መፅሃፍ ቅዱሳዊ ጋብቻ


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


በቻናላችን
👉 🌷ጋብቻ ምንድነው?🌷
👉 ❤️ማንን ላግባ?❤️
👉 😳ፖርኖግራፊና መዘዙ😳
🚩 የፍቅር ታሪኮች
💝 የርቀት ፍቅር
አጋር ቻናል:- @Nazrawi_tube
ለአስተያየት
👉 @Biblicalmarriage_bot
0910337074
🔵ቅድስና ለእግዚአብሔር🔵

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


ሰሜን ኮሪያ ትዳራቸውን የሚፈቱ ሰዎች እንዲቀጡ የሚደነግግ አዲስ ህግ ማጽደቋ ተነገረ
December 31, 2024
የኪም ጆንግ ኡን አስተዳደር በአለም ላይ ያልተለመዱ በርካታ ህጎችን ተግባራዊ በማድረግ ይታወቃል
እያዊቷ ሀገር ሰሜን ኮሪያ ትዳራቸውን በሚፈቱ ጥንዶች ላይ በሌላ የአለም ክፍል የማይገኝ እንግዳ ህግ ተግባራዊ ማድረጓ ተሰምቷል፡፡
አዲሱ ህግ ባለትዳሮቹ አንዳቸው በአንዳቸው ላይ አካላዊ ጥቃትን ጨምሮ ሌሎች በደሎችን ቢያደርሱም ለመፋታት እስከወሰኑ ድረስ ቅጣቱ እንደሚተላለፍባቸው ይደነግጋል፡፡
የእንግሊዙ ዘ ሰን ጋዜጣ ይዞት በወጣው ዘገባ የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን “ባለትዳሮች አጋርነታቸውን ለመበተን በመወሰን ለሰሩት ወንጀል ከፍተኛ የጉልበት ስራ ወደ ሚሰራባቸው ካምፖች እንዲላኩ ወስነዋል” ብሏል፡፡
የሰሜን ኮሪያው መሪ ፍቺ እንደ "ፀረ-ሶሻሊስት" ድርጊት ስለሚቆጠር ጥንዶቹ እስከ ስድስት ወር ድረስ በጉልበት ካምፖች ውስጥ እንዲቆዩ ወስነዋል።
እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በሀገሪቱ ተግባራዊ ሲደረግ በነበረው ህግ በመጀመሪያ ፍቺ የጠየቀው አካል ብቻ እንዲቀጣ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡
ነገር ግን በአዲሱ ህግ መሠረት የፍቺ ሂደቱ እንደተጠናቀቀ ሁለቱም ተጋቢዎች እንዲታሰሩ ደንግጓል፡፡ 
በባለፈው አመት መንግስት በብዛት የትዳር ፍቺ ጥያቁ የሚያቀርቡት ሴቶች መሆናቸውን ተከትሎ የግንዛቤ መፍጠሪያ ዘመቻ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል አድርጎ ነበር፡፡
በርካታ ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ችግሮችን በምታስተናግደው ሀገር የትዳር ፍቺ ምጣኔን ለመቀነስ የተለያዩ ጠንካራ ህጎችን ተግባራዊ ብታደርግም ከ2020 ወዲህ ምጣኔው በከፍተኛ ደረጃ እያሻቀበ እንደሚገኝ ዘገባው ይጠቅሳል፡፡
በ2019 ከኮሮና ቫይረስ መከሰት በኋላ ሙሉ ለሙሉ ዝግ በሆነችው ፒዮንግያንግ የኢኮኖሚ ሁኔታ በአስከፊ ሁኔታ መጓዝ ጥንዶች መሰረታዊ ፍላጎቶችን ማሟላት ባለመቻላቸው በርካታ ትዳሮች በመፍረስ ላይ ናቸው፡፡  
ከ2010 በኋላ የወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በሰሜን ኮሪያ በሁለቱም ጾታዎች ከ30 አመት በላይ የሆኑ ሰዎች 96 በመቶዎቹ ትዳር መመስረታቸውን ያመላክታሉ፡፡
በነዚህ መረጃዎች መሰረትም ከ1000 ባለትዳሮች መካከል 9 በመቶዎቹ ትዳራቸውን የሚፈቱት በትዳር አጋራቻው በሚደርስባቸው አካላዊ ጥቃት ምክንያት ነው፡፡


#ወጣቶችና_ቅድመ_ጋብቻ

ብዙ ወጣት "ከመጀናጀን" ያለፈ የቅድመ ጋብቻ እውቀት የለውም። Even በድብቅ የሚደረገው ቅጥ ያጣ "የጅንጀና" ሁኔታ አብዛኛው ወሲብ ቀስቃሽ ንግግር ያዘለ ሲሆን ብዙዎች ወዳልተፈለገና ጊዜው ወዳልሆነ የዝሙት ልምምድ እንዲገቡ ያደርጋቸዋል።

ቤተ ክርስቲያን ያላገቡ ወጣቶችን ሰብስባ የቅድመ ጋብቻ(Pre marriage) ትምህርት ማስተማር አለባት። በፍቅር ግንኙነት ዙሪያ ወጣቶችን Guide ልታደርግ ግድ ይላል። ይህ ካልሆነ ግን በግልፅ እንደሚታወቀው የብዙ ወጣቶች የፍቅር ህይወት ለብዙ ውድቀትና ለልብ ስብራት እየዳረጋቸው ነው።

እንዲህ ልል የቻልኩት ቢያንስ በየቀኑ በቴሌግራም የመፅሀፍ ቅዱሳዊ ጋብቻ (t.me/biblicalmarriage ) ቻናሌ ጥያቄና አስተያየት መቀበያ bot (t.me/biblicalmarriage_bot) በኩል የሚደርሰኝ የወጣቶች ጥያቄዎች ናቸው።

ቤተ ክርስቲያን ያላስተማረችውን ያልመራችውን ወጣት በኋላ Fail ሲያደርግ በምን አቅም ልትገስፀው ነው።

ስለዚህ ቤተ ክርስቲያን ነቅታ በዚህ ጉዳይ ልትሰራ ይገባል ብዬ አምናለሁ። ቤተ ክርስቲያን ዝም ስትል ሰይጣን ተግቶ ይሰራል።

❤️@Biblicalmarriage❤️
❤️@Biblicalmarriage_bot❤️


ቤቴ መጥተሽ ቡና አፍዪልኝ የሚልሽ የወንድ ጓደኛሽ/ፍቅረኛሽ ቡና ፈልጎ ሳይሆን #ቡን ሊያደርግሽ ነውና ብትችዪ ቤቱ አትሂጂ ካልሆነ ደግሞ ሁለት ሶስት ሆናችሁ ሄዳችሁ አብራችሁ ቡና ጠጡ። ለምን ይሄን ሁሉ ጀማ ይዘሽ መጣሽ ብሎ ፊቱና ንግግሩ የሚቀየር ከሆነ የአምኖን መንፈስ ተጠናውቶታል!

ቤት አስተካክዪልኝ
መጋረጃ ስቀዪልኝ
ልብስ እጠቢልኝ
ምግብ ስሪልኝ! ለሚሉ የቤት ውስጥ ግብዣዎች ላይ በጅምላ መንቀሳቀሱ ይመከራል የኔ ሚስኪን እህት!

ወንዶች አረጋጉት!

❤️@Biblicalmarriage❤️


ውድ የቻናላችን ተከታታዮች‼️

በውስጥ(@AbrishEL) በኩል ብዙ ሰዎች ያላችሁበትን ሁኔታ እያጋራችሁኝ ስለሆነ በጣም አመሰግናለሁ። ብዙ ሰዎች መልዕክት እየላኩ ስለሆነ ቶሎ ቶሎ ላንመልስ እንችላለን። ያንን ለማስቀረት ያላችሁበትን ሁኔታ በድምፅ ብትነግሩን ይመረጣል።

ተባረኩ


🛑  #በነጻ #በኦንላይን በሰርተፍኬት ፕሮግራም ይማሩ!

ሆሊስቲክ የመጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጅ ከመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ተቋማት ፌደሬሽን፣ ከኦንላይን ኮሌጆች ማሕበር እና በኢትዮጵያ ስነመለኮት ተቋማት ኮሚሽን ሙሉ እውቅና ያለው ኮሌጅ ነው።

❣️   በተግባራዊ ስነመለኮት በኦንላይን በሰርተፍኬት ፕሮግራም #በነጻ #በኦንላይን ባች #አስር ምዝገባ እያካሄደ ይገኛል።

ለሁለት ሳምንት የሚሰጠውን ትምህርት ለመከታተል ቀጥሎ ባለው የምዝገባ ሊንክ እንድትመዘገቡ እንገልጻለን።

📌 ኮሌጁ አሜሪካን ሀገር ካለው ቴራፎን ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ከዲፕሎማ እስከ ዶክትሬት ዲግሪ በስነመለኮት፣ በካውስሊንግ ሳይኮሎጂ እና በኦርጋናይዜሽናል ሊደርሽፕ ስፖንሰር ስላለው በቅናሽ ክፍያ ያስተምራል።

Register
👉 www.my.holisticbiblecollege.com/student/register

✍️የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ለሁሉም!

📞+251964773837
📞+251919741700

Telegram 👉 https://t.me/holisticbiblecollege


የተበላሸ የተቃራኒ ፆታ ፍቅር ውስጥ ያላችሁና በጣም የተጨነቃችሁ ምን ማድረግ ግራ የገባችሁ በማማከር ልረዳችሁ ዝግጁ ነኝ፡፡

ከዚህ በታች ባለው አድራሻ ልታገኙኝ ትችላላችሁ

@AbrishEL

@Biblicalmarriage_bot

ተባረኩ

መፅሃፍ ቅዱሳዊ ጋብቻ አገልግሎት


ክፍል ሁለት 2

"ምን? ማለት? እንዴት ሊሆን ይችላል? ለምን? የሚሉ ቃላት ከአፌ በድንጋጤና በብስጭት ይወጡ ነበር። ምንም ሳልላት ወዴት እንደምሄድ ሳላውቅ እየሮጥኩ ወጣሁ። ጓደኛዬን በጣም ነበር የምወዳት። እሷ ለኔ ከእህትም በላይ ነበረች:: ያለምንም ምክንያት እንዲህ ልታደርግብኝ አትችልም። ማሰብ ያቆምኩኝ ያክል ተሰማኝ። እሺ ምንድነው የማደርገው? ያለኝ አማራጭ ደግሜ እውነቱን መንገር ነው። "

" ' እግዚአብሔር መልካም ነው። እኛ የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን እንፀልያለን ደግሞም ዳኑን እኛ እራሳችን እናናግረዋለን። አሁን ፈተና ስለደረሰ ራስሽን አረጋግተሽ ለማጥናት ሞክሪ።' ብለው እኔን ማረጋጋቱ ተያይዘውታል አብረውኝ የሚያገለግሉ ጓደኞቼ። እኔ ግን ማረጋጋትም ቀስ ብሎ ማሰብም አልቻልኩኝም። ዳኒ እኔን አለማመኑ ቢያበሳጨኝም በተደረገው ክፉ ስራ ማዘኑን ሳስብ ያሳዝነኛል። እሱም እውነት አለው። ስለዚህ የቻልኩትን ማድረግ አለብኝ ብዬ ወሰንኩኝ። የመጨረሻ ምርጫዬ ጓደኛዬ ኤልሳ ናት። ያኔ ሆስፒታል ተኝቼ 'ጥፋቱ የኔ ነው' ያለችኝ ምክንያት በመጠየቅ ሰበብ እሷን አግኝቼ ለዳኒ የተደረገው ሁሉ እንድትነግረውና እኔ ምንም ነገር እንዳላደረኩኝ እንድታስረዳው ልጥይቃት ስልክ ደወልኩላት። እያለቀሰች እናገረችኝ። እኔ ግራ የገባኝና ያናደደኝ የሷ ማልቀስ ነው።የምንገናኝበትንና ሰዓት ወስነን ስልኩ ተዘጋ!"

"ከእሷ ቀድሜ ስለነበር የተገኘሁት እሷ ስትመጣ ሳያት መሆን የሌለብኝ ስሜት ተሰማኝ...ጥላቻ...። ' ማርቲ ማድረግ የሌለብኝን ነገር አድርጌያለሁ። ይቅር በይኝ!' ብላ ንግግሯን ስትጀምር በቅድሚያ ትክክለኛውን ነገር ንገሪኝ ቀጥሎም እንዴት ልትረጂኝ እንደምትችዪ አሳውቂኝ። ብዬ ተቆጣዋት! ኤልሳም እሷ እክክለኛውን ነገር እንደምትነግረው ቃል ገባችልኝ። እኔም ድጋሚ ልታገኘኝ ከፈለገች ይህን ካደረገች በኋላ እንደሆነ ነግሬያት ተለያየን።"

"እኔ ምንም ነገር ውስጤ አልከበደብኝም። እኔ ጋ እውነት አለ። ጥፋት አላጠፋሁም። ቢሆንም ግን ዳኒ እውነቱን ካወቀ በኋላ ብንለያይም አይጨንቀኝም።" ትላለች ማርታ። በዚህ ሰዓት በራስ መተማመንም የዳኒ ናፍቆትም በንግግሯ ውስጥ ይነበባል።

"ከሁለት ቀናት በኋላ የእጅ ስልኬ ጮኸ" ትለናለች ማርታ....እስቲ እንከታተላት

"ሄለው ማን ልበል? ስል 'ማርቲዬ ደህና ነሽ? ሔለን(የተቀየረ ስም) ነኝ' ሔለን አብራኝ የተማሪዎች ህብረት የምትመራ መልካም እህት ናት። 'ዛሬ ዳኒን አግኝተን አውርተን ነበር ሀሉን ነገር በስርዓት ተነጋግረናል። ለዕረፍት ቤተሰብ ጋ ስለሄደ ከሁለት ቀን በኋላ ተመልሶ እንደሚመጣና እንደሚያገኝሽ ተስማምተናል። ስለዚህ ጠብቂው። ሁሉም ነገር ተስተካክሏል እሺ ማርቲ አታስቢ። በቃ እንገናኛለን' ብላኝ ስልክ ዘጋን። የሆነ ደስታ ተሰማኝ ትላንት የሆነውን ነገር ረሳሁት።ዳኒ መጥቶ እውነትም እስከምንነጋገርና ወደ ቀድሞ ፍቅራችን እንደምንመለስ ናፍቄያለሁ።"

"ቀኑ አልፎ በሦስተኛው ቀን በአካል ተገናኘን። ውስጤን ናፍቆት ንዴት ሃዘን ይሰማኛል።ምክንያቱ ብዙ ነው። የመጀመሪያ ጥያቄዬ የነበረው የሱን ደህንነትና ለምን ስልኬ እንዳላነሳ ነበር የጠየኩት። ዳኒም ' ማርቲ ሁሉንም ነገር ደርሼበታለሁ ኤልሳም ነግራኛለች። አንቺን አለማመኔ አሳፍሮኝ ነው ስልክ ያላነሳሁት። አሁን ምንም ነገር ልታስረጂን አልፈልግም ሁሉን አውቄያለሁ። ምንም ወሬ ሳላበዛ ይቅርታ ብቻ አድርጊልኝና ፍቅራችንን እንቀጥል።' ሲለኝ ምንም ማውራት አልፈለኩም ምክንያቱም ራሱ ጥፋቱን አምኗል። ኤልሳንም ደውዬ ይቅር ብዬሻለሁ አልኳት። "

"ከብዙ ቀናት በኋላ ዳኒ 'እራት ካልጋበዝኩሽ' አለኝ። እኔም ደስ አለኝ። እሺ አልኩት። ነገር ግን የእራቱ ግብዣ ጓደኛው በተከራየው ቤት ውስጥ እንደሆነ ሲነግረኝ ውስጤ መሄድ እንደሌለብኝ ቢነግረኝም መጥፎ ነገር ሊፈጠር አይችልም በሚል የእራት ግብዣውን 12:00 ለማድረግ ተስማማን።ነገር ግን ማንም ሰው አብሮሽ እንዳይማጣ ሲለኝ ተጠራጥሬ ነበር።"

12:00 ላይ ጓደኛው ቤት ጋ ስደርስ ወጥቶ ወደቤት አስገባኝ። ቤቱ በሚያምር ሁኔታ አድምቆታል። ሰላም ተባብለን አንድ ወንበር ነበረች እሷ ላይ ልቀመጥ ስል 'በፍፁም አይሆንም እዚ ጋ ነው መቀመጥ ያለብሽ' ብሎ አልጋው ላይ አስቀመጠኝ። እሱም ተቀመጠ። የተዘጋጀውንም እራብ በላን። ከምሽቱ 1:00 ላይ እጄን መንካትና ሰውነቴ ማሸት ሲጀምር ብድግ ብዬ ተንሳሁ። ምን እያደረክ ነው እዚ'ኮ ብቻችንን ነን። ጌታን መበደል የለብንም በቃ እራት በላን አይደል እንሂድ ስለው እጄን ስቦ አስቀመጠኝና 'የምነግርሽ ነገር አለ' አለኝ። እሺ ምንድነው ዳኒ የምትነግረን? ' ትወጂኛለሽ' ብሎ ሲጠይቀኝ ተናደድኩኝ። 'በእርግጥ ድንግል ነሽ? እኔ እስካሁን ማመን አልቻልኩኝም። እዛ እላጋ ላይ አብሮሽ የተቀመጠው ወንድምሽ ነው ብዬ ለማመን እስካሁን ከብዶኛል። ስለዚህ #ድንግልናሽን_ካልሰጠሽኝ_እጣላሻለው ደግመንም አብረን አንሆንም። አንቺ በእርግጥ ድንግል ከሆንሽ ይኸው ዛሬ አይቼ ልመን' ሲለኝ ፈራሁኝ። ሁለት ፍርሃት። አንደኛ ጌታን ልበድል መሆኑ ሁለተኛ ዳኒን ላጣው በመሆኔ። ግራ ገባኝ። ትሰማለህ ዳኒ? በጣም እወድሃለሁ አፈቅርሃለሁ ታምኜልሃለሁ። ድንግል ነኝ ስልህ ልታምነኝ ይገባ ነበር። ነገር ግን አላመንከኝም። እንድታምነኝ #ዝሙት ሰርቼ አላሳምንህም! ስለዚህ በጣም አዝናለሁ። ድንግልናዬን እንዳላጣ ብዬ ሳይሆን ዋጋ ከፍሎ ያዳነኝና የራሱ ማደሪያ ያደረገኝን ጌታ አልጋ ላይ ተኝቼ ዝሙት ሰርቼ አልበድለውም። ቅድስናዬ አስጠብቄ ጌታን አስደስቼው ክብረ ንፅህናዬ ጠብቄ እስከትዳር እኖራለሁ። ለአንተ ይቅርታ አድርጌልሃለሁ። ከዚህ በኋላ ግን እኔና አንተ ማቼውም ፍቅረኛሞች መሆን አንችልም። ብዬው ልወጣ ስል እጄን ያዘኝና አልጋው ላይ ጣለኝ። እፍን አድርጎ ያዘኝ። ነገር ግን እንዴትም ብዬ ያለ የሌለ ኃይሌን ተጠቅሜ እጁን ንክስ አድርጌው በአንድ እግር ጫማ ከዛ ቤት እየሮጥኩኝ ወጣሁ። ጌታ ታደገኝ።" በማለት እንባና ሲቃ በተሞላ መልኩ ታሪኳን አጫወተችኝ። እንዲህ ያስለቀሰኝ በእንደዚህ አይነት ህይወት ያለፈች እህቴ ትዝ ብላኝ ነው። የሷ ታሪክ ሌላ ጊዜ እነግርሃለሁ" ብላ ሌላ ታሪክ ልትነግረኝ ቃል ገብታልኝ ታሪኳን ቀጠለች።

በመጨረሻም ትለናለች ውድ እህታችን " እሱም ሌላ ሱስ ውስጥ ገብቶ ከጓደኛዬ ኤልሳ ጋር አብረው ጓደኝነት ጀመረው ነበር እኔም በሰላም ተመረኩኝ። ከምርቃቴ ሦስት አመት በኋላ በጣም የምወደውና የሚወደኝ ውድ ባል አገባሁኝ። #ድንግልናዬን_ለባሌ ሰጠሁት ቆንጆም ልጅ ወለድን። የዳንኤል ታሪክ ስሰማ ከኤልሳ ጋር አብረው እንዳልቀ ጠሉና ሌላ ሴት እንዳገባ ነው"

" ስለዚህ #ድንግል_ለባል_እንጂ_ለጓደኛ_አይሰጥም" በማለት ማርቲ ታሪኳን በዚህ አጠናቀቀች። እኛም እሷ ከተነገርችው ንግግር አንዱን ወስደን የታሪኩ መቋጫ እናድርግ......

💢 #ድንግልና_ለባል_እንጂ_ለጓደኛ_አይሰጥም! 💢

💍 @Biblicalmarriage 🌷
ለአስተያየት 👉 @Biblicalmarriage_bot

የሚያሸልም ጥያቄ 3:40 ላይ ይጠብቁን! ታሪኩን ያላነበበ መልሱን በፍፁም ሊያገኘው አይችልም!


❤️ @Biblicalmarriage ❤️
❤️ @Biblicalmarriage ❤️


ዛሬ ምሽት ክፍል 2 ይለቀቃል


#ድንግልናሽን_ካልሰጠሽኝ_እጣላሻለሁ (Repost)

አንድ ማርታ(የተቀየረ ስም) የምትባል ልጅ ነበረች። እድሜዋ 20 ሲሆን 2ኛ አመት የምህንድስና ተማሪና የተማሪዎች ህብረት መሪ ነች።ዳንኤል(የተቀየረ ስም) ከሚባል ልጅ ጋር ከተዋወቀች 1 ዓመት ከ 2 ወራት አልፏል! በነዚህ ጊዜያት ከዚህ በፊት አይታው የማታውቀው እንክብካቤ ያሳያታል እሷም በጣም ትወደዋለች! ታምነዋለች። ሁልጊዜ መንፈሳዊ ነገር ያስተምራታል። ይህ ልጅ ለእሷ የሚያስብና የሚሳሳ ሰው ነው። ያስጠናታል። እሷም በነዚህ ጊዜያት ባየችው ፍቅርና እንክብካቤ ተማርካ ሙሉ ልቧን ሰጥታዋለች!ከባለታሪካችን ጋር ቆይታ እናድርግ...."ይህማ የወደፊት ባሌ ነው ብዬ አስብ ነበር" ትላለች ባለታሪኳ! "ነገር ግን ይህንን ፍቅርና እንክብካቤ ማጣጣም በጀመርኩበት ወቅት ዳኒ እጅጉን ነጭናጫና ብስጩ ሆነ። ቃሎቹም እኔን እየከበዱኝ ይመጡ ጀመር። እኔ ግን ከሱ ውጭ ማሰብ አልቻልኩኝም! ትምህርቴንም በተወሰነ መልኩ ችላ አልኩኝ። ዳኒ ምን ሆኗል ብዬ ማሰብ ሆነ ስራዬ። ዳኒ ጓደኞቹም ላይ ተቀይሯል!" እያለች ታሪኳን ትቀጥላለች።በዚህ መሃል ነበር እንባዋል መቆጣጠር አቅቷት አይኗ በእምባ ተሞላ። እኔም ታሪኩን እንድትጨርስ አደረኳት ታሪኩም እንዲህ ይቀጥላል..." ዳኒ 'ዛሬ በጣም እፈልግሻለሁ' ብሎ Text አደረገልኝ። እኔም ላለፈው ሳምንት ድምፁንም ስላልሰማሁ በአካልም ስላላገኘሁት ከግቢ ውጭ ወደ ቀጠረኝ ካፌ በፍጥነት ሄድኩኝ። ዳኒም ሰላም ካለኝ ካለኝ በኋላ ቀጥሎ 'አንቺ ግን ትወጂኛለሽ?' የሚል ጥያቄ ነበር የጠየቀኝ።እኔም ውስጤን ስለማውቀው ለእርሱ ያለኝን ከፍተኛ ፍቅር እንባ እየተናነቀኝ ነገርኩት። እርሱም 'ዛሬ ግቢ አንገባም ውጭ ነው የምናድረው!' ሲለኝ ይህ እንደማይሆን አጥብቄ ብነግረውም ይባስ ይጮህብኝ ጀመር እኔም በፍቅር ለምን ውጭ እንደማናድር ደጋግሜ ብነግረውም ጭራሽ ተቆጥቶኝ ጥሎኝ ሄደ። እንደዛ ይሳሳልኝ የነበረው ዳኒ ምን ሆኗል ብሎ ማሰብ ሆነ ስራዬ።" በማለት ምሬትም ንዴትም ጭንቀትም በሞላበት ስሜት ሃሳቧን ቀጠለች።"ጓደኞቼም 'ዳኒ የሆነ ነገር ሳይሆን አይቀርም!' ሲሉኝ ምን ሁኔታ ላይ እንዳለ የማወቅ ጉጉቴ የበለጥ ጨመረ። እንደወትሮዬም ከዚህ በፊት አብረን የምንቀመጥበትና የምንገናኝበት ቦታ እሱን ፍለጋ ስሄድ ያየሁትን ነገር ማመን አቃተኝ።ደነገጥኩኝ! ከዛ በኋላ የሆንኩትን ነገር አላውቅም። ከ30 ደቂቃ ቆይታ በኋላ ስነቃ ራሴን ያገኘሁት ሆስፒታል አልጋ ላይ ነበር። 'ማርቲዬ አይዞሽ እኔን..ምክንያቱ እኔ ነኝ' የሚል ድምፅ ሰማሁኝ። ይህን ድምፅ በደንብ አውቀዋለሁኝ። የራሴ የልብ ጓደኛዬ የሆነችው ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጀምሮ አብረን የተማርን እንደ እህቴ የማያት ጓደኛዬ ነበረች። ይህንን ድምፅ ስሰማ ይባስ ተበሳጨሁ ተናደድኩኝ ተለዋወጥኩኝ። 'አንቺ ነሻ የኔ የምለውን ዳኒን የቀየርሽብኝ። እያመንኩሽ ጉድ የሰራሽኝ ከሃዲ' ብዬ መጮህ ጀመርኩኝ። ዳኒን ፍለጋ ስሄድ እዛ ቦታ ያየሁት ሲሳሳሙ ነበር።ከዚህ በኋላ አይንሽን ማየት አልፈልግም ብዬ ከዛ ሆስፒታል ብቻዬን ወደ ግቢ ሄድኩኝ። አሁንም ግን ዳኒን ይፈልጋል ልቤ። አሁን ባየሁትና እሱ እየሆነ ያለው ነገር ትላንትን ሊሸፍንብኝ አልቻለም። ድንገት የእጅ ስልኬ ላይ Text ገባ። ክፍቼ ሳነበው 'እባክሽ ሚስጥር ለንገርሽ ስለምፈልግ ማታ 12 ሰዓት ላይ ግቢ ፊት ለፊት ያለው ካፌ እንገናኝ' ይላል። እቺ ልጅ ጉድ የሰራችኝ ጓደኛዬ ጓደኛ ናት። ይህንንማ ማወቅ አለብኝ ብላ ቀጠለች። ሰዓቱን መጠበቅ ስላልቻልኩኝ እባክሽ ከቻልሽ አሁን እንገናኝ ብዬ ላኩላት። 'የኔ እህት አሁን Class ሳላለኝ 10 ሰዓት ላይ እንገናኝ'ብላ መለሰችልኝ። 10 ስዓት ላይ ይችን ልጅ አገኘዋት። የምትነግረኝን ለማንም እንዳትናገር ቃል አስገብታኝ ሁኔታውን ትነግረኝ ጀመር። ' ያንቺና የዳኒ ፍቅር የግቢ ተማሪ ሁሉ የሚያውቀውና የሚቀናበት እንደሆነ አውቃለሁ። ኤልሳ ዳኒን ስለምትፈልገው ማርታ ከሌላ ወንድ ጋር ሆቴል ገብታ አድራለች ከዛም ድንግል ነኝ ብላ የምትዋሽህም ውሸቷን ነው ብላ ስለነገርችው ነው ዳኒ አንቺ ላይ የተቀየረው።' ብላኝ 'ከዚህ በላይ መቆየት አልችልም ብላኝ ሌላ የአዕምሮ ስራ ሰጥታኝ ትታኝ ሄደች።ሰማይ ምድሩ ዞረብኝ። እኔ'ኮ አይደለም ከሌላ ወንድ ጋር ልተኛ ይቅርና ሌላ ወንድ ሊያቅፈኝ ሲሞክር እንኳን የምጣላ ሴት ነኝ። ሳላገባ አይደለም ድምግልናዬ ከንፈሬን እንኳን አላስነካም ብዬ ለራሴም ለእናቴም ጋር ቃል ገብቻለሁ።" በትካዜ ጭልጥ ብላ ሄደች ንግግሯም ለተወሰኑ ሰከንዶች ተቋረጠ። "ዳኒ አያምነኝም ነበር ማለት ነው። እንዴት ከእኔ ሌላ  ሰው አመነ። ብለየው እንኳን እውነቱን ነግሬው መሆን አለበት ብዬ ስላመንኩኝ ደውዬለት ላገኘው  እንደምፈልግ ነግሬው በቀጠሮውም ሰዓት ወደምንገናኝበት ቦታ አመራው። እሱም ቀድሞኝ ተገኝቷል።ሰኣት አክባሪነቱን እወድለታለሁ።ነገር ግን ሳየው የተደበላለቀ ስሜት ተፈጠረብኝ። ንዴት ፍቅር ናፍቆት ጥላቻ...ብዙ ብዙ። ተጨባብጠን ተቀመጥን። ስለ እኔ ማንነት ከመጀመሪያው ጀምሮ ከነገርኩት በኋላ አስደንጋጭ ቃል ከአንደበቱ አወጣ። 'አሁንም ትዋሻለሽ እኔ'ኮ ከራሴ ይልቅ ነበር ያመንኩሽም የወደድኩሽም። አንቺ ግን አሁንም ድንግል ነኝ ስትዪ አታፍሪም? ውሸታም ነሽ' ብሎኝ ከደብተሩ ውስጥ አንድ ፎቶ አውጥቶ አሳየኝ። ደነገጥኩኝ...እኔ ነኝ ፎቶው ላይ ያለሁት። የሆነ ወንድ እኔን ሲስመኝ የሚያሳይ። ከሆነ ወንድ ጋር ተቀምጬ የሚያሳይ። ይህ ወንድ ደግሞ ግቢ ውስጥ እኔን የሚፈልገኝና ከዚህ በፊት ከዳኒ ጋር የተጣለ ልጅ ነው። አዕምሮዬ ማሰብ እንዲሁም ይህ መች እንደሆነ ሊያውቅ አቃተው። ዳኒም ጥሎኝ ሄደ።

@Biblicalmarriage

እኔና ፎቶው ተፋጠጥ። እኔ ነኝ ልጁም እራሱ ነው። ነገር ግን ይህንን ነገር አላደረኩትም። ከዚህም ልጅ ጋር እንዲህ ባለ አስነዋሪ ድርጊት የትም አልተገናኘንም። ዞረብኝ። መሳቅ ጀመርኩኝ። ጥንቃቄ በተሞላው መልኩ በሚያሳምን ሁኔታ በPhotoshop የተሰራ ፎቶ ነው! አልጋው ላይ ተቀምጫለሁ። እዛ አልጋ ላይ የተቀመጠው ግን እኔን ሊጠይቀኝ የ መጣው ወንድሜ ነበር። እንዴት እንዱህ እንደተደረገ ለማወቅ የሴት ጓደኛዬ ጋር ደውዬ ማግኘት እንዳለብኝ አመንኩ። ልጅቷንም አገኘዋት። እንዴት እንደሆነም በዘርዝር ነገረችኝ። ዳኒዬ አሳዘነኝ። ፎቶው ተሰርቆ ተወስዶ ነው እንዲህ የተሰራው። ይህንን ተንኮል ያሰራው ከምወዳት ጓደኛዬ ጋር ተመሳጥሮ ያ ይፈልገኝ የነበረው ልጅ ነው። ይህ ቀላል ስለሆነ ለዳኒብትክክለኛውን ፎቶ አሳይቼው አሳምነዋለሁ! ብዬ አሰብኩኝ። በፍጥነት ወደቤት ሄጄ ስፈልገው ፎቶው የለም። ኤልሳ ጋር ደውዬ እባክሽ እኔ ከአንቺ ምንም አልፈልግም ተንኮል የተሰራበትን ትክክለኛውን  ፎቶዬ ስጪኝ አልኳት። ይቅርታ አድርጊልኝ ማርቲ ፎቶውን ልጁ ቀዳዶ ጥሎታል አለችኝ።"

ታሪኩ ይቀጥላል......ነገ ከምሽቱ 3:00 ላይ ይቀጥላል

እራሶን በማርታ ቦታ ያድርጉና በቀጣይ ምን ያደርጋሉ? መልስዎትን  በ @Biblicalmarriage_bot በኩል ይላኩልን!










እጮኝነት ላይ ጥያቄ ካላችሁ 1:40 ጀምሮ በሚኖረኝ Live ስርጭት ላይ መጠየቅ ትችላላችሁ

Telegram live


#ስራኝና ✝️ስራብኝ‼️
===============
🔖#እግዚአብሔር አንተን ሳይሰራ በአንተ አይሰራም
#እግዚአብሔር አንተን ሳይለውጥህ በአንተ ሰውን አይለውጥም አንተን ሳያንጽህ በአንተ ሰዎችን አያንጽም ምክንያቱም ያልተለወጠ አይለውጥም ያልተሰራ አይሰራም ያልታነጸ አያንጽም።
🔖 እኛም በየዘመናቱ ያልተቀየሩ ቀያርዎችን ያልተለወጡ ለዋጮችን ያልታነጽ አናጾችን አይተንም፣ሰምተንም አናውቅም ለዚህ ህያው ምስክር ታሪክ ሳይሆን መጽሐፍ ቅዱስ ነው።
#እግዚአብሔር አንተን ይለውጣል ያንተን ነገር ይለውጣል፣በአንተ ተጠቅሞ ብዙዎችን ይለውጣል።
ቤት ለሰው መኖርያ ማረፊያ ከመሆኑ በፊት መሰራት መገንባት ቅርጽ መያዝ አለበት‼️በክርስትና ልክ እንዲህ ነው አገልጋይ ከመሆን በፊት መሰራት አለብህ።እግዚአብሔር #ለህዝብ የሚሆን #መልዕክት ለአንተ ከመስጠቱ በፊት አንተን ለመልዕክቱ ያዘጋጅሀል ይሞላሀል #ይሰራሀል።
#እግዚአብሔርን የሰማ #ይሰማል #ያደመጠው #ይደመጣል #ያከበረው #ይከብራል #የወደደው #እንደተወደደ #ይቀራል።
"ከሁሉ በፊት በእግዚአብሔር መሰራት ይቀድማል"
አሜሜሜን‼️


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
ሲስተርሊ ብራዘርሊ የሚባል ነገር የለም


አራቱ ተግባቦቶች

***

ከሰዎች ጋር  ዕለት ተዕለት በሚኖረን ግንኙነት ወቅት የሚኖሩንን የተግባቦት አይነቶችን በአራት ከፍለን ማየት እንችላለን::

1- Aggressive (ቁጡ/ሃይለኝነት ያጠላበት):- እነዚህ ሰዎች ሃሳባቸውን በሃይለ ቃል እና በስሜታዊነት በመግለጽ ይታወቃሉ:: ሲያወሩ ጠረጴዛ እየደበደቡ፣ ደምስራቸው ተገታትሮ፣ በከፍተኛ የንዴት ስሜት ውስጥ ሁነው፣ ቡጢ ጨብጠው ነው::

የራሳቸውን ሃሳብ ሌሎችን በሚጎዳ መልኩ መግለጻቸው ችግር ይፈጥራል::

የቀድሞ የኢሰፖ መሪ ኮ/ል መንግስቱ ሃይለማሪያምን ንግግሮችን በዋቢነት መጥቀስ ይቻል ይሆን? 😊

2- Passive:- ሁሉን በጸጋ የሚቀበሉ፣ ሽቁጥቁጥ፣ ሃሳባቸውን ለመግለጽ ፈራ ተባ የሚሉ አይነት ናቸው:: እነዚህ ሰዎች ችግር ቢከሰት ባይከሰት የማይደንቃቸው ፣ ለስሜታዊነት ሩቅ የሆኑ፣ ነገር በሩቅ የሚሸሹ ናቸው::  የራሳቸውን ጥቅም ለሌሎች በማሳለፋቸው ምክንያት ለብዝበዛ ሊጋለጡ ይችላሉ::

3- Passive-Aggressive:- እነዚህ ሰዎች የታመቀ ሃይለኝነት ቢኖራቸውም ሃሳብ አስተያየታቸውን ፊት ለፊት ለማቅረብ ይፈራሉ:: ይልቁንስ ብስጭት እና ቅሬታቸውን በህቡዕ መፈጸም ይቀናቸዋል:: ማለትም ስም በማጥፋት፣ ስራን በማበላሸት፣ በመልገም እና በመሳሰሉት ንዴታቸውን ሲገልጹ ይስተዋላሉ:: እነዚህ ሰዎች ለራሳቸውም ሆነ ለሌሎች አደገኞች ናቸው::

4- Assertive:- ሃሳብ አስተያየታቸውን ሚዛናዊ በሆነ ሁኔታ በቀጥታ መግለጽን የተካኑ ናቸው:: እነዚህ አይነት ሰዎች የሚፈጠሩ ቅራኔዎችን በጥበብ መፍታትን መለያቸው ነው:: በዚህም መሰረት ሁለቱንም ወገን የሚጠቅም መፍትሄ ላይ ይደርሳሉ::

እናንተስ ከሰዎች ጋር ስታወሩ ፣ ስታወጉ ፣ ስትወያዩ አልያም ስትከራከሩ የትኛውን አይነት ተግባቦት ትጠቀማላችሁ?

አሻም አሻም!

ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው- የአዕምሮ ህክምና ስፔሻሊስት

@Biblicalmarriage





20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.