ሩሲያ በሱዳን የቀይ ባሕር ወደብ ላይ የባሕር ኃይል ሠፈር ለመመሥረት ከሱዳን መንግሥት ጋር ስምምነት ላይ መድረሷ ተነገረ
---------------
ሩሲያን በመጎብኘት ላይ የሚገኙት የሱዳን ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ዓሊ የሱፍ እንዳሉት የሁለቱ ወገኖች ባለሥልጣናት የጦር ሠፈሩን ግንባታ በሚመለከቱ በሁሉም ነጥቦች ላይ ተግባብተዋል።
ሩሲያ ሱዳን የባሕር ጠረፍ ላይ የባሕር ኃይል ሠፈር ለመመሥረት እንደ ግሪጎሪያኑ አቆጣጠር ከ2017 ጀምሮ ከካርቱም ባለሥልጣናት ጋር እየተደራደረች ነዉ።የሁለቱ መንግሥታት ባለሥልጣናት በ2020 የመጀመሪያ ደረጃ ሥምምነት ተፈራርመዋል።
ይሁንና ባለፈዉ ታኅሳስ በሱዳን ጦር ኃይል የሚመራዉ መንግሥት ሥምምነቱን አፍርሷል የሚል ዘገባ ሲናፈስ ነበር።የሞስኮ ባለሥልጣናት ዘገባዉን አስተባብለዋል።
የሱዳን ጦር ከሐገሪቱ ፈጥኖ ደራሽ ጦር ጋር ለሚያደርገዉ ዉጊያ ድጋፍ ለማግኘት ከሩሲያና ከኢራን ጋር ያለዉን ግንኙነት ከቅርብ ጊዜ ወዲሕ እያጠናከረ ነዉ።
ሩሲያ ሱዳን ባሕር ጠረፍ ላይ የጦር ሠፈር ከመሠረተች ጁቡቲ ዉስጥ የጦር ኃይል ካሰፈሩት ከቻይና፣ ከዩናይትድ ስቴትስና ከፈረንሳይ ጋር ለመፎካከር ይጠቅማታል።
ዘገባው የጀርመን ድምፅ ነው