እውቀት ወለድ ክፍል አንድ
✍በ ቅድስት /@Kidymar1
ፍቅር እና ትግስት ዶርም ዉስጥ አልጋቸው ላይ ተቀምጠው እያወሩ: ወደ የፍቅር ስልክ text ይገባል::
ትግስት : ማነው?
ፍቅር : ተረጋጊ
ትግስት :ዮናስ ነዋ?
ፍቅር :አዎ
ትግስት : አረ አንቺ ልጅ ግን ለምን ጥያቄዉን አትቀበይም?
ፍቅር : ለምን?
ትግስት :ዮናስ እኮ ይወድሻል :በዛ ላይ እንደ ስሙ የዋህ ነው ::
ፍቅር :ህህህ በስም ሆነ እንዴ? በስም ከሆነ አደፍርስ እና አስጨናቂ ምን ይዉጣቸዋል ደሞ ጉዋደኛችን ሰላምም እንደስሟ ሰላም መሆን ነበረባት አንቺም እንደ ስምሽ ትግስ...
ትግስት :ተይው ተይው በቃ አንቺን ማን ይችላል ::
ፍቅር : ህህህህ አንቺ አደለሽ ያነሳሽው?
ትግስት :እኔማ በዋላ እዉነተኛ ፍቅርን ከሃሰተኛ ፍቅር መለየት አቅቶሽ እንዳይቆጭሽ ነው::
ፍቅር :ምንም አልመለሰችም ዝም አለች
ትግስት : በይ ተነሽ ፀጉር ቤትሽ ሂጂ ብላት ተነሳች ዶርሙንም ለቃ ወጣች::
ዮናስ ካፌ ተቀምጦ ወደ ምጠብቀው ሚኪ ሲሄድ እንደ ደበረው ነው
ሚኪ :ዮዮ ጭር ብለህሃል
ዮን :ተወኝ ባክህ
ሚኪ : ዛሬም?
ዮን :አዎ
ሚኪ :ለምን አትተዋትም?
ዮን : አንተ ደሞ እወዳታለሁ እኮ
ሚኪ :እሺ እሺ ቁርስ እንብላ እንዳታለቅስ ብሎ ሳቀበት
አስተናጋጅዋን ጠሩ..... መጣች
ምን ልታዘዝ?
ሚኪ: ዛሬም አሳ ነው?
ዮን: እና
ሚኪ :ለኔ እንቁላል አምጪልኝ ጥቂት ቆይቶ ምግቡ መጣ
መመገብ ጀመሩ ::ተመግበው ሲያበቁ ወተው እዛው ከተማ ወደሚገኘው የጉዋደኞቻቸው ቤት ሄዱ ይሄ የዘወትር የቅዳሜ ጠዋት ስራቸው ነው
ፍቅርም ለቅዳሜ ከሰዓት fellowship program ለመሄድ በጊዜ ፀጉርዋን ለመሰራት ተጣጥባ ተነሳች ልብሱዋን እንደ ነገሩ ለብሳ ወጣች በርግጥ ብዙ ቅዳሜዎችዋ ተመሳሳይ ናቸው አራት ዓመት እንዲሁ ታደርግ ነበር:: ዛሬ ግን አንድ ሃሳብ ላይ መወሰን እንዳለባት እየተሰማት ፀጉር ቤቱ በር ላይ ደረሰች::በካክስ ዉስጥ የሚጠበሰው ፀጉርዋ ሳይሰማት ታሰላስላለች :: አንድ ነገር ለማድረግ አሰበች+:ጨርሳም ስትወጣ ምሳ ለመብላት ወደ ካፌ ተመለሰች
ከምሳ በዋላ እንደ በፊቱ ጉዋደኛዋጋ አልደወለችም ይልቅ ሌላ ቦታ ነው የደወለችው::ሰዓት እስኪደርስ አልጠበቀችም::ብቻዋን ከሰዓቱ ቀድማ ወደ ቸርች ገሠገሠች:: ቸርች ስትደርስ የደወለችለት ሰው ቢሮ እየጠበቃት ነው ገብታ ሰላምታ ከተለዋወጡ በዋላ በዝምታ ተቀመተች ለተወሰነ ደቂቃ ዝም ካላት በዋላ ዝምታዋ ገርሞት ምን ልታማክሪኝ ነው እስኪ ንገሪኝ?
ይቀጥል?
https://t.me/Gospel_Literature