የሱማሊያ መንግሥት፣ ግብጽ ወታደቿን ወደ ሱማሊያ ልትልክ መኾኑን አስታውቋል።
ግብጽ በሱማሊያ የምታሠማራው ኹለት ዓይነት ወታደሮችን እንደሆነ የሱማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አሕመድ ፊቂ ተናግረዋል። አንዱ ሥምሪት በአፍሪካ ኅብረት የማረጋጊያ ተልዕኮ ሥር የሚሠማራ ሲኾን፣ ሌላኛው በኹለትዮሽ ወታደራዊ ስምምነት መሠረት ከአፍሪካ ኅብረት ተልዕኮ ውጭ የሚደረግ ሥምሪት እንደኾነ ፊቂ ገልጸዋል። የኹለቱ አገራት ባለሥልጣናት በግብጽ ወታደሮች ሥምሪት ዙሪያ የቴክኒክ ውይይታቸውን ማጠናቀቃቸውን በሳምንቱ መጀመሪያ መግለጣቸው ይታወሳል። ግብጽ፣ በሁለቱም ሥምሪቶች ስንት ወታደሮች ወደ ሱማሊያ እንደምትልክ ግን አሁንም አልተገለጠም።
@Ewun_Mereja