علوم القرآن የቁርኣን ትምህርቶች


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


ይህ ቻናል በአላህ ፍቃድ ዲናዊ አዳዲስ ነገሮችን የምንለቅበት ቻናል ሲሆን በተለይም በቁርዓን ዙሪያ ባሉ እውቀቶች ያጠነጠነ ይሆናል።
https://T.me/IbnuSefa
ለአስያያትም ሆነ ለምክር
👉https://t.me/Ibnu_Sefa በዚህ ሊንክ ይላኩልን
✍ወንድም ሙባረክ ሠፋ

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


ያኢላሂ:'! ዒባዳቸው ቅቡልነት ከሚያገኙ ባርያዎችህ አርገን!


كيف نستقبل رمضان
🎙ወንድም ሙባረክ

https://t.me/IbnuSefa


#أخبار_علم …💡

🌙 لم يتبقَّ على رمضان إلا القليل
وحريٌ بكل مسلم أن يتهيأ لهذا الشهر العظيم من الآن بسماع جميع ما يتعلق به من أحكام ومواعظ تعينه على استقبال هذا الشهر العظيم وحسن استغلاله ، وقد رفعنا لكم على هذه القناة المباركة جمع طيّب من الزاد الرمضاني : 


••اللهم بلغنا رمضان بلوغ توفيق وقبول وحسن  عمل ونحن في عفو وعافية …


➲ጥሩ ሚስት እረፍት ነች💎 ምን አላት ሳይሆን በዲኗ እንዴት ነች ብለህ ጠይቀህ አግባ!!

‏قال الشيخ مقبل بن هادي الوادعي رحمه الله:

"أحسن ما يستريح به العبد في هذا الزمان بعد الإيمان بالله، طلب العلم: والزوجة الصالحة"

- الإمام الألمعي(٢٥٣)




Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish


እዩኝ፣ እዩኝ ማለት
ደብቁኝ፣ ደብቁኝ ማለት ያመጣል


አንድ ሰው ቢያስከፋዎ በመልካም አንደበት ሀሳቦን ለመግለፅ ይሞክሩ።

7122 SMS | ተግባቦት


መህዲ ተብሎ በሚጠራው በዐባሲያው ኸሊፋ ዘመን አንድ ሰው ነብይ ነኝ ብሎ ተነሳ። ወታደሮች አሰሩትና ኸሊፋው ዘንድ አቀረቡት።
* ኸሊፋው፦ "አንተ ነብይ ነህ?" ብሎ ጠየቀው።
- "አዎ" አለ ሰውየው።
* ኸሊፋው፦ "ወደ ማን ነው የተላክከው?" አለው።
- ሰውየው፦ "ወደ ማንስ እንድላክ መቼ ፋታ ሰጡኝ። ረፋድ ላይ ተልኬ ከሰዓት በኋላ አሰሩኝ።

[ረቢዑል አብራር፣ አልባቡ ታሲዕ]




Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish


እራስን መመልከት
~
እየውልህ ወንድሜ! ህሊና አልባ በድን ማሽን አትሁን። የምትገባው ከራስህ እንጂ ከኡስታዝህ ቀብር አይደለም። ሲራጥን የምትሻገረው በራስህ ስራ መጠን እንጂ ኡስታዝህ እጅህን ይዞ አያሻግርህም። ያለ አስተርጓሚ ራቁትህን ከጌታህ ፊት ለምርመራ ስትቆምም ኡስታዝህ ከጎንህ አይቆምልህም። ይህንን ሁሉ የምልህ ማንንም በጭፍን እንዳትከተል ነው። በአሁኑ ሰዓት በየሰፈሩ ያሉ ሸይኾችና ኡስታዞች አብይ መታወቂያ ጭፍንነትን ሥራዬ ብለው የሚግቱ፣ ተማሪዎቻቸውን በጭፍንነት የሚኮተኩቱ መሆናቸው ነው። የወደዱትን በጭፍን እንድትወድላቸው፣ የጠሉትን በጭፍን እንድትጠላላቸው እስከ ደም ጠብታ ይታገሉሃል። ቁርኣን፣ ሐዲሥ፣ የዑለማእ ንግግር ተንኮለኛ በሆነ መልኩ ከአውድ ውጭ እያገናኙ የሃሳብ ሽብር ይነዙብሃል። እዚህ ላይ "ለምሳሌ እነ እንትናን ብንወስድ… " ብዬ ባጣቅስ የእነ እንትና ጭፍራ ጦር ሰብቆ ይነሳል። ከነሱ ውጭ ያለው ደግሞ በአመዛኙ ይደግፋል። እውነት ለመናገር ግን ጣት መቀሰሩ ስለሚቀለን እንጂ ይሄ በሽታ ይብዛም ይነስም በየቤቱ ይገኛል። ችግራችን ግን አይናችን ውስጥ ያለውን ግንድ ጥለን ከሌሎች አይን ያለን ጉድፍ ነው የምንመለከተው። የሌሎችን ጥፋት ለማጋለጥ እንረባረባለን። እሺ የራሳችንንስ ማን ያርመው? ለማነው የምንተወው? ኧረ ልባችን ፈቃጅ ተመልካች አጣ!! ድባቡ የተበከለ ሆኖ መገሳሰፅ አልቻልንም። እኛም ለራሳችን ተገቢውን ትኩረት አልሰጠንም። ግን እስከመቼ? 
እና ወንድሜ ከማንም ጎጠኛ ቡድን ጋር ጭፍን ተሰላፊ አትሁን። ከዑለማእ ንግግር ውስጥ ከስሜቱ ጋር በሚገጥምለት መልኩ እየመረጠ የሚያቀርብ ሰው ስታይ በችኮላ እጅ አትስጥ። የትኛውም ቡድን ጋር የተሰለፈው ሁሉ ይህንን እያደረገ ነውና የሱ ከሌሎች በምን እንደሚለይ ረጋ ብለህ መርምር። የማይነቃነቅ ነባራዊ ሐቅ፣ የአህለ ሱና ዋና መታወቂያ አስመስሎ ያቀረበልህ ጉዳይ አብዛኞቹ ዑለማዎች ዘንድ ያለው አቋም እሱ ካወራህ ተቃራኒ ሆኖ ልታገኘው ትችላለህና ከስሜት ነፃ ሆነህ በሚገባ ፈትሽ። ደግሞ ቆም ብለህ ታዘባቸው። ብዙዎቹ ቡድናዊነት የሰበሰባቸው አካላት:—
— "እነ እከሌ ጠርዘኞች ናቸው፣ ድንበር አላፊዎች ናቸው" እያለ ከፍ አድርጎ ያስተጋባል። የሚያስከነዱ ጠርዘኞችን ግን አቅፎ ያሽሞነሙናል። ምክንያቱም እነዚህኞቹ እሱ ሲስል የሚስሉ፣ ሲያነጥስ የሚያነጥሱ የገደል ማሚቶዎች ናቸውና።
— "እነ እከሌ ጃሂሎች ናቸው" ይልሃል። በምንም መመዘኛ ከነሱ የማይሻሉ ሰዎችን ግን በትልልቅ መድረክ ላይ ያስተዋውቃል። ምክንያቱ አቋማቸው ከአቋሙ ስለገጠመለት ብቻ ነው።
— "እነ እከሌ አቋም የሌላቸው ወላዋዮች ናቸው" ያለህ ስብስብ በየክስተቱ ባደባባይ የሚዋልሉ ሰዎችን ከጎናቸው አሰልፈው ታገኛቸዋለህ። ምክንያቱም መመዘኛው ርካሹ ቡድናዊ ሚዛን እንጂ ኢኽላስ አይደለምና።

ወንድሜ ሆይ! አላህን አስበህ ስለምትሰራው ነገር የማንንም ጭብጨባ አትጠብቅ። የማንም ተቃውሞም አይጠፍህ። ይልቅ ውስጥህን አዳምጥ፣ ኢኽላስህን ፈትሽ። ያለ ኢኽላስ ጩኸትህ የቁራ ጩኸት ነው። ልፋትህም ከንቱ ድካም። በደዕዋህ ቀዳሚው ትኩረትህ ሰፊው ህዝብ ይሁን። አትዘንጋ! ዛሬም አብዛኛው ወገናችን ከተውሒድ ግንዛቤ የራቀ ነው። ሺርክ ላይ የሚማቅቀው ብዙ ነው። ከባባድ አጥፊ ወንጀሎች ላይ እስከ አፍንጫው የተነከረው ቀላል አይደለም። ቀዳሚው ጥረትህ የዚህን ወገንህን ሸክም ለመቀነስ ይሁን። ይህንን መሰረታዊ ጉዳይ ገሸሽ በማድረግ ውሃ ቀጠነ፣ ከሰል ጠቆረ ብሎ ለሚነታረክ ጀርባህን ስጠው። የጊዜ ጉዳይ እንጂ ሁሉም አረፋ ነው።
በኢኽላስ እስከሰራህ ድረስ የማንም ጫጫታ ቅስምህን አይስበረው። ሰዎች እንቅፋት ሲያበዙ አንተ ፅናትህን ጨምር። ወደፊት እንጂ ወደ ኋላ አትበል።
የሌሎችን ጩኸት ሳታጣራ የምታስተጋባ በቀቀን አትሁን። በጭፍን አትደግፍ። በጭፍን አትንቀፍ። እወቅ! እውር ጥላቻና እውር ውዴታ ነገ ከአላህ ፊት ያሳፍርሃል። ማንንም በእውር ድንብር አትከተል። ጭፍን ወገንተኝነት በቃላት ቢያሸበርቅም፣ በሱና፞ ስም ቢቀርብም የተወገዘ ነው። የአሳማ ስጋ በወርቅ ሰሀን ስለቀረበ አሳማነቱ አይቀየርም። አሳማ አሳማ ነው። የመዝሀብ ሰዎች ዘንድ የምናውቀው ጭፍን ወገንተኝነት ተቀባብቶ ተከሽኖ በሱና፞ ዑለማዎች ስም ሲቀርብ ማየት እየተለመደ መጥቷል። ይበልጥ የሚያሳፍረው ደግሞ አንዳንዶች በየሰፈሩ በየመንደሩ እየተቧደኑ ‘ወላእ’ እና ‘በራእ’ የሚቋጥሩባቸው አካላት መመደባቸው ነው።
ደግሞም በልክ እንሁን። በሌሎች ሃገራት ወይም አካባቢዎች ያየነውን ወይም የሰማነውን ኺላፍ ሁሉ ሰበብ እየፈለጉ እየጎተቱ ማምጣት ግልብነት ነው። ወላጆችህ ወገኖችህ በሺርክ እየተጨማለቁ አንተ በሸይኽ እንትናና በሸይኽ እከሌ መካከል ስለተፈጠረው ኺላፍ ጧት ማታ እያቦካህ በአካባቢህ ያሉ ዱዓቶችን ለመፈረጅ አድፍጠህ ብትጠባበቅ የፊትና ጥማትህን እንጂ ንቃትህን አያሳይም። በአካባቢህ ይሄ ነው የሚባል የደዕዋ ተሳትፎ ሳይኖርህ እንዳቅማቸው እየደከሙ ያሉ አካላትን ትንሽዬ ጥረት አይኗን ለማጥፋት ጦር ብትሰብቅ ጥሬነትህን ብቻ ነው የሚያሳየው። ወንድሜ ከቻልክ አግዝ። ክፍተት ካየህ አርም። አቅሙ ከሌለህ ባላቸው አስመክር። በምትችለው ከጎናቸው ቁም። ለሰፈርህ ለአካባቢህ የደዕዋ እንቅስቃሴ አጋዥ እንጂ አፍራሽ አትሁን። ለደዕዋ እንቅፋት በመሆን ሌሎች እንዳይለወጡ መሰናክል አትፍጠር። ሰዎች የሚተላለፉበት መንገድ ላይ አስቸጋሪ ነገሮችን መጣል ፀያፍ ጥፋት ነው። ወደ ኣኺራ በሚወስደው የደዕዋ መንገድ ላይ እንቅፋት መጣል ግን እጅግ አደገኛ ወንጀል ነው። እንዲህ አይነቱን የወንጀል ሸክም የምትቋቋምበት ጫንቃው የለህምና ዛሬውኑ ሚናህን ለይ። ዛሬውኑ ለደዕዋ ያለህን አስተዋፅኦ ገምግም።
=
(ኢብኑ ሙነወር፣ የካቲት 07/2013)




#سورة_الحجر(15)
🎤•القارئ• الشيخ
(( #هزاع_البلوشي ))


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
ከአላህ ትላልቅ ፀጋዎች መካከል ህይወትህን ከቁርዐን ጋር ማቆራኘቱ ነው ።

اللهم اجعلنا من اهل القرآن الذين هم اهلك
وخاصتك 🤲


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish


የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
"ከወንድምህ ፊት ፈገግ ማለትህ ላንተ ሶደቃ ነው።" [አልባኒይ ሶሒሕ ብለውታል።]


በባልና ሚስት መካከል ያለው መኗኗር መሠረቱ፤ ፍቅር እና መተማመን ሊሆን ይገባል።
አሊያ ግን በመካከላቸው የሚያስተሳሰራቸው ገመድ ይሳሳል።
በዚህም የተነሳ አንዱ ለሌላው የስቃይ እና የቅጣት አለንጋ ይሆናል።

https://t.me/IbnuSefa


በሃሜት ያማናቸው ሰዎችን አስመልክቶ ምን ማድረግ አለብን?

ሸይኽ ኢልያስ


#إكرام_الخبز
عن عائشة رضي الله عنها قالت: قال النبي ﷺ:
" أكرموا الخبز ".
(رواه الحاكم وصححه ووافقه الذهبي، وصححه السيوطي وحسنه الألباني).

قال العلامة المناوي رحمه الله:
" وإكرام الخبز أن لا يوطأ، ولا يمتهن كأن يستنجى به،
أو يوضع في القاذورة والمزابل، أو ينظر إليه بعين الإحتقار ".
https://t.me/IbnuSefa

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.