በቅርቡ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ሆነው የተሾሙት ዶ/ር እመቤት መለሰ ለባንኩ የሥራ መሪዎች ትውውቅ አደረጉ፤ የሥራ መመሪያም ሰጡ፡፡
ጥቅምት 7 ቀን 2017 ዓ.ም በባንኩ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ከባንኩ ዋና መስሪያ ቤትና ከዲስትሪክት ኃላፊዎችን ባነጋገሩበት መድረክ ከየሥራ ኃላፊዎቹ ጋር ትውውቅ ያደረጉ ሲሆን፣ እያንዳንዱ የሥራ መሪ በተሰጠው ሥራና ኃላፊነት መሠረት ሥራው በምን ደረጃ ላይ እንዳለ ገለፃ በማቅረብ የትውውቅ መርሃ ግብሩ የተከናወነ ሲሆን፣ የባንኩን ርዕይ ከማሳካት አንጻርና ወደተሻለ ሽግግር ለመሄድ በትኩረት ለመስራት ዝግጁ እንደሆኑም ለፕሬዚዳንቷ አቅርበዋል፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ዶክተር እመቤት መለሰ በበኵላቸው እያንዳንዱ ሠራተኛና የሥራ ኃላፊ በባንኩ ውስጥ የሚሠራበትን ዓላማና ድርሻ ለማበርከት ኃላፊነት እንዳለበት አውቆ ስትራቴጂክ አመራረርን ለማስፈን መንቀሳቀስ እንዳለበት አሳስበው በሀገራችን ብቸኛ የሆነውን የፖሊሲ ባንክ ውጤታማ በማድረግ ሀገር የምትፈልገውን ልማት ለማረጋገጥ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
ለዚህም በታማኝነት፣በቅንነት፣ መሥራት፣ የሙያ ብቃትን በማሳየት ሥራን መወጣት፣ የጋራ አመራር በመስጠት ራስን ሙያው ለሚጠይቀው ዲስፕሊን በማስገዛት እና በኃላፊነት መንፈስ ተግባራቶቻችንን መወጣት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡ ለዚህም ተቋማዊ አመራርና ኃላፊነትን ለመወጣት የሚያስችሉ በሂደት ላይ ያሉ የተለያዩ ፖሊሲዎች እና መመሪያዎች ፀድቀው በአጭር ጊዜ ወደ ሥራ ማስገባት፣ የአቅም ግንባታ ሥራዎችን በመስራትና የተጓደሉ የሰው ኃይል ቦታዎችን በፍጥነት ማሟላላ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራም አብራርተዋል፡፡ በቀጣይም በሁሉም አካባቢዎችና በዋና መስሪያ ቤት ደረጃ ከሚገኙ እና በየደረጃው ካሉ ሰራተኞች ጋር ውይይት እንደሚያደርጉ ፕሬዚዳንቷ አብራርተዋል።