ሱዳን አውሮፕላን ተከስክሶ 46 ሰዎች ሞቱ
-----------
የሱዳን አንቶኖቭ ወታደራዊ የማጓጓዣ አውሮፕላን ከዋና ከተማዪቱ ካርቱም ወጣ ባለ የመኖሪያ ሥፍራ አካባቢ ተከስክሶ 46 ሰዎች ሞቱ ። ከሟቾቹ መካከል የመላ ካርቱም የቀድሞ ጦር አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ባህር ይገኙበታል ተብሏል ።
ከሞቱት ሰላማዊ ሰዎች በተጨማሪ ሁለት ወታደራዊ መኮንኖችም ይገኙበታል ተብሏል፥ 10 ሰዎችም ቆስለዋል ።
የዓይን ምስክሮች በወቅቱ ከባድ ፍንዳታ መስማታቸውንና በአካባቢው የነበሩ ቤቶች ላይም ጉዳት ሲደርስ ማየታቸውን ተናግረዋል። አንድ ወታደራዊ ምንጭ ለፈረንሳይ ዜና አገልግሎት እንደተናገሩት፦ የአደጋው መንስኤ የቴክኒክ ችግር ሳይሆን አይቀርም ።
የአውሮፕላን አደጋው ትናንት ሌሊት የደረሰው ኦምዱርማን ከተማ ውስጥ በሚገኘው ትልቁ ወታደራዊ የአየር ኃይል ጦር ሰፈር፤ ዋዲ ሴይድ አቅራቢያ መሆኑን የአካባቢው መንግሥት ዐሳውቋል ።
አደጋው ከመድረሱ አንድ ቀን አስቀድሞ የሱዳንን ጦር የሚወጋው ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ኢልዩሽን የተባለ ሩስያ ሠራሽ አውሮፕላን በደቡብ ዳርፉር ዋና ከተማ ኒያላ ውስጥ ተኩሶ መጣሉን ተናግሮ ነበር ። ቡድኑ እንዳለው አውሮፕላኑ በውስጡ ከነበሩት ሠራተኞች ጋር ወድሟል ።
የሱዳን ጦር ሠራዊት ከሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ጋር ጦርነት ውስጥ ከገባ ሁለት ዓመታትን ሊያስቆጥር ነው ።