ግብፅ ለናይል ተፋሰስ አባል ሀገራት "ግድቡን አትጎብኙ" የሚል ደብዳቤ ፅፋ እንደነበር ተገለፀ
---------
የናይል ተፋሰስ አባል ሀገራት የዓባይ ግድብን የጎበኙት የግብፅን "አትጎብኙ" ደብዳቤ ውድቅ አድርገው መሆኑ ተነግሯል።
በዓባይ ግድብ ላይ የናይል ተፋሰስ አባል ሀገራት ሚኒስትሮች የተካሄደው ጉብኝት በኢትዮጵያ ተቃራኒ የቆመውን አካል ያሽመደመደ ነው ሲል የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ሀገራቱ ሚኒስትሮች ወደ ናይል ቀን ስብሰባ ሲመጡ እግረ መንገዳቸውን የዓባይ ግድብንም እንዲጎበኙ ኢትዮጵያ አስቀድማ ደብዳቤ መላኳን የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ሀባታሙ ኢተፋ ተናግረዋል።
በአንጻሩ የግብፁ የውሃ ሚኒስትር ለሁሉም የተፋሰሱ ሀገራት ሚኒስትሮች በኢትዮጵያ በኩል የተላለፈላቸውን የዓባይ ግድብን ጎበኙ ጥሪ መቀበል የለባችሁም ብሎ ነበር።
ይሁንና ሚኒስትሮቹ የግብፅን ጥሪ ባለመቀበል የዓባይ ግድብን ጎብኝተው ከሰማይ በታች፤ ከምድር በላይ አለኝ የሚሉትን ጥያቄዎቻቸውን ሁሉ ጠይቀው ምላሽ ማግኘት ችለዋል ነው ያሉት ሚኒስትሩ።
እኛ በደብዳቤ ለታጀበው የግብፅ የ"አትጎብኙ" መልዕክት የመልስ ምት አልሰጠንበትም ያሉት ሚኒስትሩ፣ ጉዳዩ የተለመደ የግብፅ የሐሰት ፕሮፖጋንዳ አካል እንደመሆኑ ንቀን አልፈነዋል ብለዋል።
ኢትዮጵያ ግድቧን ለማስጎብኘት መጋበዝ መብቷ እንደሆነ ጠቅሰው፤ በዚህ ረገድ በመጀመሪያም ቢሆን የዓባይ ግድብን እንዲጎበኝ የጋበዘችው ኢትዮጵያ እንጂ የናይል ቤዚን ኢንሼቲቭ አይደለም ሲሉ ገልጸዋል።
በመሆኑም የግብፁ የውሃ ሚኒስትር የአትጎብኙ መልዕክታቸውን ሲያስተላልፉ አንድም ሀገር እንዳልተቀበላቸው ተናግረዋል። ይህ ደግሞ ለኢትዮጵያ ትልቅ ስኬት ነው ብለዋል።
ግብፅም በኢትዮጵያ ሜዳ ለመጫወት ፈልጋ በራሷ ላይ ግብ አስቆጥራለች ሲሉ ገልጸውታል።
አስገራሚው ነገር እንዳትሔዱ ብለው ያሏቸው ሚኒስትሮች ወደ ዓባይ ግድብ የሔዱት እንዲያውም በከፍተኛ ተነሳሽነት ጉብኝቱን እንደጎበኙም አስረድተዋል።
የታንዛኒያው የውሃ ሚኒስትር በሀገራቸው ምርጫ ጉዳይ ጋር ተያይዞ ባጋጠማቸው አስቸኳይ ጉዳይ ካለመሄዳቸው በስተቀር ሁሉም የዓባይ ግድብን በሚኒስትር ደረጃ ጎብኝተዋል።
ሚኒስትሮቹ ዓባይ ግድብ ከደረሱ በኋላ የነበራቸው አግራሞት በግልጽ የሚታይ ነበር ያሉት ሚኒስትሩ፤ ቀደም ሲል ሲነዛ የነበረው ፕሮፓጋንዳ እና መሬት ላይ ያዩት እውነታ ልዩነቱ አስደንቋቸዋል ብለዋል።
ያንን የሚያክል ግድብ ኢትዮጵያ መገንባት መቻሏ እንደ ተዓምር የሚታይ ነው የሚል አስተያየትም መስጠታቸውንም ገልጸዋል።
እንደ ሚኒስትሩ ማብራሪያ፤ ጎብኚዎቹ አንደኛ የግድቡ መጠን ከጠበቁት በላይ ሆኖባቸዋል። ስፋቱና የውሃ መጠኑ አስደምሟቸዋል።
ከምንም በላይ የሥራው ጥራት ትንግርት ሆኖባቸዋል። ትልቁ ስኬት ያሉት ደግሞ ኢትዮጵያ የዓባይ ግድብን ለመገንባት ስትል ያለፈችው ፈተና የሚያስደነቅ ስለመሆኑም የጉብኝቱ ሚኒስትሮች አስተያየታቸውን አካፍለዋል።
ምክንያቱም ጎብኚዎቹ ግድቡን ገና እንዳዩት ከመደነቃቸው ባለፈ፣ ግብፆች ሲያራግቡት የነበረው ፕሮፓጋንዳ ሐሰት መሆኑን ተገንዝበዋል ሲሉም አብራርተዋል።