መውሊድና ነባሩ እስልምና አይተዋወቁም!
{ምስክር እራሳቸው!}
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
በሺርክ የተወረረውን፣ በኹራፋት ያበደውን፣ በመውሊድ የታጀበውን የሱፍዮች እስልምና “ነባሩ እስልምና” እያሉ የሚያሞካሹ ጩኸቶችን አልፎ አልፎ እንሰማለን። ይህንን የማይቀበለውን “ወሃቢ” በማለት በሙሐመድ ኢብኑ ዐብዲል ወሃብ የተጠነሰሰ መጤ ኢስላም እንደሆነ ሊነግሩን ነው የሚውተረተሩት። ይህ “ነባሩ” የሚሉት “ኢስላም” ግን ፍፁም እንግዳ የሆኑ መጤ አስተሳሰቦችን አጭቆ የያዘ እምነት ነው። የዚህ ፎርጅድ “ኢስላም” አብይ መገለጫ የሆነውን መውሊድን እንደ አብነት ብንወስድ ደጋፊዎቹ ሳይቀሩ ከነባሩ ኢስላም ውስጥ የማይታወቅ መጤ እንደሆነ መስክረዋል። ለምሳሌ፡-
1. አቡ ሻማ፡-
“በዘመናችን ከተፈጠሩ ከዚህ አይነት ነገሮች ያማረ ከሆነው የላቀው አላህ ይጠግናትና በኢርቢል ከተማ በያመቱ ከነብዩ ﷺ የልደት ቀን ጋር በሚገጥመው ቀን ይፈፀሙ የነበሩ ሶደቃዎች፣ በጎ ነገሮች፣ ጌጦችንና ደስታን ማንፀባረቅ ነው።” [አልባዒሥ ዐላ ኢንካሪል ቢደዕ ወልሐዋዲሥ፡ 95]
2. ኢብኑ ሐጀር፡-
“የመውሊድ ድርጊት መሰረቱ ቢድዐ ነው። ከሶስቱም ክፍለ-ዘመናት መልካም ቀደምቶች አልተላለፈም።” [አልሓዊ ሊልፈታዊ፡ 1/188]
3. ሰኻዊ፡-
“የተከበረው መውሊድ ተግባር በተከበሩት ሶስቱ ክፍለ-ዘመናት ይኖሩ ከነበሩት ደጋግ ቀደምቶች ከአንድም አልተገኘም። ይልቁንም የተከሰተው ከዚያ በኋላ ነው።” [ሱቡሉልሁዳ ወርረሻድ፡ 1/439]
4. ተዝመንቲ፡-
“የመውሊድ ተግባር በመልካም ቀደምቶች የኢስላም ቀዳሚ ዘመን አልተከሰተም።” [አስሲረቱ አሽሻኒያህ፡ 1/441]
5. አልሓፊዙል ዒራቂ፡-
“ይህንን ነገር ምግብ በማብላት መልኩ እንኳን ከሰለፎች አናውቀውም።” [ተሽኒፉል ኣዛን፡ 136]
6. ሲዩጢ፡-
“የመጀመሪያው ይህን ስራ የፈጠረው የኢርቢሉ ንጉስ ሙዞፈር ነው።” [አልሓዊ፡ 1/189]
(መጤ እንደሆነ መናገራቸውን ለመውሰድ ያክል እንጂ ያጣቀስኳቸው የተጀመረው በሺዐዎች እንደሆነ በማስረጃ አሳልፌያለሁ።)
7. ዘርቃኒ፡- “መውሊድን መፈፀም ቢድዐ ነው።” [ሸርሑል መዋሂብ፡ 1/264]
ይስተዋል። እነዚህ ሁሉም የመውሊድ ደጋፊዎች ከመሆናቸው ጋር ቢድዐ እንደሆነ ግን ባንድ ድምፅ እየመሰከሩ ነው። {ወሸሂደ ሻሂዱን ሚን አህሊሃ።}
የድሮዎቹ መውሊድ አክባሪዎች ከነ ክፍተታቸው ኢንሷፍ ነበራቸው፣ ሚዛናዊነት። ቢያንስ እንዲህ እቅጩን ይናገራሉ። የዛሬዎቹ ግን አይናቸውን በጨው አጥበው እነ አቡበክርንና እነ ዑመርን ሳይቀር መውሊድ አክባሪዎች ሲያደርጓቸው ትንሽ እንኳን አይሰቀጥጣቸውም። አንዳንዶቹማ ከዚህም አልፈው ነብዩን ﷺ ሳይቀር መውሊድ አክባሪ ለማድረግ የማያመነቱ ሃፍረተ ቢሶች ናቸው። ነብዩ ﷺ “በኔ ላይ ሆነ ብሎ የዋሸ ሰው መቀመጫውን ከእሳት ያዘጋጅ!” ብለዋል። [ቡኻሪና ሙስሊም]
ስለዚህ አንባቢ አንድ ቁም-ነገር ሊጨብጥ ይገባል። እሱም መውሊድ በደጋፊም በነቃፊም ኢጅማዕ (ስምምነት) መጤ ፈሊጥ ነው፣ ቢድዐ!! በየመንደሩ ከዚህ የተለየ እያስተጋቡ ለሚበጠብጡ አካላት ይሄ አስደንጋጭ መብረቅ ነው!! “ነባሩ እስልምና” እያሉ ልባችንን ለሚያደርቁ ሁሉ አንድ መልእክት ይድረሳቸው። ነባሩ ኢስላም ማለት የነብዩ ﷺ፣ የሶሐቦች፣ የታቢዒዮች፣ የአትባዑ ታቢዒን ኢስላም ነው። የአራቱ አኢማዎች፣ የነ ቡኻሪ የነ ሙስሊም፣… ኢስላም እንጂ የሱፍዮች ኢስላም አይደለም። ይሄ ኢስላም ነባር ካልሆነ የማን ኢስላም ነው ነባር የሚሆነው?!
እንዳየነው መውሊድ በደጋፊዎቹም በነቃፊዎቹም ኢጅማዕ ቢድዐ ነው፣ መጤ ፈሊጥ። መጤ ደግሞ በየትኛውም አረዳድ “ነባር” ሊሰኝ አይችልም። ስለሆነም መውሊድና ነባሩ እስልምና ፈፅሞ አይተዋወቁም። ስለዚህ መውሊድን የሚቃወመው የተሀድሶ እንቅስቃሴ ወዝጋባ ሱፍዮች እንደሚሉት የሃያና የሰላሳ አመት እድሜ ያለው ወይም በ “ወሃብዮች” የተጀመረ አዲስ ፈሊጥ ሳይሆን ስሩ ከነብዩ ﷺ ዘንድ የሚዘልቅ ከሱፍዮቹ የተንሻፈፈ አረዳድ የቀደመ ጥንታዊ ነው ማለት ነው።
ከ “መውሊድ፤ ታሪክ፣ ግድፈት፣ እርምት” መፅሐፍ ተነካክቶ የተወሰደ