ኢትዮ ቴሌኮም የ4ጂ ሞባይል ኔትዎርክ አገልግሎትን በ67 ከተሞች አስጀመረ
**
ኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ ፍጥነት እና አስተማማኝ የዳታ አገልግሎት ማቅረብ የሚያስችለውን ዘመናዊ የ4ጂ LTE የሞባይል አገልግሎት በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ 67 ከተሞች አስጀምሯል፡፡
የ4ጂ LTE ኔትዎርክ ማስፋፊያው በከተሞቹ በከፍተኛ ሁኔታ በማደግ ላይ የሚገኘውን የደንበኞችን ፍላጎት መሰረት ያደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ተቋሙ በቀጣይም የቴሌኮም ኔትዎርክ እና የዲጂታል መሰረተ ልማቶችን የማስፋፋት ሥራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ከኢትዮ ቴሌኮም የማኀበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡