Christ and Him Crucified


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Inglizcha
Toifa: Din


As we navigate the journey of life together, let’s focus on pursuing truth, holiness, and godliness. Let's to gently confront sin, along with the influences of the world & the flesh. CORAM DEO.

Bog‘liq kanallar  |  O‘xshash kanallar

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Inglizcha
Toifa
Din
Statistika
Postlar filtri


Wishing you all a wonderful Reformation Month. It's a October!


በዚህ ጉዳይ ምን ሐሳብ ኣላችኹ?


የፕሮቴስታንት እምነት ዘላለማዊ አሻራ በዓለም የታሪክ መድረክ

ከ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ የተነሣው የፕሮቴስታንት ንቅናቄ ዓለምን በአዲስ መነጽር እንዲታይ ያደረገ አብዮት ነው። ይህ እምነት የሰውን ልጅ ከባህላዊና ከስርዓታዊ ገደቦች ነፃ በማውጣት፤ በግል ሕሊና፣ በዕውቀት ተደራሽነት እና በማኅበራዊ ልማት መስክ ዓለምን የለወጠ የማይጠፋ አሻራ ጥሏል።

ማርቲን ሉተር መጽሐፍ ቅዱስን ወደ ጀርመንኛ መተርጎሙ እና በጉተንበርግ የሕትመት ማሽን መባዛቱ የሰውን ልጅ የማንበብና የመጻፍ አቅም በከፍተኛ ሁኔታ አሳድጎታል። በወቅቱ በነበረው እምነት መሰረት መጻሕፍት ለጥቂቶች ብቻ ተወስነው የነበረውን አሰራር በመስበር ሕዝቡ ራሱ አነፍንፎ ዕውቀትን እንዲቀስም በማድረግ የዘመናዊው የትምህርት ሥርዓት መሠረት ተጥሏል።

ይህ የዕውቀት ዲሞክራሲያዊነት ለዘመናዊ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መመስረት ትልቅ መንገድ ከፍቷል። በዓለም ላይ የሚገኙ እንደ ሃርቫርድ፣ ዬል እና ፕሪንስተን ያሉት ታላላቅ የዓለም ዩኒቨርሲቲዎች መጀመሪያ ሲቋቋሙ በፕሮቴስታንት ክርስቲያናዊ ተቋማት እና ሰባኪዎች ተነሳሽነት ነበር። እነዚህ ተቋማት ሚሊዮኖችን በማስተማር የሳይንስ፣ የቴክኖሎጂ እና የፍልስፍና ባለሙያዎችን ለዓለም አበርክተዋል።

ዛሬ ከዓለም አጠቃላይ ክርስቲያኖች ውስጥ ከ900 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ የፕሮቴስታንት (Evangelical, Pentecostal, and Mainline Protestant) ቤተ ክርስቲያን ተከታዮች አሉ። ይህ ግዙፍ ማኅበረሰብ በየዓመቱ በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር በማውጣት በዓለም ዙሪያ ባሉ ድሆች ሀገራት የትምህርት፣ የንጹህ ውኃ፣ የጤና እና የሰብአዊ ድጋፍ ፕሮግራሞችን በመዘርጋት ግንባር ቀደም ሚና ይጫወታል።

ከዚህም ባሻገር እንደ ታዋቂው ሶሺዮሎጂስት ማክስ ቬበር ጥናት መሠረት ፕሮቴስታንታኒዝም "ማንኛውም ሐቀኛ ሥራ ለአምላክ የሚሰጥ አገልግሎት ነው" የሚለውን የሥራ ምግባር እና የካፒታሊዝም መንፈስ (The Protestant Work Ethic) ጽንሰ-ሐሳብ አስተዋውቋል። ይህ ፍልስፍና ግለሰቦች በዲሲፕሊን፣ በታታሪነት እና በኃላፊነት ስሜት እንዲሠሩ በማነሳሳት የዘመናዊውን የኢኮኖሚ፣ የንግድ እና የኢንዱስትሪ ሥርዓት እንዲጎለብት አስችሏል። በተጨማሪም እያንዳንዱ ሰው ከፈጣሪ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት እንዳለው እና የራሱን የሞራል ውሳኔ በሕሊናው የመወሰን መብት እንዳለው ማስተማሩ፤ ለዘመናዊው የዲሞክራሲ፣ የሰብአዊ መብት እና የሐሳብ ነፃነት ጽንሰ-ሐሳቦች መፈጠር የፍልስፍና መሠረት ሆኗል።

የፕሮቴስታንት መንፈስ እንደ አዲስ ንጋት የወጣ፣ የሰውን ልጅ ሕሊና የፈታ ኃይል ነው። ይህ ታሪክ በትውልዶች ልብ ውስጥ የሚዘመር የዕውቀትና የነጻነት ዜማ ነው። በአጠቃላይ የፕሮቴስታንት እምነት በታሪክ ውስጥ የሰውን ልጅ አእምሮ በዕውቀት፣ በታታሪነት እና በግል ኃላፊነት ላይ የተመሠረተ የዕድገት ጎዳና እንዲይዝ አድርጓል።

ዛዲግ አብርሃ
የአፍሌክስ ፕሬዝደንት






የጴንጤን ቸርች የምሽት ጭፈራ ክለብ እያስመሰለ ያለ ጅል ሙዚቀኛ፤ ዮሐንስ ዋቂጋሪ። ሥራኽ ይፍረስ! ስጀምር ለቸርች አንድ መጠነኛ ጊታር ከጥሩ sound system ጋር ካላት በቂ ነው። Keyboard የጴንጤ ታቦት ነው።

ሌላው ደሞ ምንወዳቸውን ዘማሪዎች ከጅሎች ጋራ አብሮ ማየት በጣም አሳዛኝ ክስተት ነው።

መሐረነ 🤨


This picture is a sobering reminder when you stop to look at these men and ask where they are now.

It was taken at the 2020 G3 Conference. Five men on one stage. Steve Lawson, John MacArthur, Voddie Baucham, Paul Washer and Josh Buice. Thousands sat in front of them that day and I doubt one person in that hall imagined what the next six years would do to that row of chairs.

Two of them have fallen. Steve Lawson, on the far left, was removed from his church and ministry in 2024 for what his elders called an inappropriate relationship with a woman, after decades of preaching holiness to the rest of us. Josh Buice, on the far right, the man who founded the very conference this picture was taken at, resigned in 2025 after confessing that he had been running anonymous accounts online to attack other believers, some of them the same men he shared this stage with. Two men, same platform, same Bibles, same doctrine, both brought down not by an enemy outside but by sin they were hiding inside.

Two of them have finished the race. John MacArthur went home to the Lord in July 2025 after more than fifty years in one pulpit. Voddie Baucham followed him in September 2025, still preaching until his body gave out. Whatever anyone thought of them, they did what Paul said at the end: "I have fought the good fight, I have finished the course, I have kept the faith" (2 Timothy 4:7). They finished.

And one of them is still running. Paul Washer, in the middle, is still preaching, still weeping over sinners, still in the race. And that is not a reason to cheer him. That is a reason to pray for him, because the two men on either side of him were still running once too.

It is a reminder that ministry is not about moments on a stage but endurance to the end. Many start well. Few finish. Every one of these five started well. Every one of them had the right doctrine, the right confession, the right books on the shelf. Doctrine did not keep two of them from falling and it will not keep you either, because "let him who thinks he stands take heed that he does not fall" (1 Corinthians 10:12) was written to people with sound doctrine.

"But the one who endures to the end will be saved" (Matthew 24:13). Not the one who starts. Not the one who gets invited to speak. Not the one whose name is on the banner. The one who endures. Look at the picture again and let it do its work on you, because you are not in the audience. You are in one of those chairs. God help us to remain faithful. Lord, keep us from falling and present us blameless before Your presence with great joy (Jude 24).

He, who has ears to hear, let him hear.

- Jeremiah Knight

- The Reformation Resurgence




ብሮ ነቃ ደንገጥ በል 🤠
We're in charge 😄


Good Christian Books Shelf dan repost
እህቶች ለትዳራችሁ the best possible ወንድ..... ወንዶችም እንዲሁ the best possible ሴት በመፈለግ ተጋደሉ🥰
አብራችሁ በአንድ ቀንበር የምትጣመሩ፥ አንዱን ተስፋ የምትወርሱ፥ አንድ መንገድ የምትሄዱ፥ ለአንድ ህልም የምትኖሩ፥ በአንድ መንፈስ እምትመላለሱ፥ በአንድ የእምነት ታዛ ስር ምትጠለሉ፥ አብራችሁ ምትጸልዩ፥ ምትንበረከኩ፥ ምትጦሙ፥ ምታመልኩ፥ የልግስና እጃችሁን ለሌሎች እምትዘረጉ፥ በመከራ፣ በደስታ ጊዜ እርስ በእርስ እምትቀባበሉ፥ በአደባባይ እምትመሰጋገኑ፥ መከባበርና መፈራራት ገንዘባችሁ የሆነ፥ ኢየሱስ የሚደሰትባችሁ ባለትዳሮች ለመሆን ዘወትር ተጋደሉ…. የጠርጡሊያን ምክር ነው ደግሞ😊


When you grow in your Christian faith, there is nothing like Christianity to discipline you. Christianity has disciplined me in many more ways than my personal trials ever could.


የሚበላና የሚለበስ ነገር ካለን፣ ከኹሉ በላይ ደሞ የቅዱሳት መጽሐፍትን በላይነት የሚታምን ቤተክርስቲያን ከአጠገባችን ካለች፤ አንዳች ነገር እንደጎደለብን በእግዚአብሔር ፊት የምናጉረመርመው እስከመቼ ድረስ ነው?

የክርስትና ሕይወት በሌለን ነገር ስለ መጨነቅ ሳይኾን ባለን ነገር ስለ መርካት ነው። በዚኽ በወደቀ ዓለም ከእግዚአብሔር ውጪ ማን አለን? ከታላቅ ፍቅሩ የተነሳ እሰማይም ብሆን ያልሰጠን ምን አለ?! ከዓለም ዘለዓለማዊ እርካታን ጠብቅን እንደኾነ የኾነ ቦታ ላይ ስተናል ማለት ነው።

#contentment


አንድን ሠርግ ደማቅ ለማድረግ የወላይታና የትግሪኛ መዝሙሮች የግዴታ አስፈላጊ ናቸው። Their rhythm hits different 😊


“ለሰው ሳያደላ በእያንዳንዱ ላይ እንደየሥራው የሚፈርደውን አባት ብላችሁ የምትጠሩት ከሆነ፣ በዚህ ምድር በእንግድነት ስትኖሩ በፍርሀት ኑሩ።”

1 ጴጥሮስ 1:17 NASV


ሕይወት በሚከብድብንና የፈተናው ማዕበል ጽኑ ሆኖ ሲሰማን፣ የሰማዩ አምላክ ፍቅርና ቸርነት ከጭንቀት በላይ ብርታት ይሰጠናል። ዓለምና ሰይጣን እስከ ጥግ ቢፈትኑንም፣ ያሰብነው ያለምነው ባይሰምር፣ የጨለማው ግርማ አያሎ ቢከበንም እንኳ እግዚአብሔር ሁልጊዜም መልካም አምላክ ነው። በብቸኝነት ስሜት ውስጥ ሆነን የተወንና የተለየን መስሎን ቢመስለንም እርሱ ከጎናችን ላፍታ አይለይም፤ በታላቅ ምህረቱና ቸርነቱ በእጁ ይይዘናል።

እግዚአብሔር ልዑላዊ አምላክ በመኾኑ፣ የእርሱን ፍጹም ሉዓላዊነትና ማሰብ የልባችንን ከባድ ሸክም ቅልል ያደርገዋል። በእርሱ ላይ ያለን መተማመን ሊናወጥ ቢችልም፣ የእርሱ የማያቋርጥ ርኽራሄና ማስተዋል ግን በጸጋ ይጠብቀናል። ስለዚኽ በችግራችን ላይ ሳይኾን በዙፋኑ ላይ ባለው ጌታ ላይ ዓይናችንን ስንተክል፣ የሰላሙ ውበት በውስጣችን ነግሶ የድካማችን ሐዘን ይጠፋል።

Our God is Sovereign!

@Christisallsufficient




Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
I'm really worried about this issue 🌒🌒


I prefer practical life reflecting my biblical theology over a purely theological life lacking practical application.

እውነተኛ እምነት ሰውን በሥራ (ተግባር) ይመራዋል።


I love this guy for real. His prophecies are always goes in opposite direction.

ከወራት በፊት ታቦር ተራራ ላይ ባሰናደው ጸሎት፤ ከንቲባውን 'ከፍታ ስትጨምር አያለኹ' አለው። ሁለት ሳምንት ሳይቆይ ከንቲባው ከሥልጣን ተባረረ።

ኤርትራም ሂዶ ነበር። አስመራ አደባባይ ላይ ወንጌል ይሰበካል፤ ክርስትና ያብባል አለ። ልክ እሱ እንደወጣ በሁለት አገራት መካከል የነበረው ግንኙነት ተቋረጠ። ክርስቲያኖች ላይም እስርና ስደት በረታ። የአየር በረራም ተቋረጠ። 😁

ዘንድሮ ደሞ 'የንግሥና ዓመት ነው' ብሏል። ወይ በሐሰት ከነገሰበት ይወድቃል፤ ወይም አዲስ መንግሥት ይመጣል። 😂


እግዚአብሔር አንድያ ልጁን ስለ ኃጢአተኞች መስዋዕት አድርጎ እስከ መስቀል ሞት አሳልፎ መስጠቱ፣ ለኃጢአት ያለውን መለኮታዊ ጥላቻና የጽድቅ መመዘኛ በምንም መልኩ አያቀልለውም። ዛሬም ቢሆን እግዚአብሔር በክፋትና በኃጢአት ላይ ያለው ጽኑ መራርነት እንደጸና ነው፤ ይልቁንም የእርሱ ቅድስና ዘለአለማዊ ነውና ሁልጊዜም ጽድቅንና እውነትን አጥብቆ ይወዳል።

ስለሆነም የእርሱ የሆኑትና በስሙ የተጠሩት ሁሉ ኃጢአትን መጥላትን፣ በጽድቅና በቅድስና መመላለስን ልክ እንደ ሕይወት መለያ የአንገት ማኅተማቸው አድርገው ሊይዙት ይገባል። ምክንያቱም ጽድቅና ቅድስና የጎደለው ክርስትና፣ ሕይወት የሌለውና የሞተ ክርስትና ብቻ ነው።

የክርስትና አፍ 'የምኖር ሕይወት' ነው!

@Christisallsufficient

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.