አፓርትመንት ቤቱስ? ጥንቅቅ ተደርጎ የተሰራውን ውብ አፓርትመንት ቤት መሀል አዲስ አበባ ሲግናል አለፍ ብሎ ከምስራቅ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት አጠገብ ያገኙታል፡፡ ባለሁለት መኝታ ቤት የተንጣለለ ሳሎን፣ ኪችንና መታጠቢያ ቤት የያዘው የአፓርትመንት ቤትም ይትባረክ ሳሙኤል ሰኔ 28/2016 ዓ.ም የወጣው የቶምቦላ ሎተሪ በ1ኛ ዕጣ የደረሰው ነው፡፡
ይህ ታሪክ ይትባረክ ሳሙኤልን የቶምቦላ ሎተሪ ዕጣ ከጊዶ ቀበሌ አምጥታ ሚሊየኖች በሚኖሩበት፣ ቢሊየን ብሮች በሚንቀሳቀስበት በመሐል አዲስ አበባ ባለሁለት መኝታ ቤት ባለዕድለኛ ያደረገችው ታሪክ ነው፡፡ይትባረክ የሎተሪ ደንበኛ ያደረገኝ ቲያትር ነው ይላል፡፡ ብዙግዜ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እያለ ያጋጠመውን ያስታውሳል፡፡ አንድ እለት የአማርኛ መምህሩ ክፍል እንደገቡ የአራት ልጆች ስም ጠርተው የዛሬ አስራ አምስት ቀን በተማሪዎች መድረክ የሚቀርብ ድራማ አዘጋጅታችሁ እንድታቀርቡ ብለው አዘዟቸው፡፡ ቲያትር እንዲሰራ በመምህሩ የታዘዘው አንዱ ተማሪ ይትባረክ ነበር፡፡
የድራማው ታሪክ ሶስት ጓደኛሞች ወደ ገበያ ሄደው ሸቀጣሸቀጥ ከገዙ በኃላ 50 ብር ይተርፋቸዋል፡፡ በቀረው ገንዘብ ምን እናድርግበት በሚለው ሃሳብ ሳይስማሙ ሲጨቃጨቁ ቆይተው በመጨረሻ ሎተሪ ለመግዛት በመወሰናቸው ሎተሪ ይገዛሉ፡፡ የመውጫው ቀን ሲደርስ የአንድ ሚሊዮን ብር ዕድለኛ ይሆናሉ፡፡ ድራማው ሲጠናቀቅ ተማሪው ያጨበጭባል፡፡
ይትባረክ ከዚህ ቀን በኋላ የሎተሪ ደንበኛ መሆኑን ይናገራል፡፡ ሎተሪ ከቦንጋ ብቻ ሳይሆን ከጅማም፣ ከሚዛንም ሰው እያስላከ ይገዛል፡፡
ከአቅመ ደካማ እናቱ ጋር የሚኖረው ይትባረክ አባቱ በህይወት የሉም፤ የቤተሰቡን የእርሻ መሬት እያረሰ ቤተሰቡን ያስተዳድራል፡፡
በሎተሪ ዕምነቱ ሎተሪ ሁልጊዜ ቁረጡ አንድ ቀን ይደርሳችኃል ይላል፡፡ በድጋሚ የሚሊዮኖች ብር እድለኛ ሆኖ እንደሚመጣ በእርግጠኝነት ይናገራል፡፡