ደቡብ ሱዳን ሰዓት እላፊ አወጀች
የደቡብ ሱዳን ፖሊስ የምሽት ሰዓት እላፊ አውጇል።
ፖሊስ ሰዓት እላፊውን ያወጀው ትላንት ጠዋት ሱዳናውያንን በመቃወም የተደረገው ሰልፍ ወደ ዘረፋ ረብሻ በማምራቱ ነው።
በደቡብ ሱዳን በሚኖሩ ሱዳናውያን ላይ የበቀል ጥቃት ይፈፀማል የሚል ስጋት በመኖሩ አደጋውን ለመከላከል የሰዓት እላፊ እወጃውን አስፈላጊ አድርጎታል ተብሏል።
ለተቃውሞው መነሻ የሆነው 29 ደቡብ ሱዳናውያን በዚህ ሳምንት በሱዳን ሰራዊት ተገድለዋል በሚል እንደሆነ የኤኤፍፒ ዘገባ አመልክቷል።
የሱዳን ሠራዊት ዋድ ማዳኒ የተሰኘችውን ከተማ ከፈጥኖ ደራሽ ኅይሉ ቁጥጥር ነጻ ካወጣ በኋላ ሲቪሎችን ገድሏል የሚል ክስ ቀርቦበታል።
በሰዓት እላፊው ከምሽቱ 12 ጀምሮ የእንቅስቃሴ ገደብ ተጥሏል።
#እውን_መረጃ