የፈተና ክፍያ ተመን ጭማሪ ተደረገ
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በሚመራበት ደንብ ቁጥር 260/2004 መሠረት የሚሰጣቸውን የፈተና አገልግሎቶች በመንግሥት በጸደቀ ተመን መሠረት ያስተዳድራል።
በአዲሱ የመንግሥት አገልግሎት አስተዳደር ሪፎርም መሠረት የተሻሻለው ክፍያ ተመን በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 593/2016 መሠረት ከሐምሌ 22/2016 ዓ.ም. ጀምሮ ተገቢ ሆኗል።
በመሆኑም በተሻሻለው ተመን መሠረት በእያንዳንዱ ተፈታኝ ላይ ለምዝገባና ለፈተና አሰጣጥ:-
👉 ለዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና 2,000 ብር
👉 ለድህረ ምረቃ መግቢያ ፈተና 3,500 ብር
👉 ለሙያ ብቃት ፈተና ምዘና 3,500 ብር እና
👉 ለሊቃውንት ማረጋገጫ ፕሮግራም ፈተና 950 ብር በምዝገባ ሲስተሙ ላይ በተቀመጠው የክፍያ ሥርዓት የሚፈጸም ይሆናል።
እንዲሁም የተሻሻለው ተመን ከመውጣቱ በፊት ለተከፈሉ ፈተናዎች የሚከፈል ቀሪ ክፍያዎች 750 ብር በእያንዳንዱ ተፈታኝ ተሰልፎ እንዲፈጸም፤ ያልተከፈሉ ክፍያዎችም የተሻሻለው ተመን በሲስተሙ ላይ ከመጫኑ በፊት በመክፈል ተገቢውን አገልግሎት እንድታገኙ እናሳስባለን።