Ethio Digital Skills


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Ta’lim


ኢትዮጵያ ዉስጥ ስለሚገኙ ሁሉም ዩኒቨርሲቲወች እና ኮሌጆች ትክክለኛ መረጃወችን የምታገኙበት ቻናል ነው!!! You tube channel 👇

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


ኢንተርኔትን ስንጠቀም ልንጠነቀቅ የሚገቡን 10 ጉዳዮች

1. የግል መረጃችንን ከማጋራት መቆጠብ፤

2. የምናውቃቸውን ሰዎች ብቻ ማነጋገር

3. በኦንላይን ብቻ የምናውቃቸውን ሰዎች ከፍተኛ እምነት አለመጣል፤

4. የጓደኝነት ጥያቄን በአካል ከምናውቃቸው ሰዎች ብቻ እንቀበል፤

5. ሁልጊዜ ስለምንለጥፈው ነገር በጥንቃቄ ደጋግሞ ማንበብ

6. በሁሉም የማህበራዊ ሚዲያ መለያዎች ላይ የግላዊነት(privacy 🔏) መጠበቂያዎችን መጠቀም፤

7. ሁሉም ሰው በኦንላይን እሱ እንደሆነ የሚነግረን ሁሉ እውነት አድርጎ አለመቀበል፤

8. ከጓደኞቻችን እና ከቤተሰባችን ጋር ስንመለከታቸው ምቾት የሚሰጡንን ምስሎች ብቻ ማጋራት፤

9. የይለፍ ቃላችንን በፍጹም ከማጋራት መቆጠብ

@EthioDigitalskills


ቻይና የኤአይ(Ai) ባለሙያዎቿ ወደ አሜሪካ እንዳይጓዙ አገደች

የዓለም ቴክኖሎጂ የበላይ ለመሆን ብርቱ ፉክክር ላይ የሚገኙት አሜሪካ እና ቻይና አሁን ደግሞ ፉክክራቸው ወደ ኤአይ ዞሯል፡፡

እገዳው የተጣለው ምዕራባዊን ሀገራት የቻይና ባለሙያዎችን አስረው ሊደራደሩ ይችላሉ ተብሏል።

የዲፕሲክ ኤአይ ሞዴል መስራች በቅርቡ በፓሪስ በተካሄደው የኤአይ(Ai) ጉባኤ ላይ እንዲገኝ ቢጋበዝም በፍራቻ ምክንት ሳይገኝ ቀርቷል ተብሏል

@EthioDigitalskills




በ2017 Entrance ፈተና ላይ ከ 10ኛ እና 11ኛ ክፍል የሚካተቱ ምዕራፎች / Common Units for grade 10 and 11 for entrance👇👇👇

https://youtu.be/qqOW0KAFVyI


ከዚህ ቀደም 10ኛ ክፍልን በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት የተማሩ ተማሪዎች ፈተናዉ የሚዘጋጀዉ በሁለቱ ሥርዓተ ትምህርት ውስጥ ከሚገኙ የጋራ የሆኑ ጥያቄዎች ይዘጋጃል👇👇👇

https://youtu.be/H9Y51G_7dxw


ያነበብነውን አየረሳን ለተቸገርን ተማሪዎች መፍትሔ

https://youtu.be/SGtHq2Q6OCo




#Exit_Exam_Result

ሀገር አቀፍ የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ውጤት ተለቋል።

https//:result.ethernet.edu.et ላይ በመግባት ExitExam የሚለውን በመምረጥና የራስዎን User Name በማስገባት ውጤትዎን መመልከት ይችላሉ።

በ2017 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት የመውጫ ፈተና ከጥር 26-30/2017 ዓ.ም መሠጠቱ ይታወቃል።

@EthiopianUniversitystudents1


ሀገር አቀፍ የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራም የመውጫ ፈተና ዛሬ ይጠናቀቃል።

ፈተናው 5ኛ ቀኑ ላይ የሚገኝ ሲሆን፤ በዛሬው የጠዋት 2:30 መርሐግብር የነርሲንግ ፈተና እየተሰጠ ነው።

በጁምዓ ምክንያት ጠዋት 5፡30 የሚጀመረው የመውጫ ፈተና ወደ 7፡30 እንዲሁም ከሰዓት 8፡30 የሚጀመረው ፈተና ወደ 10፡30 ተቀይሯል።

የመውጫ ፈተና መጠናቀቅን ተከትሎ በሚኖሩ ቀጣይ ቀናት ውጤት እንደሚገለፅ ይጠበቃል።

በሌላ በኩል በመምህርነት ሙያ ከዲፕሎማ ወደ መጀመሪያ ዲግሪ የትምህርት ደረጃ ማሻሻያ ስልጠና በክረምት መርሐግብር ሲከታታሉ የቆዩ #መምህራን የመውጫ ምዘና ነገ ቅዳሜ የካቲት 1/2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ መገለፁ ይታወቃል።

ምስል፦ ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ

@EthiopianUniversitystudents1


#Update

ነገ አርብ ጥር 30/2017 ዓ.ም በሚሰጡ የመውጫ ፈተና ላይ የሰዓት ለውጥ መደረጉን የተወሰኑ ዩኒቨርሲቲዎች እየገለፁ ነው፡፡

በዚህም ጠዋት 5፡30 ይጀምር የነበረው ፈተና ወደ ከሰዓት 7፡30 እንዲሁም ከሰዓት 8፡30 ይጀምር የነበረው ፈተና ወደ 10፡30 የተሸጋሸገ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ምስል፦ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ፣ ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ፣ ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ እና ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ

@EthiopianUniversitystudents1


የ2017 ኢንትራንስ ፈተና ዝግጅት ምን ይመስላል❓

https://youtu.be/7hSs-PTJyvs


Freshman Tricks dan repost
የ ጤና እና የ ኢንጂነሪንግ ዲፓርትመንቶች ንፅፅር / Health Bs Engineering Departments comparison 👇👇👇

https://youtu.be/JQRlyHMGJpM


#ExitExamSchedule #AAU

ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ከሰኞ ጥር 26/2017 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሰጥ ይታወቃል፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተና ለመፈተን የተመዘገባችሁ የፈተናው የመጀመሪያ ሁለት ቀናት መርሐግብር (ጥር 26 እና 27/2017 ዓ.ም) ከላይ ተያይዟል።

@EthiopianUniversitystudents1


#ExitExam

176 ሺሕ ተማሪዎች የመውጫ ፈተናን ለመውሰድ መመዝገባቸው ተገለጸ

👉ፈተናው ከጥር 26 እስከ 30 ድረስ ይሰጣል

ጥር 23/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በ2017 ዓ.ም አጋማሽ ላይ የሚሰጠውን የቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና ለመውሰድ 176 ሺሕ ተማሪዎች መመዝገባቸውን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

ፈተናውን በድጋሚ የሚወስዱትን ጨምሮ በጠቅላላው 176 ሺሕ ተማሪዎች የመውጫ ፈተናውን ይወስዳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ በትምህርት ሚኒስቴር የአካዳሚክ ጉዳዬች መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ኤባ ሚጀና #ለአሐዱ ገልጸዋል።

በዚህም መሰረት በኢትዮጵያ የሚገኙ በሁሉም የኒቨርሲቲዎች ፈተናው የሚሰጥ ሲሆን፤ ተጠሪነቱ ለትምህርት ሚኒስቴር ያልሆነው የመከላከያ ዩኒቨርሲቲ ጭምር በዚህ ፕሮግራም ተካታች መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

የግል ኮሌጆችን በሚመለከት አሐዱ ላቀረበላቸው ጥያቄ ትምህርት ሚኒስቴር የግል ኮሌጆች ላይ ገብቶ ለመፈተን የሚያስችል መዋቅር እንደሌለው በማንሳት፤ ነገር ግን ተማሪዎች በአቅራቢያቸው በሚገኝ የመንግስት ተቋም በኩል መፈተን እንደሚችሉ ገልፀዋል።

የፈተና ቀኑ በተለያዩ ምክንያቶች ዘግይተው ትምህርት የጀመሩትን ዩኒቨርሲቲዎች ታሳቢ ያደረገና በቂ ዝግጅት ማድረጋቸው ከተረጋገጠ በኋላ መወሰኑን ተናግረዋል።

ፈተናውን ለመስጠት ታቅዶ የነበረው ጥር 14 እና 15 የነበረ ቢሆንም፤ ሁሉም ዩኒቨርስቲዎች እኩል ትምህርት ባለመጀመራቸው ወደ ጥር 26 ቀን 2017 ዓ.ም. እንዲሸጋገር መደረጉን ገልጸዋል፡፡

በዚህ የፈተና ፕሮግራም ተንቀሻቃሽ ስልክና የወረቀት ፅሁፍ ይዞ መገኘት ፈፅሞ #የተከለከለ መሆኑን የገለጹት የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈፃሚው፤ "ተፈታኞች መታወቂያ መያዝና ከፈተና ፕሮግራሙ 30 ደቂቃ ቀድሞ ቦታው ላይ መድረስ ይጠበቅባቸዋል" ብለዋል፡፡ የወጣው ፈተናም ከተማሩት በመሆኑ ሳይጨነቁ በተረጋጋ መንፈስ መስራት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

የዘንድሮው የዩኒቨርስቲዎች የመውጫ ፈተና ከዚህ በፊት ይሰጥ እንደነበረው ሙሉ ለሙሉ በኦንላይን የሚካሄድ ሲሆን፤ ከጥር 26 እስከ 30 ከሰኞ እስከ አርብ ባሉት አምስት ተከታታይ ቀናት እንደሚሰጥ አስታውቀዋል።

የተማሪዎች ፈተና እንደተጠናቀቀ ቅዳሜ ማለትም የካቲት 1 ቀን የመምህራንን ስልጠና ሲወስዱ የነበሩ መምህራን ፈተና ይወስዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

[ዘገባው የአሃዱ ሬድዮ ጣቢያ ነው]

@EthiopianUniversitystudents1




ማካካሻ_ትምህርት_REMEDIAL_ማስፈፀሚያ_ሰነድ.pdf
4.9Mb
📘የሪሜዲያል ማስፈፀሚያ ሰነድ ለ2016 ዓ.ም
📝ለዘንድሮም አንድ አይነት ሲሆን የተቀየረው የምዘና ሂደቱ ብቻ ነው።

@EthiopianUniversitystudents1


ዝምተኛው ገዳይ ካርበን ሞኖክሳይድ(CO) (የከሰል ጭስ)

✍ አብዛኞቻችን  በቤታችን ውስጥ ከሰል የማጨስ ልምድ አለን፡፡ ታዲያ ይህ በቤታችንን የምንጠቀምበት ጭስ በአግባቡና በጥንቃቄ ካልያዝነው ለዕድሜ ልክ ህመም ለሆኑት የአንጎል ውድመትና የልብ በሽታን ሲያጋልጥ ባስ ሲልም ሕይወታችንን ሊያሳጣን የሚችል አደገኛ ጋዥ ነው::

✍ እንደ አሜሪካ የበሽታዎች መቆጣጠሪያና መከላከያ ማእከል መረጃ መሠረት የከሰል ጭስ ወይም ካርበን ሞኖክሳይድ በአይን የማይታይና ሽታ አልባ መርዛማ ጋዝ ነው፡፡

👉ካርበን ሞኖክሳይድ የሚፈጠረው ጋዝ፣ዘይት፣ ከሰል ወይም እንጨት ሙሉ በሙሉ ተቃጥለው ባለማለቃቸው የሚፈጠር ነው፡፡

✍የእንጨት ከሰል (charcoal) የመኪና ጭስና ሲጋራ ይህንኑ ካርበን ሞኖክሳይድ በማመንጨት ይጠቀሳሉ፡፡ ከሰልን ጨምሮ የካርበን ምንጭ የሆኑ እንደ ጋዝ ስቶቭ፣ውሃ ማሞቂያ፣ የቤት ማሞቂያ፣የምግብ ማብሰያ ምድጃዎች በሙሉ በአግባቡ ካልተገጠሙ፣በአግባቡ ካልተጠገኑና ነፋስ የማያገኛቸው ጥብቅብቅ ያለቦታ ከተቀመጡ ችግሩን ሊያከትሉ ይችላሉ፡፡

✍የከሰል ጭስ ወይም ካርበን ሞኖክሳይድ ወደ ውስጣችን በምንስበብት ወቅት በቀጥተ በደማችን ውስጥ በመግባት የቀይ የደም ሕዋስ አካል የሆነውና ኦክስጅን ተሸክሞ ለለተያዩ የሰውነታችን ክፍል ከሚያደርሰው ሂሞግሎቢን ጋር በመቀላቀል ካርበኦክሲሄሞግሎቢን ይሆናል፡፡

👉ይህ ከሆነ በኃላ ደማችን ኦክሰጅን መሸከሙን ያቆማል፡፡ በዚህ የተነሳ ሕዋሳቶቻችንና የሕዋሳቶቸችን አነስተኛ ክፍሎች ይጎዳሉ፤ይሞታሉ፡፡ህይወታችንንም እናጣለን::

✅በመሆኑም  በከሰል ጢስ  ምክንያት በርካቶች በዝምታ እየሞቱ  በመሆኑ ጥንቃቄ እናድርግ የሚለው ምክራችን ነው::

@EthiopianUniversitystudents1


በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት 10 ዩኒቨርሲቲዎችን ራስ ገዝ ለማድረግ እየተሰራ ነው፡- ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ


በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት 10 ዩኒቨርሲቲዎችን ራስ ገዝ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገልጸዋል።

የዩኒቨርስቲዎች የቀጣይ የሪፎርም መዳረሻ ራስ ገዝ መሆን ነው ያሉት ፕሮፌሰር ብርሃኑ፤በትምህርት ጥራት እና ተደራሽነት ላይ ያለውን ችግር ለመፍታት የተለያዩ የማሻሻያ ስራዎቸ መሰራታቸውን ተናግረዋል።

የትምህርት እና የምርምር ስራዎችን የበለጠ ለማጠናከር ራስ ገዝነት የተሻለ እድል ይፈጥራል ነው ያሉት።

ሚኒስትሩ የጎንደር ዩኒቨርስቲ የተመሰረተበትን 70ኛ ዓመት እና የጎንድር ዩኒቨርሲቲ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል 100ኛ ዓመት ክብረ በዓል ላይ ተገኝተዋል።

ጥራትን መሰረት አድርጎ የትምህርት ተቋማት ሃገር ተረካቢዎችና መሪዎችን በመቅረጽ ዩኒቨርሲቲዎች ከመቼውም ጊዜ በላይ ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።

እስካሁን የተሰሩ ስራዎች እንዳሉ ሆነው በቀጣይ ሊሰሩ የሚገቡት ላይ ማተኮር ይገባል ብለዋል ሚኒስትሩ።

ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ ዝግጅቶች የምስረታ በዓሉን እያከበረ ይገኛል።

የጎንድር ዩኒቨርሲቲ ኢትዮጵያ የራሷ የጤና ባለሙያዎች ያስፈለጓታል ተብሎ በ1942 በተነሳ ሃሳብ መነሻነት በተደረገ ጥረት 1947 ዓ.ም የጤና ባለሙያ ማሰልጠኛ ሆኖ መመስቱ የዩኒቨርስቲው ታሪክ ያሳያል።

@EthiopianUniversitystudents1


#BongaUniversity

በ2017 ዓ.ም ለአቅም ማሻሻያ ትምህርት (Remedial Program) ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት የካትቲ 1 እና 2/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➭ የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
➭ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➭ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቅያ ሰርትፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
➭ ስድስት ፓስፖርት መጠን ፎቶግራፍ፣
➭ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።

@remedial_tricks


እጃችሁ ላይ ያላችሁን ማንኛውንም ነገር ካላችሁበት ቦታ ሆናችሁ መሸጥም ሆነ መግዛት የምትችሉበትን የቴሌግራም ቻናል እናስተዋውቃችሁ 👇👇👇

@Habesha_Gebeya1
@Habesha_Gebeya1

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.