የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከአዲስ ቻምበር የስልጠና ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ሴቶችን ለአመራርነት ለማብቃት የሚያስችል ሥልጠና ለባንኩ ሴት ባለሙያዎችና መሪዎች ሰጥቷል፡፡
ትኵረቱን በጾታ ልማት እና አስተዳደር ላይ በማድረግ ከባንኩ ዋና መስሪያ ቤት፣ ዲስትሪክቶች እና ቅርንጫፎች ለተውጣጡ ሴት ባለሙያዎችና አመራሮች የተሰጠው ሥልጠና ከወራት በፊት የተሰጠው ተመሳሳይ ሥልጠና ሁለተኛው ዙር መሆኑንም ባንኩ አስታውቋል፡፡
የሴት አመራሮችን የመሪነት ክህሎት ለማሳደግ በተሰጠው በዚህ ሥልጠና የተሻለ ሥራ ለመሥራትና ከፍተኛ ኃላፊነትን መወጣት የሚያስችል ወኔ እንዲሰንቁ እንዳስቻላቸው ሠልጣኞቹ ገልጸዋል፡፡
ከሥልጠናው ተሳታፊዎች መካከል የወልቂጤ ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ ወይዘሮ ልደት አጥናፉ ባንኩ የሴቶችን ጉዳይ ቦታ ሰጥቶ ይህን ስልጠና ማዘጋጀቱ ጥሩ ጅምር መሆኑን ገልጸው ባንኩን በተሻለ እውቀት ለማገልገል ስልጠናው የራሱ አስተዋጽዖ እንዳለው አመላክትዋል፡፡ ባንኩም ሴቶችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ምቹ ሁኔታዎችን እንዲፈጥር የጠየቀች ሲሆን በተለይ የሚወጡ ፖሊሲዎችና ስትራቴጅዎች በሴት እይታም የተቃኙና ሴቶችን ያካተቱ እንዲሆኑ ጠይቀዋል፡፡
በሥልጠናው ከተሳተፉ ዲቪዥን ኃላፊዎች መካከል አንዷ የሆኑት ወይዘሮ ትርንጎ ግስላ በባንኩ ውስጥ የሴቶችን ጉዳይ በተሻለ መዋቅራዊ ሁኔታ እንዲሠራ መወያየታቸው በመግለጽ ስልጠናው ችላ ያልናቸውን ጉዳዮች የበለጠ ትኩረት እንድንሰጣቸው አግዞናል ሲሉ አብራርተዋል፡፡
ሥልጠናውን የሰጡት ዶ/ር ቃልኪዳን ኢሳያስ በበኩላቸው ስልጠናው የባንኩ ሴት አመራሮች የተሻለ ደረጃ ላይ እንዲደርሱ፣ ያላቸውንም አቅም አውጥተው እንዲጠቀሙ እና ለባንኩ የተሻለ አስተዋጽዖ እንዲያደርጉ እንደሚያግዝ ገልጸዋል፡፡
ሌሎች እድሉን ያላገኙ ሴቶች እድሉ እንዲሰጣቸው እና ሥልጠናውን የወሰዱ ሴቶች ያገኙትን እውቀት ተጠቅመው ለባንኩ የተሻለ አስተዋጽዖ እንዲያበረክቱ ባንኩ እድሉን እንዲያመቻችም ጠቁመዋል፡፡
ሠልጣኞቹ ረጅም ዓመት ያገለገሉና በቂ የተግባር ዝግጅት ያላቸው መሆናቸውን የጠቀሱት ዶ/ር ቃልኪዳን ስልጠናው መሰጠቱ የበለጠ ችሎታቸውን እንዲያወጡ ያስችላል ያሉ ሲሆን ባንኩ የያዘውን እቅድ እውን እንዲያደርግ የአመራር ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ሴቶች ወደ አመራር ቢመጡ የሚፈለገው ውጤት እንዲመጣ ስልጠናው መሰጠቱ የራሱ ጉልህ ሚና ይጫወታል ብለዋል፡፡
መሰል ስልጠናዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የገለጹት የስልጠና ክፍል ዲቪዥን ሀላፊ አቶ ይታገሱ ሶሬሳ በበኩላቸው የስልጠናው ዋና ዓላማ የሴቶችን አቅም መገንባት እና ኔትዎርክ መፍጠር መሆኑን ጠቁመዋል፡፡