መዝሙር -የእግዚአብሔር ፋሲካ
በእህት ኤልሳቤጥ በቀለ
የእግዚአብሔር ፋሲካ የታረድከው ጠቦት
ደምህን አፍስሰህ ኪዳኔን የመረቅህ
ሁሌ አከብርሃለው ሞትህን እያሰብኩ
ሁሌ አመልክሃለሁ መዳኔ እያሰብኩ
ሁሌ አከብርሃለው ሞትህን እያሰብኩ
ሁሌ አመልክሃለሁ ሞቴን ስለወሰድክ
በግርፋት ብዛት ኢየሱስ አልሞትክም
አጥንትህን ሰብሮ ሰው አልገደለህም
ስልጣንም የላቸው ነፍስህን ሊወስዷት
አንተው በፍቃድህ ራስህ ነህ የተውካት
በደምህ ሆንክልኝ የሃጢያት ስርየቴ
ታረድክ ፋሲካዬ ከሰረ እርግማኔ
ነውር የሌለበት አንድያውን ጠቦት
ወስደው ይረዱት ለአባታቸው ቤት
በሚበሉት መጠን ይብሉ ከጠቦቱ
በደሙ ይቀባ መቃኑ ጉበኑ
አንዳች ሳያስቀሩ በቶሎ እንዲበሉ
ከሆድ እቃው ጋራ ከራሱ ከጭኑ
እንደሚል መፃፉ
የሚጣል የለውም የአካል ክፍልህ
ተፈትነህ ያለፍክ ከሀጢያት በቀር
ከሰማይ የወረድክ የእግዚአብሔር በግ
ጣፋጭ ነህ ኢየሱስ ሳላስቀር ልብላህ
በመግቢያ በር ላይ ከልካይ አላቆመም
ኢየሱስ ያልሞተለት የቀረ ሰው የለም
መጋረጃው ከላይ እስከ ታች ተቀዷል
በኢየሱስ በኩል ወደ አብ ይደርሳል
ብርሃን ፈነጠቀ በጨለማ ላለ
መጽደቅ ተፈቀደ ጻድቁን ላመነ
መድሃኒት ተሰጥቷል መዳኑን ለሚሻ
አለት ተሰንጥቋል እንዲሆን መሸሻ
@DawitFassilMinistry
በእህት ኤልሳቤጥ በቀለ
የእግዚአብሔር ፋሲካ የታረድከው ጠቦት
ደምህን አፍስሰህ ኪዳኔን የመረቅህ
ሁሌ አከብርሃለው ሞትህን እያሰብኩ
ሁሌ አመልክሃለሁ መዳኔ እያሰብኩ
ሁሌ አከብርሃለው ሞትህን እያሰብኩ
ሁሌ አመልክሃለሁ ሞቴን ስለወሰድክ
በግርፋት ብዛት ኢየሱስ አልሞትክም
አጥንትህን ሰብሮ ሰው አልገደለህም
ስልጣንም የላቸው ነፍስህን ሊወስዷት
አንተው በፍቃድህ ራስህ ነህ የተውካት
በደምህ ሆንክልኝ የሃጢያት ስርየቴ
ታረድክ ፋሲካዬ ከሰረ እርግማኔ
ነውር የሌለበት አንድያውን ጠቦት
ወስደው ይረዱት ለአባታቸው ቤት
በሚበሉት መጠን ይብሉ ከጠቦቱ
በደሙ ይቀባ መቃኑ ጉበኑ
አንዳች ሳያስቀሩ በቶሎ እንዲበሉ
ከሆድ እቃው ጋራ ከራሱ ከጭኑ
እንደሚል መፃፉ
የሚጣል የለውም የአካል ክፍልህ
ተፈትነህ ያለፍክ ከሀጢያት በቀር
ከሰማይ የወረድክ የእግዚአብሔር በግ
ጣፋጭ ነህ ኢየሱስ ሳላስቀር ልብላህ
በመግቢያ በር ላይ ከልካይ አላቆመም
ኢየሱስ ያልሞተለት የቀረ ሰው የለም
መጋረጃው ከላይ እስከ ታች ተቀዷል
በኢየሱስ በኩል ወደ አብ ይደርሳል
ብርሃን ፈነጠቀ በጨለማ ላለ
መጽደቅ ተፈቀደ ጻድቁን ላመነ
መድሃኒት ተሰጥቷል መዳኑን ለሚሻ
አለት ተሰንጥቋል እንዲሆን መሸሻ
@DawitFassilMinistry