🔺ኡዝር ቢል ጀህል #ክፍል36
~~~~~~~~~~~
አልዑዝሩ ቢልጀህል የተገነባባቸው #መሰረቶች (አል ኡሱል) #ክፍል1
~~~~~
ዑለሞች ያስቀመጧቸው መሰረታዊ መስፈርቶችን ለመረመረ ግለሠብ አንድ ግለሠብ ለኃላፊነት የደረሰ ግለሠብ
ባለማወቅ ለሚሰራው ስህተት ባለማወቁ ምክኒያት ይቅርታ ይደረግለታል እንዲሁም ሊሳሳት የቻለባቸው ምክኒያቶች
ጥፋተኛ ከመሆን ያቅቡታል የሚለው መሰረታዊ መስፈርት በሁሉም የዲኑ ጉዳዮች ላይ እንደሆነ ግልጽ በሆነ ሁኔታ
እንዳስቀመጡ ይርረዳል !!
√ ጠቅለል ባለ መልኩ ይህን ጉዳይ ስንመለከተው አልዑዝሩ ቢልጀህል የተገነባባቸው መሰረቶች
#በሁለት ሁለንተናዊ
መሰረቶች ( አልአስለይኒ አልኩልሊየይኒ) ላይ መሰረት ያደረገ እንደሆነ እንረዳለን፡
📌 لا تكليف على العباد الا بالشرع المنزل
① ከአላህ በተወረደ ሸሪዓዊ ማስረጃ ብቻ ነው ኃላፊነትን መሸከም ግዳጅ የሚሆነው የሚለው መሠረታዊ ሸርጥ ወይም
መስፈርት የመጀመሪያው ሲሆን
📌 ان الشرع المنزل لا يلزم الجاهل به
② ሸሪዓዊ ማስረጃዎች ደግሞ አላዋቂ የሆኑ ግለሰቦችን (ጃሂሎችን)ተጠያቂ እንዲሆኑ አያደርጋቸውም የሚለው
መሠረታዊ ሸርጥ ደግሞ ሁለተኛው ነው !!
በመሆኑም እንዚህን ጉዳዮች በመዘርዘር መመልከት አስፈላጊ ስለሆነ እንደሚከተለው እናያቸዋለን !!
👉① ከአላህ በተወረደ ሸሪዓዊ ማስረጃ ብቻ ነው ኃላፊነትን መሸከም ግዳጅ የሚሆነው
√ ቁርአንና ሱንና እንደዚሁም ሰላማዊው የሰው ልጅ አእምሮ እንደሚያረጋግጥልን አብዛኛውም ዑለሞች
የሚስማሙበት ትክክለኛ አቋም የሰው ልጆች በሚሰሩት ተግባር ላይ በሚናገሩትም ነገሮች ኃላፊነት የሚጣልባቸው ፤
ማድረግ ያለባቸውና ማድረግ የሌለባቸው ሁልተናዊው የእምነት ስርአትና ድንጋጌ የሚደነገገው ከአላህ በወረደ ሸሪዓዊ
ማስረጃ ብቻ እንደሆነ ነው !!
የተለያዩ ሊቃውንት በእምነት ስርአት ውስጥ ስላሉ የድንጋጌ ደረጃዎች ፡ አንድ ተግባር ወይም ንግግር ያለው ብያኔ
ግዴታ ነው? (ዋጂብ ነው? ) ፣ እርም የሆነ ነው? (ሐራም? ) ፣ ቢደረግ ተመራጭ ነው? (መንዱብ? )፣ የተጠላ ነው?
(መክሩህ ?) ፣፣ፍቁድ ነው? (ሐላል? ) የሚለውን ጉዳይ ለይቶ ለመወሰን አእምሮ ድርሻ አለውን ?! በሚለው መሰረታዊ
ሀሳብ ላይ የተለያዩ አቋሞች እንዳላቸው እንመለከታለን !! በተጨማሪም የነገሮችን መጥፎነት(አስቀያሚነት)ና መልካምነት(ቆንጆነት) በአእምሮ ነው የሚለየው ወይንስ አላህ
ባወረደው ሸሪዓዊ መመሪያ ?! በሚለውም መሠረታዊ ጉዳይ ልክ እንደመጀመሪያው የተለያየ አቋም ይዘዋል !!
ከነዚህ ሁለት ሃሳቦች ላይ መሰረታዊ መመሪያ አቋማቸውን ሲመሰርቱ የቅጣትና የምንዳ ጉዳይም በአእምሮ ነው
የሚወሰነው የሚል አመለካከትን ያራመዱ ጎራዎች ተፈጥረዋል !! እነዚህን ሊቃውንት በሶስተ ከፍለን እንደሚከተለው እንመለከታቸዋለን :
👉 #አንደኛው_አቋም
አእምሮ ወይንም ዐቅል አንድ ተግባር መልካም ተግባር አልያም መጥፎ ስራ ፣ ውጉዝ የሆነ ተግባር ነው አልያም የተቀደሰ
የሚለውን ነገር ለይቶ አያስረዳንም ፤ እንዲያውም አንድ ተግባር ሸሪዐዊ መመሪያ ሳይመጣ በፊት የተቀደሰ አልያም
የተወገዘ አይባልም ። ውጉዝ (መዝሙም ) አልያም ደግሞ ቅዱስ (መምዱሕ ) የሚል ስያሜ እራሱ አይሰጠውም
የሚሉት የመጀመሪያዎቹ ጎራዎች ሲሆኑ እነዚህ ጎራዎች የአሻዒራ ጎራዎች ናቸው ።
(📚ኒቃሽ አልኡሱል ፤ አልቀራፊ ፥
1/351)
👉 #ሁለተኛው_አቋም
ነገሮችን የተቀደሱ አልያም የተወገዙ በማለት የሚለየው አእምሮ ወይንም ዐቅል ነው የሚሉት ጎራዎች ሁለተኞቹ
ናቸው ። እነዚህ ጎራዎች እንደሚያራምዱት አቋም ዐቅል ነው ሁሉንም ነገሮችን ሐላል ፣ ሐራም ፤ መክሩህ
፣መንዱብበማለት የሚለየው የሸሪዓዊ መመሪያ በዚህ ውስጥ ምንም ቦታ የለውም እንደነዚህ ዓይነት ስያሜዎችን
የሚመዝነውና የሚያጸድቀው አእምሮ ብቻ ነው ይላሉ!! የሰውን መቅቀጣት አለመቅቀጣት የሚወስነውም ዐቅል ነው
ይላሉ ።
ይህን አቋም አብዛኛዎቹ የሙዕተዚላ አቋም አራማጆችና ማቱሪዲያዎች የሚመሩበት መሰረታቸው ነው !!
📚ደርኡል ቀውሉል ቀቢሕ ፤አጥጡፊ፥82 )
👉 #ሶስተኛው_አቋም
አእምሮ ወይንም ዐቅል መልካምን አልያም መጥፎን ተግባር መለየት ያስችለናል ። ዉጉዝ የሆነን ተግባር ይህ ውጉዝ
ነው በማለት መለየት ይችላል ቅዱስ የሆነንም ተግባር ይህ ተግባር ቅዱስ ነው ማለትን ከሸሪዐዊው ብያኔ በፊት መለየት
ይችላል ። ይህን የመለየት ብቃት ተሰጠው ማለት ግን አንድን ተግባር ሐላል ፣ ሐራም ፣ መክሩህ ፣መንዱብ ፣ የሚሉትን
ሸሪዓዊ ድንጋጌዎች ያለ ሸሪዓዊ መመሪያ በራሱ ለይቶ ይወስናል የሚለውን ሥልጣን አያስሰጠውም ። በሌላ አገላለጽ
ያለ ሸሪዓዊ መመሪያ ተግባሮችን ይህ ፍቁድ ነው !! ይሄኛው ክልክል ነው ፣ ይህ የተጠላ ነው ፣ ያኛው ቢተገበር ተመራጭ
ነው ለማለት ሸሪዐዊ መመሪያ እንጂ አእምሮ የውሳኔ ድርሻ የለውም !! የሚሉ ጎራዎች ሶስተኞቹ ሲሆኑ በዚህ አቋም
ላይ በአጠቃላይ ሰሃቦችና እና የነርሱን መንገድ በመልካም አርአያነት የተከተሉ ሁሉ የሚራመዱበት አቋም ነው ።
ሁሉም ጎራዎች አቋማቸውን የሚደግፉላቸውን ማስረጃዎች በመጥቀስ አቋማቸውን ለማጠናከር ሞክረዋል !! በዚህ
ቦታ ይህን ጉዳይ በማንሳት መዘርዘር አላማችን አይደለም ። ዋናው ዓላማችን ከላይ እንደገለጽነው ሁሉ ማንም ግለሠብ
ከአላህ በወረደ ሸሪዓዊ ማስረጃ ብቻ ነው ኃላፊነትን መሸከም ግዳጅ የሚሆንበት የሚለውን መሠረታዊ ሸርጥ ወይም
መስፈርት ለመመልከት ነው ።
የሰለፎች ሚዛናዊ
አካሄድ እንደሚያሳየን እንዲሁም የተወሰኑት የአሻዒራ ጭፍሮች እንደሚያምኑት ከአላህ በወረደ ሸሪዓዊ ማስረጃ ብቻ
ነው ኃላፊነትን መሸከም ግዳጅ የሚሆነው !! በአእምሮ ፣ በፊጥራ ወይም በንጹህ የተፈጥሮ ማንነት ፣ በተወሰኑ ግለሰቦች ጣዕምንና ለዛን የመለየት ክሕሎት ፣ እና መሰል የመለያ ዘዴዎች ማንኛውም ግለሠብ ስለሚተገብራቸው
ጉዳዮች ብያኔ (ሑከም ) ሊብበጅለት አይችልም !!
ይህን እውነታ በማስመልከት ሸይኩል ኢስላም ኢብኑ ተይሚየህ ረሒመሁሏሁ ተዓላ ሲገልጹ እንዲህ ይላሉ ፡
(( በመጨረሻው ዓለም የሚያስጠይቁ ግዳጅ የሆኑ ተግባሮች እንዲሁም ለመልካም ተግባርም ይሁን ለመጥፎ ተግባር
የሚሰጥ ምንዳ ያለሸሪዓዊ ድንጋጌ ፈጽሞ ተግባራዊ አይሆንም ))
(📚ደርኡትተዓሩድ ፤ ኢብን ተይሚየህ ፥ 8/14)
(በመሆኑም በአላህና በመልክተኛው የሚያምኑ ምእመናን የእምነት ሥርዓታቸው ውስጥ የሚገኙት አምስቱ
የድንጋጌ መበይኖች (1) ግዴታ የሆነ (2) የተወደደ (3) የተፈቀደ (4) እርም የሆነና (5) የተጠላ የሚሉት ብያኔዎች
ከአላህ መልክተኛ እንጂ ከማንም አይወሰድም ። አላህና መልክተኛው ዋጅብ ወይም ግዴታ ካደረጉት ውጭ ግዴታ የሆነ
ድንጋጌ የለም ፣ አላህና መልክተኛው ሐራም ወይም እርም ካደረጉት ውጭ ግዴታ የሆነ ድንጋጌ የለም!!))
(📚መጅሙዐልፈታዋ ፤ ኢብን ተይሚየህ ፥ 22/226 )