ቤተ ያሬድ


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Ta’lim


የአብነት ትምህርት ለመማር
@lealem16 (+251934104451) ያናግሩን።

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


👉ካልዕ ቅኔ በእንተ ትንሣኤ
ከሊ/ጉ አባ ገብረማርያም

ከዋኔምንትኑመ ኖኅ መቃብረ መስፍን ኢያሱ
እስመኖኅ መቃብረሙሴ ተዐርቀ እምልብሱ

👉ዘአምላኪየ

አማኑኤል ሊቅ ለአርዳዒሁ ይብሎሙ
ሐዲሰ መጽሐፈ ትንሳኤ ጸሐፍኩ ለክሙ
ወአንብቡ ዘንተ ወትርጓሜሁ ቀዲሙ

👉ሚበዝሁ

መድኃኔዓለም በግዕ እምድኅረ ተጠብሐ እንከ
ወድኅረ ሐልቀ ሥጋሁ
ኮነነ ልብሰ መቃብር አነዳሁ
ወኮነነ ለነ መንበረ ትንሣኤ አቢየ ዘአስተዳለዎ ለሊሁ

👉ዋዜማ

ነጽር አማኑኤል ዘውስተ መቃብር ቤትከ ወዘውስቴቱ ነበረ
መቃብር ኆኅተቤትከ አኮነ ተሰብረ
ወነጽር ካዕበ መስፍነ ገሊላ ዘገብረ
ወጺአ ትንሳኤ እግርከ እምድኅረነጸረ
እስመነዋ ያስተዋርድ ክብረ

ሁለተኛ

ህድግ አማኑኤል ለቢሰ መቃብር ልብስ ዘእምነአዳም ቀነይኮ
እስመልብስ መቃብረሙሴ መጠንከ አኮ
ወለልብሰ አቤል ሞት በይነ ምንትኑ ለበስኮ
እስመ ዘተለብሰ ሞት ልብሰተሐውኮ
ወአንተሂ በይነምንት አፈቀርኮ

👉ሥላሴ

አማኑኤል ኢትፍርሆ ለበዓለ ዘመን መቃብር
እመክብረቤቱ ይበዝህ እስመ ከመ ሙሴ ነጋሲ
ይመውት ምስለክብረቤቱ መቃብር ብእሲ
ወክብረ ስልጣኑ ገሐነም ሀላፊ ምስለሰብአቤቱ ወራሲ
በከመ አዛርያስ ተበዐሲ
ወተዘከር ጽድቀ ግብረሳሉሲ
እስመ አንተ እምኩሉ ሐያሲ

👉ዘይዕይዜ

ይብል ሞት ወላዴሥጋ ትንሳኤ አልዓዛር ግብረ
እምድኅረ ገብረ ህቡአ
እምልብየ መቃብረሙሴ አማኑኤል ወጽአ
ወእንዘ የዋህ ይብል ተሰወረ ወተኀብአ
ሰራቄ ንዋዩ ለዮናስ ዘአስተጋብአ
ባዕል ዮናስ ብእሴ አክብሮ እግዚአ
ሰራቄ ንዋዩ ለዮናስ ዘአስተጋብአ

👉መወድስ

ለብሂለ የዋህ የዋህ መድኃኔዓለም ዘኩሎ የአምን ወያፈቅር ዘፀአሎ
ትንሳኤ ካህን ድኅረ አስተርአየ ኩሎ
እምኩይ መቃብረሙሴ ተገሓስ ይቤሎ
እስመ ቅድመ ያየውሆ ወያስህቶ መቅበርት ብእሴ እከይ ወተኀጉሎ
ሞትሂ ዘመደሥጋ ድኅረመከረ አህባሎ
ኢይርዓይ ከዊኖቶ ለመድኃኔዓለም አሰስሎ
ወኀበሀሎ ኢይብጻሕ ለመድኃኔዓለም አምሓሎ
ወመሐለ እንዘይብል ኢይበጽሕ ኀበሀሎ

እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው አደረሳችሁ 🙏🙏🙏

@beteyared21
@beteyared21
@beteyared21


"ወይእዜኒ ክርስቶስ ቀደመ ተንሥኦ እምኵሎሙ ሰብእ ምዉታን።"
አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኵር ኾኖ ተነሥቷል።

ኀበ ሰብአ ቆሮንቶስ ፩ ፲፭÷፳

እንኳን አደረሳችኹ።


{ቅኔያት በእንተ ትንሣኤሁ ለእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ በዕለተ ስንበት}

በየኔታ ቅዱስ ያሬድ

ጉባኤቃና

ተስፋ መንግሥተ ሄኖክ ኀሊ ወተዘከር ባዕለ ዮናስ እልመክኑ፣

ዓለመ ሥጋ መቅበርት አሐቲ አምጣነ ተኀልፍ ቦኑ።

2ጉባኤቃና

ውስተ ዓለመ ድዮስ ዝኅር ኢተፈጸመ ተምኔተ ዕፄያት አእዋም፣

አምጣነ ሕፅፅት ይእቲ መቃብረ ሥጋ ዓለም።

3ጉባኤቃና

ሞታ ለዝኅር ነፍሰ አልዓዛር ብእሲ፣

ነዋ ርሒቅ እምእግዚአብሔር ነጋሢ።

ዘአምላኪየ

ተስሕትከ ወልድ ሐናፄ መቃብር ታዕካ፣

እስመ አንተ በግብረ ትንሣኤ ለሰንበት ሰዐርካ፣

ወኢተዘከርከ ቃለ ዘሙሴ ለደብረ ናባው መልአካ።

2 ዘአምላኪየ

ዕፁታ ተሀሉ ቤተክርስቲያን መቅበርት፣

እስመ ኀልቁ እንዘይሰደዱ ኀበቦ ሕይወት ፣

ካህናተ ማስያስ አፅም ወሥጋ እለ አልቦሙ ማኅለቅት።

ሚበዝኁ

በግዐ ትንሣኤ ክቡር እግዚአብሔር ይሠየጥ ውስተ አሦርዮን ጎልጎታ፣

በሰሚዐ ሤጡ ደንገፀ መቃብር እጓለማውታ፣

አምጣነ አኮ ቀሊል ሤጠ በግዐ ዮሴፍ ያርብሕ ፆታ ኒቆዲሞስ ፆታ።

ዋዜማ

አብዕልተ ራጉኤል ብርሃናት ዘክብረ ትንሣኤ ክብሮሙ ፀወርተ ዘኤልያስ መና፣

ሐወፅዋ በጊዜ ትንሣኤ ለመቅበርት መባልና፣

ዘንዴተ ሥጋ አድከመ ወአመፅጕዐ ዘባና፣

እስመ በመከራ ዘሴኬም ወዘስልማና፣

ተፈጸመ ወኀልቀ ዘመና።

ሥላሴ

ስልጣነከ ዘትሴፎ በዓለ ስልጣን አማኑኤል እንዘ ከመ አልዓዛር አንተ ነሣኢ ዘዘአልዓዛር ሲመት፣

በኀይልከ ወበሥልጣንከ ትትሜካሕ ለምንት፣

እስመ ከመኢምንት በሳሌም ርኢኮ ለዘርዐ ዘሩባቤል ሞት፣

ወለውሉደ ሔዋን ዕፄያት፣

ኢያንበርካሆሙ ካዕበ እምውስተ መቅበርት፣

ሀገሪታ ለሔዋን ንግሥት።

ዘይእዜ

ኀያላነ ሞተ ወመቃብረ መዋዒ አምላክ ዘቀራንዮስ ንጉሥ፣

ገብአ ወተመይጠ በዘዮናስ ትፍሥሕተ ትንሣኤ ዘዘዮናስ ርእስ፣

ጌሰ ጌሰ ጌሰ ይገይስ፣

ኀበ ኀበ ሀለዉ አብ ወመንፈስቅዱስ፣

ነገሥተ አርያም ሰልሞን ዐጸፍተ ብርሃናት አልባስ፣

ኀበ ኀበ ሀለዉ አብ ወመንፈስቅዱስ።

መወድስ

ወልደ ሥጋ አዳም ወሔዋን ምውታነ ሥጋ ደመ አዝማዲሁ ኢረሥአ ወለጸላዒሆሙ ተበቀሎ፣

አምጣነ ወልደ አብ ለሞት ቀታሊሆሙ ቀተሎ፣

በሐፀ ትንሣኤ ዘሳሙኤል ወፄወወ በኃይለ ሥጋሁ ዘአኀዘ ኵሎ፣

ወለመቃብር ማኅደሪሁ በነደ ሙስና ዘሲኦል ወገሀነም አንበልበሎ፣

በደመናሂ ጉባኤቃና ወበመወድስ ዓውሎ፣

ወልደ ባሕርየ ያሬድ ለኢዮብ መርድአ ደብረጽዮን ተሰአሎ፣

ለእመ ቃሎ አጽምዐ ወኢተሐየየ ቃሎ፣

ለምድረ ጥበብ አምጣኒሃ ከመ ምንትኑመ ኀበሀሎ።

@beteyared21
@beteyared21
@beteyared21


👉👉ቅኔ ዘትንሣኤ
(ሊቀ ጉባኤ አባ ገ/ማርያም)

👉👉ጉባዔ ቃና

ዘርዐ ገራህተ ወልድ ወንጌል ዘበሐሰሳ ሐሰሳ
ኮነ ህየንተ አሐዱ ሰላሳ ወስሳ

ሁለተኛ

ምንትኑ ለወልድ ሃይማኖቱ እስመዘወልደአብ ፈቀደ
ትንሣኤ አልዓዛር ሦረ በዕለተ ሰንበት ጸመደ

ሶስተኛ

በቃለ አፉሁ ለወልድ ዘፍጡራነ አክበረ
ትንሣኤ አልዓዛር ዕጽ በዕለተ ሰሉስ ተፈጥረ

አራተኛ

ዲበሰለስቱ አህጉር መንክራተ ወልድ ቁልኤ
ተሰይመ ወልድ በአንብሮተ ዕድ ትንሣኤ

አምስተኛ

ምንተ ኮነ አማኑኤል ወአንሳሕስሖ አቀመ
እስከነሰሉስ ዕለት እስመ አማኑኤል ኖመ

👉👉ዘአምላኪየ

ብእሴ ዓመጻ መቅበርት ዘብዝሐ ንዋዩ ማሰነ
ይብል ዘመነ ትንሣኤ ክፍልየ ኢኮነ
ዘይደልወኒ ሊተ እስመ ኀጣዕኩ ፍጡነ

ሁለተኛ

ሊቀ ደብረ ኤልያስ ወልድ መገስፀ አዕሩግ አዕሩገ
ሀገረከ መቃብረ ሙሴ በይነ ምንት ኀደገ
እምድኅረ ሰራህከ ለነ ትንሣኤ አልዓዛር ህገ

ሶስተኛ

ተሐሰዪ እንከ ትንሣኤ አልዓዛር ምድር
ኀቤከ አምጣነ ተመይጠ አማኑኤል ክብር
ወብኪ ብኪ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ ምስጢር

👉👉ሚበዝሁ

ብእሴ ዓመጻ መቅበርት ምስሌሁ ለወልድ
በይነምንት ተጻብአ
ብእሴ ዓመጻ መቅበርት ዕብነ ኃቅል እስመ አንሥአ
ላዕሌሁ ለወልድ ዘያከብሮ መኑመ ወኢሳይያስ አጥብአ

ሁለተኛ

ኩሉ ይብልዎ ለባዕለፀጋ መቅበርት ቃለ አልዓዛር ሰማኤ
ጸዓዳ በግዐ አቅረበ ለትንሣኤ
ወአቅረበ ካዕበ ወይነ ተዋርዶ ወሞተ ሲሳየ አሞን በቋኤ

ሶስተኛ

መከራአማኑኤል ኮነ ሕላዌ ጉባዔ መቅበርት
ዘብዙህ ምንዳቤሁ
እስመኢበቁኦ በምንት መቃብር ጉባኤሁ
አማኑኤልሂ ልሂቅ በእንተ ጉባዔ መቅበርት እንዘ ይትነሳእ ይላሁ

አራተኛ

አዝማደ አማኑኤል ሐፍሩ በነሲዖቱ ብዙሐ
ትንሳኤ ሥጋ ብሩረ
እምነሐገሩ መቅበርት እስመ አማኑኤል ተሰወረ
አማኑኤልሂ የዋህ ለዓለመ ዓለም ኀደገ መቃብረ ሙሴ ሀገረ

አምስተኛ

በከመ ቅዱስ ውእቱ ስርወ ዕፀ ሕይወት ወንጌል ቅዱሳን አዕጹቂሁ
ወፍሬ ትንሣኤ ብዙሐ ይቀስሙ እምኔሁ
አዝማደ ሥጋሁ ለወልድ ወአግብርቲሁ ለወልድ እለሐለው ምስሌሁ

👉👉ዋዜማ

መደንግጸ ድምጸ ትንሣኤ ዘኩሎ ያፈርሕ
እምድኅረ አማኑኤል ሰምአ
በመስኮት መቃብረ ሙሴ አማኑኤል ወጽአ
ኢተመይጠሂ ዳግመ እስከ አማኑኤል ቦአ
ወቅድመገጸ ሞት ጎየ በሌሊት ህቡአ
እንዘ ይብል ኢየሐፍር ሰብአ

ሁለተኛ

ኢተመይጠ ውስተ ቤቱ ኖላዊ መቅበርት
ፈራሄ እግዚኡ ማህየዊ
በግዐ እስመ አማሰነ መቃብር ኖላዊ
ወኢተናገረ ምንተ መቃብረ ሙሴ ሀላዊ
እንዘ ለበግዕ ግዙፍ በፍናሌዊ
ይወስዶ ትንሣኤ ነዓዊ

👉👉ሥላሴ

መቃብር ሰዱቃዊ እመ ኢነጸርኩ ኢነጸርኩ ትንሣኤ ሙታን ዘርእየ እግዚአ ብዙህ ይባቤ
ትንሣኤ ሙታን ኢየአምን ይቤ
ወተናግሮ ኀደገ ድኅረ ነጸረ ነባቤ
ትንሣኤ ሙታን ምስጢረሶቤ
ወሐዋርያት አብዝሑ ምክረምንዳቤ
እስመሰምኡ ቃለአብ አቃቤ

ሁለተኛ

ይበኪ ወያስቆቁ መቅበርተ አልዓዛር ሰብአግፍዕ እንዘይብል መቅበርት ብእሴ ብዙህ ጎጉኦ
ንዴትየ ወተገፍዖትየ ተዘከር እግዚኦ
ትንሣኤ ሥጋ መስፍን ዘኢይፈርሕ ተገፍኦ
እስመ ለስምየ ያጠፍኦ
ወኀዘነ ካዕበ ዘይሰምኦ
እንዘይብል አማስን ሙኅባኦ

👉👉ዘይዕዜ

ተመነየ ወልድ ስደተሥጋ እክለ ቤተ አልዓዛር ሞት
ድኅረ ቀዲሙ ሰረጸ
ገራህትየ መቃብረሙሴ እስመኮነት ሐጸ
ወበእንተዝ መኑመ ኀዘነ ወደንገጸ
ወዓይነአማኑኤል ካዕበ ኢያስተሐየጸ
መንገለ ገራህቱ መቅበርት ወሀገረ ባዕድ ሐወጸ
ወዓይነአማኑኤል ካዕበ ኢያስተሐየጸ

👉👉መወድስ

ይቤ ካህን መድኃኔዓለም ዘሐሰሰ ይድህር
ውስተመቃብር ቤተ ዮሐኒ
ዘመደ አልዓዛር ሞት ዘበአልዓዛር ሰፋኒ
መቃብረ ጽላሎተቤቱ ከልዓኒ ከልዓኒ
ሞትሂ ባዕደ ሄኖክ በከዊኖትየ ሊተ ዘመደ ክርስቶስ ጸልዐኒ
ለዓለመ ዓለም ይእዜኒ ወዘልፈኒ
ሞት ባዕደ ሄኖክ ኢየሐድገከ ይቤለኒ
ወትንሣኤ ሥጋ ዘመድ ዘበአልዓዛር ወጣኒ
በጽሐ ወአልጸቀ ይርድዐኒ ይርድዐኒ

ሁለተኛ

በከመ ይቤ ነቢይ ትንሣኤአሐዱ አማኑኤል ሊቅ
ጎየ ወተግህሰ
ዘመደ አልዓዛር ሞት እስከሰብዐቤቱ ፈለሰ
ነቅዐማይ መቃብረሙሴ እስመየብሰ የብሰ
ወጠፍአ ዳግማየ ፍሬ ገራህቱ ለአቤል
እስመ ኢረከበ ዘሐሰሰ
አማኑኤልሂ አመረከበ እክለትንሣኤ ንዑሰ
ይብል አማኑኤል ሕይወትየ ተሐደሰ
ወይብል ቅውመ አፍአ መቃብር መቅደሰ
እስመአነ እመሰል ካህነ ወንጉሰ

ሶስተኛ

ለአጥፍኦ ዛቲ መቅበርት ምድረ ደማስቆ
ይቤለነ ለነ እግዚአኩሉ ፍጥረት
እሳተ ትንሳኤ እፌኑ ኀበ ደማስቆ መቅበርት
ከመትብላእ መሠረታቲሁ ትንሣኤ እሳት
ወናሁ እቀጠቅጥ ሙስና ወኀጉለ መናስግቲሃ እምጥንት
እስመ ደማስቆ መቅበርተሙሴ ዘበነቢያት
ኮነት መፍቀሪተ አምልኮተ ባዕድ ወጣዖት
ወበላዕሌሃ ዘበጽሐ ትንሣኤ ሥጋ ትንቢት
መቃብረአቤል ደማስቆ በአዝማዲሃ ተዋረደት

👉👉አጭር መወድስ

አማኑኤል ይብል ምስለ ሞተሥጋ ፌስቡክ
ሆከኒ ወአመንደበኒ መቃብር ቲክቶክ

በዓሉን የበረከት በዓል ያድርግልን አሜን 🙏🙏🙏🙏🙏

ሊ/ጉ አባ ገብረማርያም

@beteyared21
@beteyared21
@beteyared21


አዘጋጅ፦
"Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት"

@beteyared21
@beteyared21
@beteyared21























16 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.