በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን የቴክኖሎጂ ዕውቀት ለማላቅና በዘርፉ ተፈላጊነታቸውን ለማሳደግ የሚሰራውን ተቋም ተዋወቁት፤
ድርጅቱ አመኒም ሶሉሽንስ ይባላል።
የድርጅቱ መስራቾችም እዛው አሜሪካ ነዋሪና የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች የሆኑት ጀሚላ ተሰማና ጸጋዬ ሽንብር ናቸው።
ድርጅቱ ወደ ስራ በገባባቸው ባለፉት አራት አመታት በቴክኖሎጂ ዘርፍ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ስኬታማ መሆን የሚያስችላቸውን ክህሎት ተኮር ስልጠና እና የማማከር አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል።
በ19 ዙሮች የተቋሙን ስልጠና የወሰዱ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንም በቴክኖሎጂ ዘርፍ በመንግስታዊና የግል ተቋማት ተፈላጊ ባለሙያዎች መሆን የቻሉ ሲሆን፣ ገቢያቸውንና ኑሯቸውን በማሻሻል ላይ ይገኛሉ።
ተቋሙ ከሚሰጠው ስልጠና ባሻገር በወሰዱት ስልጠና ስኬታማ የሆኑ ሰዎች ልምዳቸውን የሚያጋሩበትና ወጣቶችም ትስስር የሚፈጥሩበትን መድረክ ያመቻቻል።
በቅርቡ በአሌክሳንደሪያ ቨርጂኒያ ባዘጋጀው ተመሳሳይ መድረክ ላይም የተቋሙ የቀድሞ ሰልጣኞች ስኬት የተከበረ ሲሆን፣ በሥራ ገበያ ውስጥ አስፈላጊ ስለሆኑ ክህሎቶች የባለሙያዎች ምክርና የልምድ ልውውጥም ተካሂዷል።
ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን በቴክኖሎጂው መስክ ከተሻሉ የሥራ አማራጮች ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያግዙ መሰል የስልጠና ተቋማት በዋሺንግተን ዲሲና አካባቢዋ እየተበራከቱ በመምጣት ላይ እንዳሉ ከቪኦኤ አማርኛ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
════❁✿❁ ═══════
ለበለጠ መረጃ
ከዚህ ታች ባለው አድራሻ በፌስቡክና በቴሌግራም ይከተሉን
ፌስቡክ አድራሻችንን
Gettechinfofb (https://www.facebook.com/profile.php?id=100022088745521)
የቴሌግራም አድራሻችንን
https://t.me/Gettechinfonow