የኑሮ ውድነትን በዘላቂነት ለመከላከል የሚያስችለው ብቸኛው አማራጭ የስራ ዕድሎችን በማስፋትና ምርታማነትን ማሳደግ እንደሚገባ በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገለጸ።
ቋሚ ኮሚቴው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የወልቂጤ ዲስትሪክት የስራ እንቅስቃሴን በተመለከተበት ወቅት እንደገለጸው፣ የአምራች እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን አቅም በማሳደግ ምርትና ምርታማነታቸውን በመጨመር በሀገራችን የሚፈጠረውን የዋጋ ንረት በዘላቂነት መከላከል ይቻላል ብሏል።
ቋሚ ኮሚቴው፤ የወልቂጤ ዲስትሪክት በቅርበት ሆኖ ድጋፍ እና ክትትል በሚያደርግላቸው ፕሮጀክቶች ምልከታ አካሂዷል። በተደረገው የመስክ ምልከታም በቂ የሆነ ምርትና የግብዓት አቅርቦት መኖሩን መታዘቡን የገለፀ ሲሆን፣ ከስራ ዕድል ፈጠራ እና ከማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎቶች ጋር በተያያዘ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች አበረታች መሆናቸውን ገልጿል።
የውጭ ምንዛሪ እጥረትን ከመቀነስ እና ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሃገር ውስጥ መተካት የግል ባለሀብቱ የማይተካ ሚና ይጫወታል ያለው ቋሚ ኮሚቴው፤ በክልሉ የሚገኙ ባለሀብቶች ወደ ምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ምርታቸውን ለመላክ አቅደው የሚሰሩበትን ሁኔታ በቅርበት መደገፍ ይገባል ብሏል።
በኢትዮጵያ ልማት ባንክ የወልቂጤ ዲስትሪክት ስራ አስኪያጅ አቶ ጉሩሙ ዶጫ በበኩላቸው፤ ባንኩ የሚደግፋቸው አምራቾች ውጤታማ በሚሆኑበት ወቅት የባንኩም ትርፋማነት የሚጨምር መሆኑን በመረዳት፤ ተቋማቱ ለሚያጋጥማቸው ማንኛውም አይነት ችግር ፈጥኖ መፍትሔ በመስጠት እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ በመስራት ምርትና ምርታማነትን ለመጨመር እየሰራ መሆኑን አስረድተዋል።
ሁሉም የሀገሪቱ ዜጎች ባንኩ በሚሰጣቸው የልማት ስራዎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል ከወለድ ነጻ የሆነ የፋይናንስ አገልግሎትን ወደ ስራ ማስገባቱን ጠቁመው፤ ከልማት ስራው በተጨማሪ ባንኩ በተለያዩ ማህበረሰብ አቀፍ ስራዎች ግንባር ቀደም በመሆን እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡