Ethiopian Electric Power


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha


Ethiopian Electric Power (EEP) | Official Channel
Powering Ethiopia’s future ⚡️🇪🇹
Official news, updates, projects, and announcements from EEP.

Bog‘liq kanallar  |  O‘xshash kanallar

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


Humni Elektiriikaa Itoophiyaa baga Ayyaana Irreechaa bara 2019 nagaan geessan jechaa hawwii gaarii qabu ibsa.

Ayyaanni Kun kan Nagaa, Jaalalaa fi Badhaadhinaa akka isiniif ta’us ni hawwa!

Ayyaana Gaarii!
Humna Elektiriikaa Itoophiyaa!


የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እንኳን ለ2019 ዓ.ም የኢሬቻ በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱን ይገልፃል።

በዓሉ የሰላም፣ የፍቅርና የብልፅግና እንዲሆንላችሁ ይመኛል።

መልካም በዓል!
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል!

💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric
📌ቴሌግራም↠https://t.me/ethio_power
📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopianelectricpower
📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia
📌ዩትዩብ↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia
📌ድረ- ገጽ ይጎብኙ https://www.eep.com.et
መስከረም 22 ቀን 2019 ዓ.ም


ሠራተኛው የተመደበበትን ሥራ በኃላፊነት ስሜት ሊወጣ ይገባል
 .......///......
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከመስከረም 7 እስከ 21 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ ለተቋሙ ሠራተኞች በአምስት ዙር  "የሠራተኞች ተሳትፎ ለተቋማዊ ዕድገት" በሚል ርዕስ ሲሰጥ የቆየውን የአቅም ግንባታ ስልጠና አጠናቀቀ።
 
ሥልጠናዉ በተቋሙ ውስጥ የሚታዩ ክፍተቶችን ለመሙላት፣ የሠራተኛውንና የአመራሩን ግንኙነት ለማጠናከርና የአሰራር ስልትን ለመዘርጋት ታልሞ የተዘጋጀ መሆኑን የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ተወካይ ኃላፊ አብራርተዋል።
 
ተወካይ ኃላፊው ዶ/ር ግርማ ግዛቸው እንደተናገሩት ሠራተኛው በተመደበበት ሥራ ላይ በኃላፊነት ስሜት መስራት እንዳለበት አሳስበዋል።
 
ተቋሙ የሚቀየረው የሠራተኛው ተሳትፎ በሁሉም አቅጣጫ እኩል ሆኖ ሲንቀሳቀስ በመሆኑ ሠራተኛው ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀምና የራሱን አሻራ በማሳረፍ ተቋሙን ወደተሻለ ደረጃ ማሸጋገር እንዳለበት ጥሪ አቅርበዋል።
 
በተቋሙ የሰው ሀብት ሥራ አስፈፃሚ አቶ አታላይ አበበ በበኩላቸው በተቋሙ ውስጥ የሚሰሩ ሥራዎች ውጤታማ የሚሆኑት የሠራተኛው ተሳትፎ ሲያድግ መሆኑን አስረድተዋል።

በመሆኑም ሁሉም ሠራተኛ የተቋሙን ተልዕኮና ራዕይ መሰረት በማድረግ የድርሻውን ሊወጣ ይገባል ብለዋል።

በሰልጠናው መድረክ ላይ የተሳተፉ ሠራተኞች በሰጡት አስተያየት ሥልጠናው ወቅታዊና ተቋማዊ ለውጥን የሚያፋጥን መሆኑን ገልፀዋል።

ሥልጠናው ተቋሙ ያለበትን ነባራዊ ሁኔታ እንድናውቅ፣ መብትና ግዴታችንን ለይተን እንድንረዳ እና በሥራ ቦታችን ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን በጋራ እንድናስተካክል ዕድል የሚሰጠን ነው ሲሉ ተናግረዋል።

💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric
📌ቴሌግራም↠https://t.me/ethio_power
📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopianelectricpower
📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia
📌ዩትዩብ↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia
📌ድረ- ገጽ ይጎብኙ https://www.eep.com.et
መስከረም 21 ቀን 2019 ዓ.ም




External Vacancy Announcement
.......///.........

💡 "Clean Energy For A Better Life!”

📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric
📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication
📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power
📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia
📌ዩትዩብ↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia
📌ድረ- ገጽ ይጎብኙ https://www.eep.com.et
መስከረም 21 ቀን 2019 ዓ.ም


⚡️ የማከፋፈያ ጣቢያ አቅም ማሻሻያና ማስፋፊያ - ለከተሞች እድገት የኃይል መሠረት

የኤሌክትሪክ ፍላጎት ከተሞች በሚያድጉበት፣ ኢንዱስትሪዎች በሚስፋፉበትና አዳዲስ የንግድ እና የአገልግሎት መስጫ ተቋማት በሚቋቋሙበት ፍጥነት እየጨመረ ነው። ይህንን እያደገ የመጣ ፍላጎት በአስተማማኝ ሁኔታ ለማስተናገድ የማከፋፈያ ጣቢያዎች አቅም ማሳደግና የማስፋፊያ ሥራዎች ወሳኝ ናቸው።
 
🏗 የአቅም ማሻሻያና ማስፋፊያ ሥራ ምን ያካትታል?

የማከፋፈያ ጣቢያ አቅም ማሻሻያ ማለት የኃይል ፍላጎቱን በመገምገም ተጨማሪ የትራንስፎርመሮችን አቅም መጨመር፣ ያረጁ ወይም የአቅም ውስንነት የገጠማቸውን መሳሪያዎች በሌላ መተካት፣ አዳዲስ ፊደሮችን (feeders) መጨመር፣ የመከላከያና የቁጥጥር ሥርዓቶችን ማዘመን፣ ኬብሎችንና ሌሎች የማከፋፈያ ጣቢያ የመቆጣጠሪያ መሣሪያዎችን አቅም ማሳደግ እና አዲስ ጣቢያ መገንባትን ያካትታል።
 
ተጨማሪ ያንብቡ.…

https://www.eep.com.et/?amh-news=የማከፋፈያ-ጣቢያ-አቅም-ማሻሻያና-ማስፋፊ&lang=am

💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric
📌ቴሌግራም↠
https://t.me/EEPCommuication
📌ሊን
ክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopianelectricpower/
📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia
📌ዩትዩብ↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia
📌ድረ- ገጽ ይጎብኙ https://www.eep.com.et
መስከረም 21 ቀን 2019 ዓ.ም


የተቋሙን የሥራ ባህል ያከበረ ሠራተኛ ለመፍጠር ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል
……..///……
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልን የሥራ ባህል  ያከበረ ሠራተኛ ለመፍጠር ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ የሰው ሀብት ሥራ አስፈጻሚ አቶ አታላይ አበበ ገለፁ፡፡

«የሠራተኞች ተሳትፎ ለተቋማዊ ዕድገት» በሚል መሪ ሃሳብ ለሠራተኞች በተዘጋጀው የመጨረሻ ዙር ሥልጠና ላይ ሥራ አስፈፃሚው እንደገለፁት ሥልጠናው የሠራተኞችን የግንዛቤ ደረጃ ከፍ በማድረግ ከሥነ-ምግባር አሠራር ጋር የተያያዙ ክፍተቶችን ለማስተካከል ያግዛል፡፡

ሥልጠናው በዋናነት ሰራተኞች የህዝብ አገልጋይነት መንፈስን እንዲላበሱ፣ በሥራ ቦታ መልካም ሥነ-ምግባርን እንዲያሳዩና የተቋሙን እሴቶች በዕለት ተዕለት ተግባራቸው ውስጥ እንዲተገብሩ የሚያስችል ጠንካራ መሠረት የሚጥል መሆኑ አመልክተዋል።

💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric
📌ቴሌግራም↠https://t.me/ethio_power
📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopianelectricpower
📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia
📌ዩትዩብ↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia
📌ድረ- ገጽ ይጎብኙ https://www.eep.com.et
መስከረም 21 ቀን 2019 ዓ.ም


የፈተና ጥሪ ማስታወቂያ
.....///......
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በHR Administration Officer I እና በFinance Administration Officer I የሥራ መደቦች ሠራተኞችን አወዳድሮ ለመቅጠር መጋቢት 30 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ማስታወቂያ መውጣቱ ይታወቃል፡፡

በዚሁ መሠረት በHR Administration Officer I ተመዝግባችሁ ከዚህ በታች ስማችሁ የተገለፀው አመልካቾች በሙሉ መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:30 ሰዓት፤

በFinance Administration Officer I ተመዝግባችሁ ከዚህ በታች ስማችሁ የተገለፀው አመልካቾች ደግሞ መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ.ም ከሰዓት 7:30 ሰዓት፤ ማንነታችሁን የሚገልጽ የታደሰ መታወቂያ በመያዝ ኮተቤ ብረታ ብረት ፊትለፊት በሚገኘው ተቋሙ ዋና መ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ የፅሁፍ ፈተና የሚሰጥ በመሆኑ ለፈተና እንድትገኙ እናሳስባለን፡፡

የስም ዝርዝራችሁን.....

HR Administration Officer I: https://www.eep.com.et/?amh-announcement=የፈተና-ጥሪ-ማስታወቂያ-7&lang=am

Finance Administration Officer I: https://www.eep.com.et/?amh-announcement=የፈተና-ጥሪ-ማስታወቂያ-6&lang=am

💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric
📌ቴሌግራም↠
https://t.me/EEPCommuication
📌ሊን
ክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopianelectricpower/
📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia
📌ዩትዩብ↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia

4k 0 54 9 12

የተጎዳውን ትራንስፎርመር ከሥፍራው ለማንሳት ሲባል ኃይል ይቋረጣል
.......///........
በአዲስ ዌስት ማከፋፈያ ጣቢያ የተበላሸውን ትራንስፎርመር ከቦታው ለማንሳት ኃይል የሚቋረጥ መሆኑን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማዕከላዊ 3 ሪጅን አስታውቋል።

ሪጅኑ እንዳስታወቀው የተበላሸውን ትራንስፎርመር በክሬን ከቦታው በማንሳት ሎቤድ ላይ ለመጫን ጣቢያው ከ9፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ 11፡00 ድረስ ሙሉ በሙሉ ኃይል መስጠት ያቋርጣል፡፡

ስለሆነም ጣቢያው እስከተጠቀሰው ሰዓት ድረስ በጊዜያዊነት አገልግሎት መስጠት የሚያቆም መሆኑን ተረድታችሁ በትዕግስት እንድትጠብቁን ሲል ሪጅኑ ጥሪ አቅርቧል፡፡

የተበላሸውን ትራንስፎርመር ጠግኖ ወደ ቀድሞ አገልግሎት ለመመለስ አልያም በሌላ ትራንስፎርመር ለመተካት ሁለት አማራጮች በተመሳሳይ ተግባራዊ መደረግ መጀመራቸውን ማስታወቃችን ይታወሳል፡፡

💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric
📌ቴሌግራም↠https://t.me/ethio_power
📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power
📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia
📌ዩትዩብ↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia
📌ድረ- ገጽ ይጎብኙ https://www.eep.com.et
መስከረም 20 ቀን 2019 ዓ.ም




በሥራ ቦታ የሚታዩ የሥነ-ምግባር ጉድለቶችን ለማረም ተከታታይ ስልጠናዎች አስፈላጊ ናቸው

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በሥራ ቦታ የሚታዩ የሥነ-ምግባር ጉድለቶችን በማረም ተቋማዊ ግቦችን ለማሳካትና የአፈጻጸም ክፍተቶችን ለመድፈን የሠራተኞችን የመፈጸም አቅም የሚያጎልብቱ ተከታታይ ስልጠናዎች ወሳኝ መሆናቸው ተገለጸ፡፡

የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ተወካይ ኃላፊ ግርማ ግዛቸው (ዶ/ር) «የሠራተኞች ተሳትፎ ለተቋማዊ ዕድገት» በሚል መሪ ቃል ሲሰጥ በቆየው አራተኛው ዙር ስልጠና ሲጠናቀቅ ባስተላለፉት መልዕክት ተቋሙ በ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ያስመዘገባቸው በርካታ ስኬቶች ቢኖሩትም በፕሮጀክት አመራር፣ በሠራተኛ ተሳትፎ፣ በሀብት አጠቃቀም እና ንብረት አስተዳደር በኩል ክፍተቶች እንደነበሩ ገልፀዋል።

በመሆኑም የተዘጋጀው ስልጠና የሠራተኛውን የመፈጸም አቅም በማጎልበት የተቋሙን ግቦች ለማሳካት አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት በመረዳትና «ተቋሙ ካልኖረ እኔም አልኖርም» የሚል አስተሳሰብ በመያዝ የተቋሙን ገጽታና ስትራቴጂ በሚገባ ተረድቶ መስራት እንዳለበት ጥሪ አቅርበዋል።
 
ተጨማሪ ያንብቡ.…

https://www.eep.com.et/?amh-news=በሥራ-ቦታ-የሚታዩ-የሥነ-ምግባር-ጉድለቶች&lang=am

💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric
📌ቴሌግራም↠
https://t.me/EEPCommuication
📌ሊን
ክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power
📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia
📌ዩትዩብ↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia
📌ድረ- ገጽ ይጎብኙ https://www.eep.com.et
መስከረም 20 ቀን 2019


⚡️ የግሪድ አካላዊ ደህንነት፦ የሁላችንም ኃላፊነት

የኤሌክትሪክ ግሪድ ማለት ኤሌክትሪክን ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ የሚያደርሱ የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎች ብቻ አይደለም።

የኃይል ማመንጫዎች፣ ማስተላለፊያ መስመሮች፣ ማከፋፈያ ጣቢያዎች፣ ትራንስፎርመሮችና የመቆጣጠሪያ መሳሪያዎች በሙሉ የአንድ ግሪድ አካላት ናቸው። ይህ መሠረተ ልማት በአካላዊ ጉዳት ከተጎዳ የኃይል አቅርቦት ሊቋረጥ፣ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴም ሊጎዳ ይችላል።

የግሪድ አካላዊ ደህንነት ማለት እነዚህን የኃይል መሠረተ ልማቶች ከስርቆት፣ ከብልሽት፣ ያልተፈቀደለት ሰው መሳሪያዎቹ ወደሚገኙበት ከመግባትና ከሌሎች አካላዊ ጥቃቶች መጠበቅ ማለት ነው። በዓለም አቀፍ የኃይል ዘርፍ ውስጥ የግሪድ አካላዊ ደህንነትን ማስጠበቅ የኤሌክትሪክ አቅርቦት አስተማማኝነት ከሚያረጋግጡ ዋና ጉዳዮች አንዱ እንደሆነ ይታወቃል።
 
🛡 እያንዳንዱን የኃይል መሠረተ ልማት በሰው ጥበቃ ብቻ ማስጠበቅ ይቻላል?
 
ተጨማሪ ያንብቡ.…

https://www.eep.com.et/?amh-news=የግሪድ-አካላዊ-ደህንነት፦-የሁላችንም-ኃ&lang=am

💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric
📌ቴሌግራም↠
https://t.me/EEPCommuication
📌ሊን
ክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power
📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia
📌ዩትዩብ↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia
📌ድረ- ገጽ ይጎብኙ https://www.eep.com.et
መስከረም 20 ቀን 2019 ዓ.ም


የተቋሙ ሠራተኞች ማህበራዊ ሚዲያን በኃላፊነት ሊጠቀሙ ይገባል
....///....
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ሠራተኞች የማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀማቸውን በኃላፊነት እና የሙያ ሥነ-ምግባርን በተከተለ መንገድ መምራት እንዳለባቸው የተቋሙ የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና መምሪያ ዳይሬክተር አቶ ደረጀ አጥናፌ አሳሰቡ።

ዳይሬክተሩ "የሠራተኞች ተሳትፎ ለተቋማዊ ዕድገት" በሚል መሪ ቃል እየተሰጠ በሚገኘው አራተኛው ዙር ስልጠና ላይ እንደገለጹት ሠራተኞች የተቋሙን መልካም ስም የመጠበቅ እና ቁልፍ የመሠረተ-ልማት መረጃዎችን ደኅንነት የመጠበቅ ኃላፊነት አለባቸው።

በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚለቀቅ ሁሉም መረጃ የግል ተብሎ ሊወሰድ ስለማይችል ሠራተኞች የሚያጋሯቸው መረጃዎች የተቋሙን መልካም ሥምና ገጽታ በጠበቀ መልኩ መሆን እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

ተቋሙን የተመለከቱ መረጃዎች ሲኖሩ ተጣርተው በሚመለከተው አካል ይፋ እስከሚሆኑ ድረስ በግል ማኅበራዊ ገጽ ላይ መለጠፍ ከሙያ ስነ-ምግባር ጋር የሚጣረስ በመሆኑ ከእነዚህ ድርጊቶች መቆጠብ እንደሚገባ አስረድተዋል።

ሠራተኞች መረጃዎችን በማህበራዊ ሚዲያ ከማሰራጨታቸው በፊት ትክክለኛነታቸውን እና ተፅዕኗቸውን መገምገም እንደሚገባቸው ነው የገለጹት።

የተቋሙ ሠራተኞች የሀገሪቱ የብርሃን ጠባቂዎች በመሆናቸው በዲጂታል ግንኙነቶቻቸውና በማኅበራዊ ሚዲያ እንቅስቃሴዎቻቸው ከፍተኛ የኃላፊነትና የሙያ ሥነ-ምግባር ማሳየት እንደሚጠበቅባቸው አቶ ደረጀ አጥናፌ አሳስበዋል።

💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric
📌ቴሌግራም↠https://t.me/ethio_power
📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power
📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia
📌ዩትዩብ↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia
📌ድረ- ገጽ ይጎብኙ https://www.eep.com.et
መስከረም 19 ቀን 2019 ዓ.ም



13 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.