በአዲስ ዓመት በመጀመርያዋ ቀን 20 ሚሊየን ብር ማን ይሰጣል?መስከረም 1 ቀን፣ሁለት በዓል፣ ድርብ ደስታ ነበር
አስረሳኸኝ ጌታቸው ጳጉሜን 5 ቀን 2016 ዓ.ም የወጣው የዕንቁጣጣሽ ሎተሪ የ20 ሚሊየን ብር ዕድለኛ ነው፡፡
መስከረም 1 ቀን 2017 የዘመን መለወጫ ዕለት ጠዋት፣አስረሳኸኝ በኪራይ ቤቱ ነበር፡፡በዓሉን በጋራ ለማክበር ጎረቤቶቹን በመጥራቱ ቤቱ በበዓል ድባብ ደምቃለች፤ጎረቤት ተሰብስቧል፤ጨዋታው ደምቋል፤ሳር ተጎዝጉዞ፣ ቡና ተፈልቶ፣ ዳቦ ተቆርሶ፣ ማእድ ቀርቦ አዲሱን ዓመት እየተቀበሉት ነው፡፡
አስረሳኸኝ ጎረቤቶቹን ጠርቶ በዓሉን ቢያደምቅም በዚያን ሰአት በሙሉ ልቡ ከነሱ ጋር እንዳልነበረ ይናገራል፡፡ የእንቁጣጣሽ ሎተሪ ዕጣ በዋዜማው ጳጉሜ 5 ስለወጣና እድሉን ለማወቅ ጓጉቶ ስለነበር የገዛቸውን የእንቁጣጣሽ ሎተሪ ትኬቶች ከኪሱ አውጥቶ ከደራው ጨዋታ ገለል አለ፡፡ የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎትን የቴሌግራም ገጽ ከፍቶ የዕጣ ማውጫውን ሲመለከት የአንደኛው ዕጣ ቁጥር 0103072 ደምቃ ታየችው፡፡ ማመን ስላልቻለ ደጋግሞ አየ፡፡ የ1ኛው ዕጣ የ20 ሚሊየን ብር ዕድለኛ መሆኑን ደጋግሞ አረጋገጠ፡፡ በተደበላለቀ ስሜት ሆኖ የሞቀ ጨዋታ ይዘው የነበሩትን ጎረቤቶቹን የምስራች አለኝ፣የ20 ሚሊየን ብር ዕድለኛ ሆኛለሁ ቢልም የቀልድ ስለመሰላቸው የምስራቹን ከቁም ነገር የቆጠረው አልነበረም፡፡