" እንዲለቀቅ ይጠይቃሉ ወይስ ምላሳቸውን ውጠው ጸጥ ይላሉ ? " - ዛራኮቫ
የምዕራባውያኑ ለሰብዓዊነትና ነጻነት ቆመናል የሚሉ ድርጅቶች የቴሌግራም መስራች ፓቨል ዱሮቭ እንዲለቀቅ ይጠይቃሉ ?
የዱሮቭን ፈረንሳይ ውስጥ መታሰረን በመለተከተ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች " ምላሳቸውን ውጠው ዝም ይላሉ ? ወይስ እንዲፈታ ይጠይቃሉ ? " ብለዋል።
እ.ኤ.አ. በ2018 ፦
- ሂዩማን ራይትስ ዎች ፣
- አምነስቲ ኢንተርናሽናል ፣
- ፍሪደም ሃውስ ፣
- ድንበር የለሽ ሪፖርተሮች እና ሌሎችን ጨምሮ 26 መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ቡድን የሩስያ ፍርድ ቤት ቴሌግራምን ለማገድ የሰጠውን ውሳኔ አውግዘው ነበር ሲሉ አስታውሰዋል።
ዲፕሎማቷ ፤ " አሁን ፓሪስ ደውለው የዱሮቭን መፈታት የሚጠይቁ ይመስላችኋል ? ወይስ ምላሳቸውን ውጠው ዝም ይላሉ ? " ሲሉ በቴሌግራም ቻናላቸው ላይ ፅፈዋል።
ዛራኮቫ ፤ በ2018 ቴሌግራም ላይ የሕግ አውጭ ቅሬታዎች ነበሩ፣ ይህም በብዙ የኢንክሪፕሽን ሥርዓቱ ቴክኒካል መለኪያዎች ምክንያት ነው ሲሉ አስታውሰው ፤ ዱሮቭ ግን ነፃ ሆኖ መቆየቱን መተግበሪያውን ማሳገዱን ገልጸዋል።
የዱሮቭ በተያዘበት ቅፅበት በፈረንሳይ የሩስያ ኤምባሲ ጉዳዩን መከታተል እንደጀመረ ጠቁመዋል።
" የእኛን ዲፕሎማቶች ስለ ስራቸው ማስታወስ አያስፈልግም " ሲሉም ዛካሮቫ አክለዋል።
ቴሌግራም ሩስያ እንዲሁም በዩክሬን አካባቢ እጅግ ከፍተኛ ተጠቃሚ ያለው ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ባለስልጣናትም ተመራጭ መልዕክት መለዋወጫ አድርገውታል።
ዱሮቭ የሩስያ እና የፈረንሳይ ዜግነት አለው።