የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ባለፉት አምስት አመታት ከሰጠው አጠቃላይ ብድር ውስጥ ከ90 በመቶ በላይ ለግሉ ዘርፍ የተሰጠ መሆኑን የባንኩ ፕሬዝዳንት ዶ/ር እመቤት መለሰ አስታወቁ፡፡
ዶ/ር እመቤት ይህን ያስታወቁትት የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ለአምራች ኢንዱስትሪው ያመጣውን መልካም ዕድል፣ ተግዳሮቶች እና መፍትሄዎች ላይ ያተኮረ የመንግስት እና የግሉ ዘርፍ የጋራ የምክክር መድረክ በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አዘጋጅነት በተካሄደበት ወቅት ነው፡፡
በምክክር መድረኩ የተሳተፉት ዶ/ር እመቤት መለሰ የኢትዮጵያ ልማት ባንክን በተመለከተ ለቀረቡት ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
ከተነሱ ጥያቄዎች መካከልም ባንኩ የበለጠ ወደ ደንበኞች ቀርቦ የቴክኒክ እገዛ ቢያደርግ እና ብድር ለመውሰድ የሚፈጀው ጊዜ እንዲያጥር ቢደረግ የሚሉት ይገኙበታል፡፡
ዶ/ር እመቤት በሰጡት ማብራሪያ ደንበኞች ወደ ባንኩ ከመምጣታቸው በፊት ከባለድርሻ አካላት አሟልተው ማቅረብ ያለባቸውን ማስረጃ ባለማቅረባቸው የሚፈጠር እንጂ በባንኩ ረጅም ጊዜ እንዲወስድ እንደማይደረግ ገልጸዋል፡፡
በኢትዮጵያ የተጀመረው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራን በተመለከተም ባንኩ ለደበኞቹ ተገቢውን የጥሬ ዕቃ መግዣ የውጭ ምንዛሬ በመስጠት ላይ እንደሚገኝም ዶ/ር እመቤት አስታውቀዋል፡፡
የምክክር መድረኩን የከፈቱት የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል በበኩላቸው መንግስት የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉን ለመደገፍ በርካታ ስራዎችን እንደሚሰራ አመላክተው በግሉ ዘርፍ የሚመራ እና የመንግስት ሚና በግልጽ የተለየበት የአምራች ኢንደስትሪ መፍጠር ላይ በትኩረት ይሰራል ብለዋል፡፡
በምክር መድረኩ የተለያዩ ተቋማት የስራ ኃላፊዎች፣ባለድርሻ አካላት እና ባለሃብቶች ተሳታፊዎች ነበሩ።