ይህ ደብዳቤ የተዘጋጀው ለሚዲያ ተቋማት ስለ ዩንቨርስቲያችን የፊልድ ክልከላ ቅሬታ ለማቅረብ ነው።
ውድ ቲክቫህ ሚዲያ
በዚህ ደብዳቤ በዩንቨርስቲያችን የትምህርት እድል መከልከል ላይ ያለንን ቅሬታ ለማቅረብ እንፈልጋለን።
እንደሚታወቀው ዲላ ዩኒቨርሲቲ ሀገራችን ላይ ካሉ መሰል ዩኒቨርሲቲዎች ግንባር ቀደምና የመልካም ስም ባለቤት መሆኑ እርግጥ ነው። በአረንጓዴ ከባቢው የሚታወቀው ዲላ ዩኒቨርሲቲ ብቁና የተማረ ማህበረሰብ በማፍራት የራሱን ሚና ተወቷል አየተወጣም ይገኛል።
ነገር ግን በቅርብ ጊዜ በዩንቨርስቲያችን የተደረጉ የፖሊሲ ለውጦች እና የትምህርት እድል መከልከል በተማሪዎች ላይ ትልቅ አሉታዊ ተፅእኖ አሳድሯል።
በዘንድሮው የመማር ማስተማር ሂደት እኛ የአንደኛ አመት Freshman ተማሪዎች የአንደኛ ሴሚስተር ትምህትን ካገባደድን እና ለፊልድ መረጣ እየተዘጋጀን ባለንበት ሰዓት Pre-engineering (Civil engineering, Computer science, Electrical engineering, Food engineering, Architecture, COTM...) ዘንድሮ እንደማይሰጡ ተነግሮናል።
ይሄም ለተማሪው አስደንጋጭና ተስፋ አስቆራጭ ነገር ነበር። ይሄ ነገር ለምን እንደተፈጠረ ባለድርሻ አካላትን ለመጠየቅ ብንሞክርም ማንም በቂ ምላሽ ሊሰጠን አልቻለም። ፊልድ መረጣውም በ online እንደሚከናወንና እስከ እሁድ (የካቲት 23/2017) ብቻ እንደሚቆይ አሳውቀውናል ይሄም ትልቅ አጣብቂኝ ውስጥ እንድንገባ ዳርጎናል። Pre-engineering ውስጥ ያሉ ዲፓርትመንቶች የአብዛኛው የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ፍላጎት እንደሆኑ ይታወቃል በመሆኑም ይህ ምክንያት አልባ እና ድንገተኛ ጉዳይ ተማሪው ላይ ግራመጋባትና እና ትልቅ ጭንቀት ፈጥሯል።
ስለዚህ ይህ ችግር ላይ ትኩረት እንዲሰጥ እና አፋጣኝ እርምጃ እንዲወሰድ ሚዲያው እንዲረዳን በአክብሮት እንጠይቃለን።