ማስታወቂያ
ለየመግቢያ ፈተና ለመፈተን ብቁ ለሆናችሁ የሲቪል አመልካቾች በሙሉ።
በ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ከሲቪል በፖሊስ ሳይንስ የመጀመሪያ ዲግሪ (BA Degree in Police Science) እና በዲጂታል ፎረንሲክ ድህረ-ምረቃ ሰርቲፊኬት ፕሮግራሞች ለመማር ተመዝግባችሁ ለመግቢያ ፈተና ለተመረጣችሁ የሲቪል አመልካቾች በሙሉ፦
ከዚህ በታች በተጠቀሰው ይፋዊ የቴሌግራም ሊንክ ስማችሁን በመመልከት፣ በተመደባችሁበት የፈተና ማዕከል በመገኘት የኦሬንቴሽን እና የፈተና ሂደቱን እንድታጠናቅቁ እንገልጻለን።
🔗 የስም ዝርዝር ለማየት፦
https://t.me/Epupage/6877?singleማሳሰቢያ
አመልካቾች የተጠቀሱትን ቀናትና ሰዓታት በጥብቅ በመጠበቅ፣ አስፈላጊውን የትምህርት ማስረጃ ዋናውን (Original) እና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ፣ ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ፣ እንዲሁም ከምትኖሩበት ፖሊስ ጣቢያ ከወንጀል ነፃ መሆናችሁን የሚገልጽ ማስረጃ በመያዝ በተመደባችሁበት የፈተና ማዕከል በሰዓቱ እንድትገኙ እናሳስባለን።