FDRE Education and Training Authority dan repost
#ማስታወቂያ
#ለሁሉምየግልከፍተኛትምህርትተቋማት
#ባሉበት
ጉዳዩ፦ የተመራቂ ተማሪዎችን ዝርዘር መረጃ እንድትልኩ ስለማሳሰብ ይሆናል፤
የፌዴራል መንግስት አስፈፃሚ አካላት ስልጣን እና ተግባር ለመወሰን የወጣ አዋጅ 1263/2014 ዓ.ም እና የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ለማቋቋም በሚኒስትሮች ምክርቤት በወጣ ደንብ ቁጥር 515/2014 ዓ.ም መሰረት በተሰጠው ስልጣን እና ተግባር የትምህርት ጥራትና አግባብነት ለማስጠበቅ እና ለመከታተል ያስችለው ዘንድ በመመሪያ 987/2016 ዓ.ም አንቀፅ 17 ንኡስ አንቀፅ 2 መሰረት ተቋማት የተመራቂ ተማሪዎችን መረጃ ወቅቱን ጠብቃችሁ ለባለስልጣኑ መላክ እንዳለባችሁ ተደንግጓል፡፡ ሆኖም ግን ባለስልጣኑ በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ ባደረገው ክትትል ያስመረቋቸውን ተማሪዎች ወቅቱን ጠብቀው አለመላካችው እና የተናጠል(የግለሰቦች) መረጃዎች የላኩ መሆኑ ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡
ስለዚህ ተቋማት ያስመረቋቸውን ተማሪዎች መረጃ አጠናቅረው በወቅቱ ባለማቅረባቸው ምክንያት የተመረቁ ተማሪዎች ለእንግልት ተዳርገዋል፡፡
በመሆኑም በተቋማችሁ ፈቃድ በተሰጣችሁ ትምህርት መስኮች፣ትምህርት ደረጃ፣መርሃ ግብር እና ካምፓስ ከዚህ በፊት ያላካችሁትን የተመረቁ ተማሪዎችን መረጃዎች በ2015 ዓ.ም አና 2016 ዓ.ም የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች መውጫ ፈተና ያለፉ ብቻ ከዚህ በፊት በተላከው ቅጽ መሰረት ዝርዝር መረጃውን እስከ ሰኔ 30/2016 ዓ.ም በሶፍት እና በሃርድ ኮፒ እንድትልኩ ለመጨረሻ ጊዜ እናሳስባለን፡፡
በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA
በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA
በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA
በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ