላይ ይደርሳሉ። ውሸት እውነትን በድጋሚ ''ውሀው በጣም ጥሩ ነው፣ አብረን እንታጠብ'' ትላታለች። እውነትም የጉድጓዱን ውሀ ባየች ጊዜ ጥሩ መሆኑን ተገነዘበች። በዚህም፣ እውነት የአብረን እንታጠብ ግብዣውን ተቀብላ ልብሳቸውን ከጉድጓዱ ዳር አስቀምጠው መታጠብ ይጀምራሉ።
መታጠብያ ጉድጉዋድ ውስጥ እያሉ ውሸት ከውሀው በድንገት ትወጣለች ፣ የእውነትንም ልብስ ትለብስና ትሸሻለች። በሁኔታው በጣም የከፋት እውነት ከጉድጓዱ ትወጣና ውሸትን ለማግኘት እናም ልብሷን ለመቀበል በየቦታው ትሯሯጣለች። በየመንገዱ የምታገኛቸው ሰዎች እውነትን እርቃኗን በማየታቸው በንቀትና በንዴት ይመለከቷታል። ውሸትን ሮጣ መያዝ ያልቻለችው ምስኪኗ እውነት ወደ ጉድጓዱ ተመልሳ የውሀው ጉድጓድ ውስጥ በመደበቅ ለዓለም ስትል እርቃኗን ለዘላለም ተሸፍናለች። እነሆ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ውሸት እንደ እውነት ለብሶ በአለም ዙሪያ በመዘዋወር የህብረተሰቡን ፍላጎት በማርካት ላይ ይገኛል።
ዓለምም እውነትን የመፈለግ በጭራሽ ፍላጎት የለውምና የእውነት ለዘላለም ከጉድጓድ ውስጥ መቅረት አያስጨንቀውም። ዓለም፣ እውነት እርቃኗን ስትሆን የሚሸከምበት ሞራሉም ስለሌለው በመደበቋ ደስተኛ ነው።
👉👉Telegram channels 👇👇
➱ https://t.me/Asresee 🌹🌹