የብቃት ምዘና ፈተና ለምትወስዱ ጤና ባለሙያዎች በሙሉ
____
ጤና ሚኒስቴር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ Medicine, Nursing, Public Health, Anesthesia, Pharmacy, Medical Laboratory Science, Midwifery, Dental Medicine, Medical Radiology Technology, Environmental Health, Psychiatric Nursing, Pediatric & Child Health Nursing, Emergency & Critical Care Nursing, Surgical Nursing, Physiotherapy እና Human Nutrition ሙያዎች በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቃችሁ ቴምፓራሪ ዲግሪ የተሰጣችሁና የብቃት ምዘና ፈተናውን ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ ለምትገኙ የጤና ባለሙያዎች በነሀሴ ወር 2016 ዓ.ም የብቃት ምዘና ፈተና ለመስጠት በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡
ስለሆነም የዚሁ ፈተና ምዝገባ ከነሀሴ 06 - 15/2016 ዓ.ም የሚከናወን ስለሆነ ፈተናውን የምትወስዱ የመንግስትም ሆነ የግል ተቋማት ተመዛኞች በኦንላይን http://hple.moh.gov.et/hple ላይ በመግባት እንድትመዘገቡ እያሳሰብን ከላይ ከተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውጪ ምንም ዓይነት የምዝገባ ጥያቄ የማናስተናግድ መሆኑን አውቃችሁ በተጠቀሱት ቀናት እንድትመዘገቡና ሲስተሙ የሚሰጣችሁን የፈተና መለያ ቁጥር (Registration No) የያዘ ስሊፕ print አድርጋችሁ በመያዝ ስትመዘገቡ በመረጣችሁት የፈተና ጣቢያ በፈተናው ወቅት እንድትገኙ እናሳስባለን፡፡
ማሳሰቢያ፦
-በሰኔ 2016 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር በኩል የተሰጠውን የፋርማሲ ሙያ የመውጫ ፈተና ተፈትናችሁ ያለፋችሁ ተመዛኞች በጤና ሚኒስቴር በኩል የሚሰጠውን የብቃት ምዘና ፈተና መውሰድ የሚጠበቅባችሁ መሆኑን እያሳሰብን ከላይ በተጠቀሰው ዌብሳይት ላይ በመግባት እንድትመዘገቡ እናሳስባለን፡፡
- በሰኔ 19/2016 ዓ.ም በተሰጠው የመውጫ ፈተና አልፋችሁ ዲግሪ የያዛችሁ የአንስቴዥያ ተመዛኞች ይህ የምዝገባ ጊዜ እንደተጠናቀቀ የተግባር ምዘና(OSCE) ፈተና ምዝገባ የምንጀምር መሆኑን እያሳወቅን በትዕግስት እንድትጠባበቁ እንዲሁም ለፈተናው ዝግጅት እንድታደርጉ እናሳስባለን።
- እያንዳንዱ የፈተና ጣቢያ በየሙያ መስኩ ማስተናገድ በሚችለው ከፍተኛ የተመዛኝ ቁጥር ልክ ገደብ ስለተቀመጠለት ተመዛኞች ምዝገባውን ቀድማችሁ በማጠናቀቅ ተጠቃሚ መሆን የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን ከፍተኛው የተመዛኝ ቁጥር በደረሰበት የፈተና ጣቢያ ላይ ተጨማሪ ምዝገባ ማከናወን የማይቻል መሆኑን እናሳስባለን።
- ማንኛውም ተመዛኝ ወደ ፈተና ጣቢያ ሲመጣ ሲስተሙ የሚሰጠውን የፈተና መለያ ቁጥር (Registration No) የያዘ ወረቀት /ስሊፕ/ print አድርጎ ካልያዘ ፈተናውን መውሰድ የማይችል መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን፡፡
- ከዚህ በፊት የብቃት ምዘና ፈተናውን ተፈትናችሁ ያላለፋችሁ ወይም አዲስ ተመዛኞች ከታች በተቀመጠው ማስፈንጠሪያ/Link/ በመጫን ስማችሁን በመፈለግ ስልክ ቁጥራችሁን እንድታስገቡ እያሳሰብን ከዚህ በኋላ ውጤት የምታዩት ወይም ማንኛውም ከብቃት ምዘና ፈተና ጋር የተያያዙ መረጃዎችን ማግኘት የምትችሉት ባስመዘገባችሁት ስልክ ቁጥር መሆኑን እየገለጽን ይህንን መረጃ ሳታሟሉ ቀርታችሁ ለሚፈጠረው ማንኛውም ችግር ኃላፊነት የማንወስድ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
(https://docs.google.com/spreadsheets/d/118unZ6bK8AGLIfMfmFIxCNbeccMkP4yz8kfGBGsGk7s/edit?usp=sharing)
Website: moh.gov.et
Facebook: Ministry of Health, Ethiopia
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: @FMoHealthEthiopia
Tiktok: @mohethiopia