ቻይና ለመጀመሪያ ጊዜ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እገዛ በሚሰሩ ሮቦቶች የመንገድ ጥገና አካሄደች፡፡
ሮቦቶች እና ሾፌር አልባ ተሽከርካሪዎችን በመጠቀም የተከናወነው የመንገድ ጥገና 158 ኪ.ሜ ርዝማኔ እንዳለው ተገልጿል፡፡
መንገዱ የሀገሪቱን መዲና ቤጂንግን ከደቡባዊ የቻይና ግዛቶች ጋር የሚያገናኝ የፍጥነት መንገድ ነዉ፡፡ በስራዉ ላይ ድሮኖች የመንገዱን አጠቃላይ ገጽታ በመከታተል ምስላዊ መረጃዎችን ያቀርባሉ፡፡ ምስሉ ላይ ያለዉን መረጃ መሰረት በማድረግ ሮቦቶቹ ጥገና በሚያስፈልገዉ የመንገድ ክፍል ላይ በመሰማራት አስፈላጊውን ጥገና ያደርጋሉ፡፡
በስራዉ ላይ የተሳተፉት ማሽኖች በስራ ወቅት ለሚገጥማቸዉ ችግር ምላሽ መስጠት እንዲችሉ ሆነዉ የበለጸጉ ናቸዉ፡፡ በመሆኑም ደህንነቱ የተጠበቀና ወጪ ቆጣቢ የጥገና ስራ መስራት ስለመቻሉ ሀይዌይስ ኢንዱስትሪ የተባለው ድረ-ገጽ ዘግቧል፡፡
ይህ ጅማሮ ጥራታቸውን የጠበቁ መንገዶችን ለመገንባት አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ፣ ሮቦቶች እና ሾፌር አልባ ተሽከርካሪዎች ትልቅ አቅም እናዳላቸው ያሳየ ስለመሆኑ ተጠቁሟል። ════❁✿❁ ═══════
ለበለጠ መረጃ
ከዚህ ታች ባለው አድራሻ በፌስቡክና በቴሌግራም ይከተሉን
ፌስቡክ አድራሻችንን
Gettechinfofb (https://www.facebook.com/profile.php?id=100022088745521)
የቴሌግራም አድራሻችንን
https://t.me/Gettechinfonow