Toleha Ahmed (Official Channel) ☪️ dan repost
የዕውቀት ፈላጊ ተማሪው ይህን ሀዲስ በሸይኽ አብዱረዛቅ አል-በድር ላይ በሚቀራበት ወቅት በሀዲሱ ተመስጦ ዕልቅሻውን መቆጣጠር አልቻለም!
ያ አሏህ ሀዲሱ በጣም ልብን ይነካል ወሏህ
ዕውቀት ፍለጋ የአሏህን ዲን ለመማር መሰባሰብ፣ አሏህን ለማውሳት መሰባሰብ ትልቅ ትሩፋት ነው ያለው
አሏህ ይወፍቀን!
ይህን የሚያስለቅስ የነብያችን ሀዲስ በግርድፉ ልተርጉምላችሁ
ለአሏህ በየመንገዱ የሚጓዙ እሱ የሚወሳበትን፣የሚዘከርበትን ቦታ የሚፈልጉ እና የሚቀማመጡ መላኢካዎች አሉት አሏህን የሚያወሱ ሰዎችን ባገኙ ጊዜ እርስበርሳቸው ይጠራራሉ ኑ....! የምትፈልጉት ጉዳይ እዚህ ነው ይባባላሉ ከዚያም በክንፋቸው ሰማይ እስኪደርሱ ድረስ ያካብቧቸዋል
ወደ አሏህም ሄደው አሏህም እያወቀ ባሮቼ ምን እያሉ ነው በማለት ይጠይቃቸዋል
መላዒኮችም፦ አንተን እያጠሩ እያመሰገኑ እያተለቁ እንዲሁም እያሞገሱህ ነበር ይሉታል
አሏህም፦ እኔን አይተውኛል እንዴ? ይላቸዋል
መላዒኮችም፦ በፍፁም ወሏሂ አላዩህም ይሉታል
አሏህም፦ ቢያዩኝ እንዴት ይሆኑ ነበር? ይላቸዋል
መላዒኮችም፦ ቢያዩህማ በጣም አብዝተው ነበር ዒባዳ የሚያደርጉት በርትተውም ነበር የሚያሞግሱክ ይሉታል
አሏህም፦ እሺ ምንድነው የሚጠይቁኝ? ይላቸዋል
መላዒኮችም፦ የሚጠይቁህ ጀነትህን ነው ይሉታል
አሏህም፦ ጀነትን አይተዋታል እንዴ? ይላቸዋል
መላዒኮችም፦ በፍፁም ወሏሂ አላዩዋትም ይላሉ
አሏህም፦ ቢያዩዋትስ እንዴት ይሆኑ ነበር ይላቸዋል
መላዒኮችም፦ ቢያዩዋትማ በጣም ጉጉታቸው የበረታ ፍላጎታቸውም የጠና እንዲሁም በጣም ለመግባት የከጀሉ ይሆኑ ነበር ይሉታል
አሏህም፦ ከምንድነው በኔ የሚጠበቁት? ይላቸዋል
መላዒኮችም፦ ከዕሳትህ ነው ጌታችን ይሉታል
አሏህም፦ አይተዋታል እንዴ? ይላቸዋል
መላዒኮችም፦ በፍፁም ወሏሂ አላዩዋትም ይሉታል
አሏህም፦ ቢያዩዋትስ እንዴት ይሆኑ ነበር? ይላቸዋል
መላዒኮችም፦ ቢያዩዋትማ ከእሷ በጣም የሸሹ እና ፍራቻቸውም በጣም የበረታ ይሆን ነበር ይሉታል
አሏህም፦ እንግዲህ መስክሩ ለነሱ እኔ ምሬያቸዋለሁ ይላል
ከመላዒካዎች ውስጥ አንደኛው፦ ጌታችን ሆይ ከነዚያ ሰዎች መካከል እኮ ከነሱ ያልሆነ ለሌላ ጉዳይ መጥቶ የተቀመጠ ሰው አለ ይላል
አሏህም፦ እነሱ ሰዎች እኮ አብሯቸው የተቀመጠ ሰውም እንኳን ቢሆን እድለ ቢስ የማይሆነበት ሰዎች ናቸው ይላቸዋል።
አሏህ ሆይ በመጪው ዓለም ፊትህን ከሚመለከቱት ጀነት ከሚገቡት ከዕሳት ከሚድኑት ደጋግ አንተን አስታዋሽ ባሮችህ መካከል አድርገን! አሚን!!!
✍Toleha Ahmed
ይ🀄ላ🀄ሉን👇👇 share👇
┏━ 🍃 ━━━━ 🍃 ━┓
@tolehaahmed
┗━ 🍃 ━━━━ 🍃 ━┛