እናት ባንክ በበጎአድራጊዋ ወይዘሮ ነፃነት መንግሥቱ ስም የሰየመችውን የካራቆሬ ቅርንጫፍ በዛሬው እለት አስመረቀች፡፡
የሴቶችን የኢኮኖሚ አቅም እያጎለበትና ለሁሉም ማህበረሰብ ዘመናዊ የባንክ አገልግሎት እየሰጠች የምትገኘው እናት ባንክ፣ በአገር ውስጥና በዐለም አቀፍ ተቋማት ሀገራቸውንና ህዝባቸውን በማገልገል በበጎ አድራጎት ሥራቸውና በታታሪነታቸው በሚታወቁት በወይዘሮ ነፃነት መንግሥቱ ስም የካራቆሬ ቅርንጫፍን ሰይማ በይፋ አስመርቃለች፡፡
ወይዘሮ ነፃነት መንግሥቱ በኢትዮጵያና በአለምአቀፍ ተቋማት በአመራርነት ደረጃ ሀገርንና ህዝብን በማገልገል፣ ግብረ-ሠናይ ድርጅትን በማቋቋም የሴቶች ተጠቃሚነት በማጎልበትና ከጥቃት በመከላከል እንዲሁም በኢኮኖሚ ዘርፍ ማይክሮ ፋይናንስ ድርጅት በማቋቋም አመራር በመስጠት ሴቶችን በኢኮኖሚ ተጠቃሚ በማድርግ ሳይታክቱ በመሥራት ለብዙዎች ዓረአያ መሆን የቻሉ ሴት ናቸው፡፡
በትምህርቱ ዘርፍ ትምህርት ቤት በመገንባትና ቁሳቁስ በማሟላት ሴቶች በአቅራቢያቸው የትምህርት ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማድረግ ብዙ የተማሩ ሴቶችን ማፍራት ችለዋል፡፡በምርቃትሥነ-ርዓቱ፣የእናት ባንክ ከፍተኛ አመራሮች፣ሰራተኞችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ሲሆን፣የባንኳ ከፍተኛ አመራሮች ባደረጉት ንግግር፣ እናት ባንክ አገራቸውና ህዝባቸውን በቅንነት በማገልገል ተምሳሌት በሆኑ እናቶች ስም የባንክ ቅርንጫፍ በመሰየም እውቅና መስጠቷን መቀጠሏን ተናግረዋል፡፡
እናት ባንክ የተቋቋችበትን የሴቶችን የኢኮኖሚ አቅም በማጎልበትና ለሁሉም የማህበረሰብ ክፍሎች ዘመናዊ የባንክ አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድርግ የሚያስችሉ ቅርንጫፎችን ተደራሽ በማድረግና የዲጂታል ባንክ አገልግሎትበመስጠት በባንክ ኢንዱስትሪው ተወዳዳሪነቷን እያሳደገች መምጣቷን ገልፀዋል፡፡