" ግብረሰዶማዊነት በሀገራችን ህግ ፍፅሙ የተከለከና በህግ የሚያስጠይቅ ተግባር ነው " - ፖሊስ
የአዲስ አበባ ከተማ ባህል ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ወግ እና ባህል ያፈነገጡ ድርጊቶችን አስመልክተው መግለጫ አውጥተዋል።
" ሀገራችን በህብረ ብሄራዊነቷ የምትታወቅና የተለያዩ ባህሎችና ወጎች ያሏት ሀገር ነች፡ " ያሉ ሲሆን ፤ " ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከማህበረሰቡ ወግና ባህል ያፈነገጡ ድርጊቶች እያጋጠሙ ነው " ብለዋል።
በከተማው አንዳንድ ሆቴሎች እና ሬስቶራንቶች የሀገሪቷን ህግ በሚጥስና ከማህበረሰቡ ወግ ተቃራኒ በሆነ መልኩ የግብረሰዶም እንቅስቃሴ መኖሩን መረጃዎች እያመለከቱ መሆኑን ህብረተሰቡ ተገንዝቦ መረጃ በመስጠት ተባባሪ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል።
ፖሊስ ፤ ግብረሰዶማዊነት በሀገራችን ህግ ፍፅሙ የተከለከና በህግ የሚያስጠይቅ ተግባር መሆኑን ገልጾ በሚደርሰው መረጃ በመመስረት በህግ አግባብ እርምጃ እንደሚወስድ እያስታውቋል።
በዚህ ህገ-ወጥ ተግባር የሚጠረጠሩ ሆቴል ቤቶች እና ሬስቶራንቶች የሀገርቷን ህግ አክብረው የመስራት ግዴታ እንዳለባቸው አሳስቧል።
ከዚህ ጉዳይ ጋር የተያያዘ መረጃ እና ጥቆማ ያለው ማንኛውም ሰው በአቅራቢያው በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ በግንባር በመቅረብ በተጨማሪም በነፃ የስልክ መስመር 991 እና 987 እንዲሁም በ011-1- 11-01-11 እና 011-5-52-63-02 በመጠቀም መረጃና ጥቆማ መስጠት እንደሚችል የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡