ኢትዮጵያ ልማት ባንክ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ለነበሩት ለዶ/ር ዮሐንስ አያሌው ሽኝትና የአዲሷ ፕሬዝዳንት ዶ/ር እመቤት መለሠ የአቀባበል ስነ ስርዓት ተካሄደ፡፡
ስነ ስርዓቱ የተካሄደው ጥቅምት 23 ቀን 2017 ዓ.ም በስካይላይት ሆቴል ሲሆን፣ በስነ ስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ዶ/ር እመቤት መለሠን ጨምሮ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ምክትል ሰብሳቢና የግብርና ሚኒስቴር ሚንስትር ዶ/ር ግርማ አመንቴና የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት የመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር የስራ ኃላፊዎች የባንኩ የስራ አመራር አባላት፣ዳይሬክተሮችና የሰራተኛ ማህበር አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
መርሃ ግብሩን በንግግር የከፈቱት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ዶ/ር እመቤት መለሠ ባስተላለፉት መልእክት ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው ባንኩን ፕሬዚዳንት ሆነው በመሩባቸው ዓመታት ላበረከቱት መልካም ተግባር አመስግነው ወደፊት ከባንኩ ጎን በመሆን እንደሚያግዙ ያላቸውን እምነት ገልፀዋል፡፡
ዶክተር እመቤት አክለውም በአመራር መተካካት ሒደት የስራ ጊዜያቸውን ጨርሰው የሚሄዱ የስራ መሪዎችን አመስግኖ መሸኘት እንደ ባህል መወሰድ ያለበት መልካም ተግባር ነውም ብለዋል፡፡
ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው ባለፉት 30 ዓመታት በትላልቅ የማክሮ ኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች ላይ ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳበረከቱ አስታውሰው በቀሪ ዘመናቸውም መልካም የስራ ጊዜ እንዲሆንላቸውም ተመኝተዋል።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ምክትል ሰብሳቢና የግብርና ሚኒስቴር ሚንስትር ዶ/ር ግርማ አመንቴ በበኩላቸው እንደዚህ ዓይነት የምስጋና እና የሽኝት መርሃ ግብር ባንኩ ማካሄዱ በጣም አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰው ትላንት ከሌለ ዛሬ ሊኖር አይችልም፤ ዛሬ ከሌለ ደግሞ ነገ የለም ከትላንት ሁልጊዜ መልካም ነገሮችን መውሰድ እና ትላንት ውስጥ ያሉትን መልካም ነገሮች ይዞ መቀጠል ይገባል ብለዋል።
ሚንስትሩ አክለውም የነበሩ አመራሮች የራሳቸውን አሻራ፣ የራሳቸው ተፅኖ፣ የራሳቸውን አስተዋፅኦ አበርክተው አልፈዋል፤ ዶ/ር ዮሐንስ አያሌውም በተመሳሳይ ባለፉት ዓመታት አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበረን ባንክ በመምራት ሂደት ውስጥ ከነበረው ስራ አመራር ቦርድ ጋር የራሳቸውን አሻራ ጥለው አልፈዋል ለዚህም ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል፡፡
አሁን በያዙት ኃላፊነትም መልካም የስራ ዘመን እንዲገጥማቸውም መልካም ምኞታቸውን ተመኝተዋል፡፡
በተመሳሳይ ዶ/ር ግርማ አመንቴ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ሆነው ለተሾሙት ለዶ/ር እመቤት መለሠ የእንኳን ደህና መጡ መልእክታቸውን አስተላልፈው፡፡
አዲሷ ፕሬዝዳንት በባንኩ ዘርፍ ትልቅ አቅምና ብቃት ያላቸው የስራ መሪ በመሆናቸው ወደ ኢትዮጵያ ልማት ባንክ በፕሬዝደንትነት መምጣታቸው ለባንኩ ትልቅ እድል ነው ብለዋል፡፡
የመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ተወካይ አቶ ሰዋገኝ ጫኔ ባስተላለፉት መልእክት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ትልቅ ተግዳሮት ገጥሞት የነበረ ባንክ እንደመሆኑ ችግሮችን ተቋቁሞ ከብዙ እልህ አስጨራሽ ትግል በኋላ አሁን ላለበት ቁመና እንዲበቃ የዶ/ር ዮሐንስ አያሌው እና የባንኩ የስራ አመራር ቦርድ ሚና ከፍተኛ እንደነበረ ገልጸዋል፡፡
በመሆኑም ለዚህ አስተዋጽ ድርሻ ለነበራው የቀድሞው ፕሬዝደንት ባንኩ የምስጋና እና የሽኝት መርሃ ግብር ማዘጋጀቱ የሚያስመሰግን ነው ብለዋል፡፡
ከምስጋናና የሽኝት መርሃ ግብሩ በኋላ ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው ባደረጉት ንግግርም ስለተሰጣቸው እውቅና አመስግነዋል፡፡
ባንኩ ጠንካራ ክህሎት እና ቆራጥነትን የሚያሳይ አመራር ያለው ስለሆነ አዲሷ ፕሬዝዳንት ዶ/ር እመቤት መለሰ ውጤታማ እንደሚሆኑ ያላቸውን መልካም ምኞት ገልፀዋል፡፡