የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በግማሽ ዓመቱ የዕቅድ አፈጻጸም በብድር መሰብሰብ ዘርፍ ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገቡን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ አስታወቀ፡፡
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ፣ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት እና የማኔጅመንት አባላት የባንኩን የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት የዕቅድ አፈጻጸም በገመገሙበት መድረክ በብድር መሰብሰብ ዘርፍ ባንኩ ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገቡ ተጠቅሷል፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል የሆኑት አቶ ፍቃዱ ሆረታ ባንኩ በለውጥ ላይ መሆኑን እና የተለያዩ አሰራሮችን በመቅረጽ ተግባራዊ ለማድረግ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን አንስተዋል፡፡
የባንኩ የስድስት ወራት አፈጻጸም በብድር መሰብሰብ ሂደት ከምንጊዜውም የላቀ አፈጻጸም ማስመዝገቡ የሚደነቅ መሆኑን የገለጹት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሀብታሙ ኃይለ ሚካኤል ደግሞ ይህንን ለማስቀጠል ባንኩ የበለጠ እንዲሰራ አሳስበዋል፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ዶ/ር እመቤት መለሰ በበኩላቸው ለባንኩ እየቀረቡ ያሉ ሰፊ የብድር ጥያቄዎችን መመለስ የሚቻለው ሀብት ማሰባሰብ ላይ አተኩሮ መሥራት ሲቻል በመሆኑ የሚገኘው ሀብት ስትራቴጂክ በሆኑ ዘርፎች ላይ በጥንቃቄ ተመዝኖ የሚሰጥ እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡
በመጨረሻም አቶ ሀብታሙ ባለፉት 6 ወራት ባንኩ ግልጽ የሆኑ አሰራሮችን ለመዘርጋት እያደረገ ያለው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን በመገለጽ ይኽው ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል ይገባዋል ብለዋል፡፡